አንድነት ሀይል ነው

አንድነት ሀይል ነው

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አንድነት ሀይል ነው, Addis Ababa.

28/07/2023

ብዙ ጊዜአችንን ስለሠላም ባሠብን እና ባአሰላሠልን ቁጥር በውስጣአችን የተሠገሠገውን የክፉ ነገር ማጠራቀሚያ ቱቦዎች እየተደፈኑ እና እየጠፋ የመሄድ ዕድላቸው ሠፊ ነው።

ሠላም በሠው ልጅ የኑሮ ሚስጢር ውስጥ ትልቁን እና የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል።ሠላም ከጠፋ ሁሉም ነገር ዋጋው እየጠፋ እና ያለን ነገር ሁሉ ከአካባቢያችን እየራቀ ይጓዛል።የሁሉም ነገር ማጠንጠኛው ሠላም ነው።

ሠላም በሀገራችን በየጊዜው በእጅጉ እየተፈተነ ይገኛል።ሠላምን የሚጠላ ሁሉ የሀገር የመጀመሪያው ጠላት ነው።ምንአልባትም ለሠላም መጥፋት ዋነኛው መነሻ ኢ-ፍታታዊ የሆኑ የነገሮች ፍላጎት በውስጣችን ስለሚመላለሱ እና ስለምንፈልግም ነው።ይህ ኢ-ፍትሃዊ የግለሠቦች ሀሳብ እያደገ ይሄድ እና የቡድኖች ፍላጎት ይሆናል።በሂደት የአንድ ትይቅ አካል ጉዳይ ሆኖ ወደ ጦርነት ያመራል።ነገሩ ግን የተነሳው ከአንድ ግለሠብ የኢ-ፍታሀዊ ፍላጎት አስተሳስብ ነው።

ሁሌም ሠላምን ለመጨበጥ ከራሳችን ይልቅ ለሌሎች ፍላጎት ቦታ መሥጠት ያስፈልጋል።ይህ ድርጊት በብዙዎች ዘንድ ሲተገበር እና ሲመላለስ አንዳአችን ለአንዳችን ሠላም መስጠትን እና መሸጥን እንጀምራለን።ስለዚህ በተሠጠን ጊዜ ሁሌም ስለሠላም ማለትም ስሌሎች ሠላም እናስብ እንጨነቅ በዋጋው ሁላችንም እንጠቀማለን ።ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው።

28/07/2023

የሰከነ አንደበት አገር ይገነባል እንጅ አያፈርስም።

ሀገራችን የአሰበችውን ዕቅድና ተግባር ለማሳካት የሰከነ አንደበት አስፈላጊ ነው። ዛሬም ወጣ ገባ በማለት የሚከሰቱ ችግሮች አይነ ግቡ በሆነ መንገድ በየአቅጣጫው ማየትና መመልከት ይጠበቅብናል።

በሀገር ላይ ሰላም እንዲሰፍን ባለመውደድና የህዝብን ለውጥ ባለመፈልጉ ሀገር እንዳትለማና እንድትፈርስ በዕቡዕ የሚንቀሳቀሱ አስመሳይ የሆኑ የሰው ደም አፍሳሾችን ለመምከርና ለማስተማር የሰከነ አንደበት ያስፈልጋል።

የነገ ሰላምን በመሻት የሀገር ፍቅር ሳይሆን በሰሜት መጫጫን ምክንያት ንፁሀን የሆኑ ወጣቶችና የነገ የሀገር ተረካቢ ሙህራንን በመገፋፋት የቀውሱ ሰለባ እንዳይሆኑ ለማድረግ ህዝቡ የሰከነ አንደበት ኖሮት የራሱን ሰላም ራሱ ማረጋገጥ አለበት።

