03/10/2025
መንግስት ደሞዝ ጨመረ? ኢኮኖሚስት ባልሆንም
ጭማሪ የተባለው የመንግስትን እንጅ የደሞዝተኛውን ችግር የሚቀርፍ አይመስለኝም ለምን እንበል።
ማሳያ 1
ደሞዙ 13,998 የነበረ ሰው በአዲሱ ጭማሪ 25,285 ሆነ። ደስ አይልም? እጥፍ በሉት። ነጋዴው፣ አከራዩ ወዘተ ደስታ ደግሞ ይለያል። ጭማሪያቸው እጥፍ ድርብ ይሆናል። (በቅርቡ እንኳን የሽንኩርት ዘይትና ቲማቲም ዋጋ ጭማሪው ያስተዛዝበናል።) በፐርሰንት ስንት እንያዝበት?...
ደሞዝተኛውስ?
ብሩን ሊወስድ ሲሄድ የስራ ግብር ከ25% ወደ 35% ፐርሰንት አድጓል። ይለዋል። ጋሽ ጡረታም 7% ፐርሰንት አለሁ ይለዋል። ለሸመታ ስትወጣ በድጋሚ እንደነጋዴው የማይመለስልህ (የቫት ተመላሽ) የማይደረግለትን 15% ወዬ ይለዋል። ወይኔ በላቸው!
እንደምረው
የስራ ግብር 35%
ጡረታ 7%
ቫት 15%
ወቸው ጉድ የደሞዝተኛው ደሞዝ 57% (14,412.45) ሆኖ ለከፈለን አካል ተመላሽ ሆኖ ያርፈዋል። በእጁ ስንት ገባ? 10,872 (አስር ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ሁለት) ሆኖ አረፈው። አስቡት አሳይቶ መንሳት አይሆንም? ብዙ የተወራለት ደሞዝ ጭማሪ ትርፉ በነጋዴዎች የባሰ መመዝበርና ከድጡ ወደ ማጡ ይሆነዋል። እሽ እንቀጥል...።
የሚደንቀኝ ፖለቲከኞቹ ሳያውቁት የሆነ ክስተት አይደለም። የቲኦቲን ጉዳይ ሰምታችኋል። ቅድሚያ ከ2% ወደ 15% አስረው ይህን አስከተሉት። የህዝቡ በተለይ የደሞዝተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ያለመ ሳይሆን በዘዴ የተቀመረ ለፖለቲካ አላማ ስኬት ሐምሳ ዜና የተሰራለት መንግስታዊ ሿሿ መሆኑ ልብ ይሏል።
እንቀጥል....
በቀድሞው ደሞዝ 13,998 የተጣራ በእጅ የሚገባው 10,998 አከባቢ ነበር። በአዲሱ ደግሞ 14,412 ልዩነቱ 3600 አከባቢ ነው። እሱንስ ማን አየብን የሚል አይጠፋም! ከዶሮው ሲባጎው በለጠ ከጥቅሙ ጉዳቱ በዛ። ዜናው ወከባና ግርግር አበዙ። የተጨመረው 3600 በዜናው ምክንያት ከሚከተለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት አንፃር ነጌቲቭ ላይ ማረፉ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።
ይቀጥላል...