አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም

  • Home
  • Ethiopia
  • Adis
  • አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም

አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም ተዝኪያ - ዕውቀት - ዳዕዋ !

18/08/2026
🕌 በውቅሮ ከተማ  መስጂድና መድረሳ ተመረቀበትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ የሚገኘው የአል ዒምራን ኢስላማዊ ተቋም ቅርንጫፍ የሆነው መስጂድና መድረሳ ዛሬ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።...
12/08/2026

🕌 በውቅሮ ከተማ መስጂድና መድረሳ ተመረቀ

በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ የሚገኘው የአል ዒምራን ኢስላማዊ ተቋም ቅርንጫፍ የሆነው መስጂድና መድረሳ ዛሬ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

መስጂዱ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ከተመሰረተ ጀምሮ ለማህበረሰቡ የሃይማኖትና የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ በቀድሞው መስጂድ ምትክ በአዲስ መልክ የተገነባው አዲሱ መስጂድ በቱርክ ሀገር የሚገኘው ሀይደር የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ መገንባቱ ታውቋል።

በተከናወነው እድሳትና ማስፋፊያ የመድረሳው የተማሪዎች ተቀባይነት አቅም ከ60 ወደ 100 ከፍ ተደርጓል።
በክልሉ በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የመድረሳው አገልግሎትም፣ አሁን በአዲስ አቅምና በተሻለ መሠረተ ልማት እንደገና መጀመሩ ተገልጿል።

📚 ከ60 ወደ 100 ተማሪዎች
🕌 አዲስ የተገነባ መስጂድ
📖 የተሻሻለ የመድረሳ አገልግሎት
🤝 ለማህበረሰቡ የተሻለ የዲንና የትምህርት አገልግሎት
አላህ ይህንን መስጂድና መድረሳ የእውቀት፣ የኢማንና የመልካም ትውልድ ማፍራት ምንጭ ያድርገው። 🤲

#አልዒምራን #ውቅሮ #መስጂድ #መድረሳ #ትምህርት #ቁርአን

📖 በአል ዒምራን የክረምት ኮርስ ከወላጆች ጋር ገንቢ ውይይት ተካሄደበአል ዒምራን የቁርአንና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም የሚሰጠው የክረምት ኮርስ በአላህ ፈቃድ በውጤታማ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይ...
01/08/2026

📖 በአል ዒምራን የክረምት ኮርስ ከወላጆች ጋር ገንቢ ውይይት ተካሄደ

በአል ዒምራን የቁርአንና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም የሚሰጠው የክረምት ኮርስ በአላህ ፈቃድ በውጤታማ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት ከተማሪዎች ወላጆች ጋር ስለ እስካሁን የተካሄደው የትምህርት ሂደት፣ የተገኙ ውጤቶች እና ለወደፊት የሚደረጉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩም የተቋሙ ኃላፊዎች ኡስታዝ አስለም፣ ኡስታዝ ዓብዱል ፈታህ፣ ኡስታዝ ሙሐመድ ዚያድ እና ኡስታዝ ዓዲል ለወላጆችና ለተማሪዎች ጠቃሚ እና ምክር አዘል መልእክቶችን አስተላልፈዋል።

🌸 በመጨረሻም ተማሪዎች ለአንድ ቀን የእረፍት ጊዜ ተሰጥቷቸው ከወላጆቻቸው ጋር ተመልሰዋል።

🤲 አላህ (ሱ.ወ) የተማሪዎቻችንን እውቀት ይጨምር፣ ወላጆቻቸውንም በበጎ ይመንዳ።

#አልዒምራን #ቁርአን

📢 ማስታወቂያ🕌 የቁርኣን ሂፍዝ መድረሳ መግቢያ ፈተናየፊታችን እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓ.ል. በአዲስ አበባና አካባቢዋ የምትገኙ፣ ወደ አልዒምራን ኢስላማዊ ተቋም እና ቅርንጫፍ መድረሳዎች ገ...
30/07/2026