26/07/2023

ለአማራ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የማንም ህይወት መጥፋት የለበትም

አቶ መካሻ አለማየሁ
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ሁልጊዜም ንግግርና የሀሳብ ፉክክርን የሚያምኑ እንደሆኑ ይነገራል።የሰላምን መንገድ አጥብቀው የሚደግፉት እኚህ መሪ በሰሞኑ የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ ላይም ሰላም ለሁላችንም የሚገባና ተጋግዘን በመመካከር የምናመጣው መሆን አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የአማራ ደም መፍሰስ እንዴት መፍትሄ ይሆናል ያሉት አቶ መካሻ በክልሉ የአማራ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ የሚሳተፍበት ምክክር እንዲካሄድ ጠይቀዋል።

የክልሉ ምክር ቤት የምክክር አማራጭን ያፀደቀው ሲሆን እኚህ መሪና የአመራር ቡድናቸው በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ ማንንም የማይገፋ አሉ የሚባሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ሁሉ የሚደመጡበት ምክክርን ለማስኬድ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል።በመላው ሸዋ የምትገኙ ምሁራን፣ወጣቶች፣ባለሀብቶች፣የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ፖለቲከኞች ሁሉ ለምክክሩ ከጎናቸው እንደምትቆሙና ቀጠናውን ወደ ተሟላ ሰላም እንደምትመልሱት እጠብቃለሁ።

Via Mangedot Ashebr

25/07/2023

የህዝብ ልጅ

የህዝብ ልጅ የሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ዛሬም እንደ ትላንቱ ሀገራችን ታሪካዊ ክብሯን እና በጀግንነት አለም ያላትን ተምሳሌት አስጠብቆ በድል እንደዘለቀ ነው።

ከውስጥም ከውጪም በጠላት የተቃጣበትን ጥቃት በመቀልበስ ድል ያደረገ ጀግና ሰራዊት ነው።

24/07/2023

የወንድም ጠላት አትሁን ። እኔ የምለፋው የአንተን ደህንነት ለማስከበር ለሰላም ነው።

ወንድም በችግሮች ላይ በመምከር ለችግሮች የጋራ የሆነ መፍትሄ ያመጣል እንጅ ከፊትህ ቀድሞ ጨለማውን ገፎ ብርሀንን ለመስጠት የሚታትርልህን ወንድም የክረምት ጉም ለብሰህ እንዴት ለማጥቃት እንዴት ትጥርና ትፈፅማለህ ።

ከዚህ በላይ የህወሓት ስልጣን ፈላጊ ቡድን ምን አደረገ..?

እኔ የምለፋው ስርዓተ አልበኝነትን ለመፈፀም ቀን ከሌሊት ዕቅድ አድርገው በህዝብ ዘንድ ቀን ከሌሊት የጥላቻ በትርን የሚያሳርፉትን የህግ ስርዓትን እንዲከተሉና አንተ ሰላማዊ ህይወትን እንድተኖሩ የገባሁትን ቃል ለመተግበር እንጅ አገር እንድትፈርስ አይደለም።

ዛሬ እኔ ብሞት ሌላ እኔን መተካት የሚችሉ እልፍ ኢትዮጵያዊያን አሉና የትም ተወለድ የትም ተፈጠር የህዝብን ተጠቃሚነት ለማትረፍና ሰላምን ለማረጋገጥ በወንድማማችነት ሰራ።

21/07/2023

የውስጥ ፀረ ሰላሞች የጠላቶቻችን ጉልበቶች ናቸው

የአማራን ህዝብ ወደ አደገኛ ቅርቅር የመጎተት ጥረት ላይ የሚገኙ የውስጥ ፀረ ሰላሞችን በየሚገባቸው ቋንቋ አናግሮ ወደ ስርዓት ማምጣት ይገባል።እነዚህ ሀይሎች ህዝቡን የሚያወናብዱና ወዳጁ መስለው ቀና በማይልበት ደረጃ ለጠላት እያመቻቹት ነው።

የአማራ ህዝብ በውስጡ ሰላምና ህብረት ከተለየው የማንም መጫወቻ ነፃ ካርድ ይሆናል።አሁን በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ሆነው በየቦታው ጥይት የሚያጮሁትና ፕሮፓጋንዳ የሚነዙት አካለት ትናንትም ለጠላት ስልታዊ መንገድ አስከፋች የነበሩ ናቸው።

