Gadda g*y.
shumka awet, sirahka awet.
bisoh.....................................
Or-filo Al
"Maaqok nahurut mayno tan." Albeshir wale
Qaalam bisoh gexak gexa................................
ሀገራችን የዓለም አቀፍ ሳይበር ደኅንነት ኢንዴክስ ከ34% ወደ 76.3% አድጓል። የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (INSA) ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሀሚድ፤ በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ የተከናወኑ ስራዎች ለቀጣዩ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030"ጉዞ ጠንካራ መደላድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል። ይህን ያሉት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ በተጀመረበት ዕለት ነዉ።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ሀገሪቱን ለቀጣዩ ምዕራፍ አዘጋጅተዋታል። ከእነዚህም መካከል፦
👉የዓለም አቀፍ ደረጃ መሻሻል፦ የኢትዮጵያ የሳይበር ደኅንነት ኢንዴክስ (Global Cybersecurity Index) ከነበረበት 34% ወደ 76.3% ከፍ ብሏል።
👉የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፦ ለኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት፣ ለ"ፋይዳ" (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) እና ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት የሚያገለግለው የሕዝብ ቁልፍ መሠረተ ልማት (PKI) ወደ ሥራ ገብቷል።
👉የሰው ኃይል ልማት፦ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለሙያዎችን ከማፍራት ባለፈ፣ በርካታ ታዳጊዎች የሳይበር ደኅንነት ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።
በቀጣዩ ስትራቴጂ የሳይበር ደኅንነት እንደ አንድ መሠረታዊ የዕድገት መሠረት ተለይቶ የተቀመጠ ሲሆን፣ የሚከተሉት ተግባራት በትኩረት ይከናወናሉ፦
👉የተቋማት ጥንካሬ፦ የመንግሥት አገልግሎት፣ የትምህርት፣ የግብርና እና የጤና ዘርፎች የሚጠቀሙባቸው መሠረተ ልማቶች ከማንኛውም የሳይበር ጥቃት የማይበገሩ (Resilient) እንዲሆኑ ማድረግ።
👉ዲጂታል ማረጋገጫ (Signature)፦ የሕዝብ ቁልፍ መሠረተ ልማትን ለሁሉም ዘርፎች ተደራሽ በማድረግ፣ አስተማማኝ የዲጂታል ፊርማ ሥርዓት መዘርጋት።
👉የግል ዘርፍ ተሳትፎ፦ የግል ተቋማት በሳይበር ደኅንነት ሥራዎች ላይ በስፋትና በጥልቀት እንዲሳተፉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር።
I got over 130 reactions on one of my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Afar Region