📢 ማስታወቂያ

🕌 የቁርኣን ሂፍዝ መድረሳ መግቢያ ፈተና

የፊታችን እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓ.ል. በአዲስ አበባና አካባቢዋ የምትገኙ፣ ወደ አልዒምራን ኢስላማዊ ተቋም እና ቅርንጫፍ መድረሳዎች ገብታችሁ ቁርኣን የማሃፈዝ ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች በሙሉ ተጋብዛችኋል።

📅 ቀን: እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓ.ል.
🕑 ሰዓት: ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30
📍 የፈተና ቦታ:
• አልዒምራን (CMC) መድረሳ
• ሀምዛ አደም በዳኔ መድረሳ

በመሆኑም መድረሳውን ለመቀላቀል ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት ፈተናውን እንድትወስዱ በአክብሮት እናሳውቃለን።

🤲 አላህ በእውቀትና በቁርኣን ይጥቀመን!

إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَለረዥም አመታት በዳዕዋ ስራ የሚታወቁት የወንድማችን ቃሪእ ዐብዱልሙዒን አባት ሼኽ ኑረዲን ወደ አኼራ ሄደዋል።የጀናዛ ሶላ...
28/07/2026

إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

ለረዥም አመታት በዳዕዋ ስራ የሚታወቁት የወንድማችን ቃሪእ ዐብዱልሙዒን አባት ሼኽ ኑረዲን ወደ አኼራ ሄደዋል።
የጀናዛ ሶላት እና ሽኝት ዛሬ ማክሰኞ
ዙሁር ላይ ኮልፌ እስላም መቃብር የሚከናወን ይሆናል።
አላህ (ሱ.ወ) ራሕመቱን ያውርድላቸው፤ መቃብራቸውን የጀነት ጨፌ ያድርግላቸው፤ ለቤተሰቦቻቸውም ሰብሩን ይስጣቸው።

19/07/2026

በመልካም ስራ ወደ አላህ መቅረብ!!
ኡስታዝ ሙሀመድ ዚያድ
https://t.me/Alimrancmc

14/07/2026

ክረምቱን ምን ላድርግ?

13/07/2026

ጥላቻ...

إنا لله وإنا إليه راجعونለዲን በቅንነት መልፋትን፣ ምንዳንም ከአላህ (ሱ.ወ) ብቻ መጠበቅን በተግባር ያስተማሩ ታላላቅ ስብእናዎች ዱንያን ሲለቁ በኡማው ውስጥ ትልቅ ክፍተት ይተ...
10/07/2026

إنا لله وإنا إليه راجعون

ለዲን በቅንነት መልፋትን፣ ምንዳንም ከአላህ (ሱ.ወ) ብቻ መጠበቅን በተግባር ያስተማሩ ታላላቅ ስብእናዎች ዱንያን ሲለቁ በኡማው ውስጥ ትልቅ ክፍተት ይተዋሉ።

ሼህ አብዶሽ (ረሒመሁላህ) በዳዕዋና በተብሊግ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም በታላቁ አንዋር መስጂድ የሴቶች የዳዕዋና የተርቢያ ሥራ ላይ የማይረሳ አሻራ ካሳረፉ ታላላቅ ስብእናዎች መካከል አንዱ ነበሩ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊሞች መቃብር የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈጽሟል፤ ወዳጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው በዱዓና በመልካም ምስክርነት ሸኝተዋቸዋል።

አላህ (ሱ.ወ) ይማራቸው፣ ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃቸው። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ህዝብ ውብ ሶብርን ይለግሳቸው።

አላህ በህልፈታቸው የተፈጠረውን ክፍተት በተሻሉ ሰዎች ይሙላልን፤ በሀዘናቸው የተሰበሩ ልቦችንም ያጽናናልን።

اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه، وأسكنه الفردوس الأعلى.

Address

+251 90 646 1111(What’s App)
Adis

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to አል-ዒምራን Cmc የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምሕርት ተቋም:

Shortcuts

Share

Category