የአማራን ህዝብና የመከላከያ ሠራዊትን ደም ለማቃባት የሚፈልጉት እነዚህ ተንኳሽና ቀስቃሽ ሀይሎችን በቃችሁ እንበል።የኢትዮጵያን የመከላከያ ሠራዊት በማይገባ መልኩ በመጥራት እና ህዝብን ለማዛባት በመሞከር ላይ መሆናቸውን በግልፅ ይታያል።ይህ ጀግና ሠራዊት ከሁሉ የተውጣጣና የሁሉ ዘብ የሆነ ነው።የህዝብን ሰላም ነስተው በትርምስ ውስጥ የሚመኙትን ነገር ለማሳካትና ከተጠያቂነት ለማምለጥ በሚያደርጉት ሩጫ መሸወድ አይገባም።

18/07/2023

የጸረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመተጋል ኃገራዊ ግዴታችንን እንወጣ !!

ከአገር ጥቅም ይልቅ የግል ፍላጎትን ለማሳከት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚታትሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ተበራክተዋል። በመደበኛ ተግባር እንቅስቃሴ ስራቸውን ሰርተው መለወጥ ያቃታቸው አገርን በማደፍረስ ሃብት ለማካበት ነው ዓላማቸው።

ስለሆነም የጸረ-ሰላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ በመታገል ሀገራዊ ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል።

15/07/2023

ሰው በመግደል ለተጠመዱና አስገድሎ ከፍ ማለት ያለ ለመሰላችሁ ሁሉ

የአማራ ህዝብ ፈተና ያነሰው ይመስል በመንፈስ ስካርና ቀቢፀ ተስፋ ውስጥ በገቡ ጥቂት ጭ**ራቆች አቀጣጣይነትና በብዙ ጠላቶቻችን መሻት ጀግኖችን የመግደል ሂደቱ እንዳይቆም እየተሰራ ነው።

በመጀመሪያ በፈጠራ ስም ይዘመታል።ሲመችም ገድሎ አበጃችሁ ይባላል።ከመጣንበት መንገድ ባልተማሩና የሚደርሱበትን ያላወቁ እነዚህ አካላት አማራን አሳናሾችና ተሸናፊዎች ናቸው።

ሁሌም የምንፈልጋትን ሰላም በህግ የበላይነት ካላጀብናት የስርዓት አልበኞች መጫወቻ እንሆናለን።

ህግ ይከበር ሰላም ይንበር።

Photos from በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 18/06/2023
18/06/2023

"ስንተባበር ውጤታማነታችን ይረጋገጣል የህዝባችንም ችግሮች ይፈታሉ"

አቶ ግዛቸው ነገሰ
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ

የልማት አቅሞቻችን በተባበረ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ የውጤታማነት ምስጢር መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል።አቶ ግዛቸው የዞኑን አስተዳደር ወክለው በወርልድ ሰርቭ ኢንተርናሽናል በተሰሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ምርቃት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይህን ያሉት።

ስንተባበር ውጤታማነታችን ይረጋገጣል የህዝባችንም ችግሮች ይፈታሉ ያሉት አቶ ግዛቸው የዞኑ አስተዳደር ሁሉንም የልማት አቅሞች አቀናጅቶና ደግፎም ለህብረተሰብ ለውጥ እንደሚሰራ ገልፀዋል።ወርልድ ሰርቭ ኢንተርናሽናል ትልልቅ ስራዎችን በአነስተኛ ወጭና በአጠረ ጊዜ በመስራት ለህብረተሰቡ ላደረገው አበርክቶም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በቀጣይም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ ዞኑ መጥተው በየትኛውም ዘርፍ ለሚያደርጉልን ድጋፍ አስተዳደሩና ማህበረሰቡ ቀና ትብብራቸውን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

~~~
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ -ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

ቴሌግራም፦

https://t.me/shewaprosperity

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064788996103

ቲዊተር፦
https://twitter.com/ShewaNorth?s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=8dEh8MoumH7&_r=1

ዩቲዩብ
https://youtube.com/

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa