18/05/2021
አርማጌዶን ...
• ፩. የአርማጌዶን ጦርነት ምንድነው ?
አርማጌዶን ቃሉ ( አርም + መጊዶ ) ከሚሉ ሁለት የአብራይጥ ቃላቶች የተዋቀረ ሲሆን ፣ አርም በእብራይስጥኛ ተራራ ማለት ነው ፥ መጊዶ ደግሞ አሁን በፍልስጤም የምትገኝ አንድ ግዛት ነች ።
••• ትርጓሜውም የመጊዶ ተራራ ማለት ነው ።
ይህ ቦታ በአለም ፍፃሜ የእግዚአብሔር ጠላቶች ከበጉ ጋር ለመዋጋት የሚሰባሰቡበት መጊዶና የመጊዶ ተራራ ነው። ይህ ሰፊ ሸለቆ ሀያ ሁለት ኪሎ ሜትር ስፍትና ሰላሳ ሁለት ኪሎ ሜትር እርዝማኔ አለው ። ሰይጣን የክርስቶስን ዳግም ምፅአት ለማደናቀፍ የመጨረሻ አማራጬ ነው ለሚለው የአርማጌዶን ጦርነት የዓለም ነገስታትን ወደ አርማጌዶን ለማስከተት ከዘንዶው ፣ ከአውሬውና ከሀሰተኛው ነብይ አፍ የሚወጡትን ሶስት እርኩሳን
መናፍስት በመላው ዓለም ያሰማራል። (ራዕ 16 ፥ 13 - 15)
በዚህ ግዜ የዓለም ነገስታት ወደ ስፍራው የሚሰባሰቡት በዓለም ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማረጋገጥ ቢመስላቸውም ሰይጣን ግን አንዴ አስቷቸዋልና ከዚያ የዘለለ አላማውን ለማስፈፀም ይጠቀምባቸዋል።
ዓለም በፍፃሜዋ ጠርዝ ላይ ቆማ ለማድረግ በምትዘጋጀው በዚህ የአርማጌዶን ጦርነት የምድር መሪዎች ራሳቸውን በትህትና ለእግዚአብሔር ዝቅ
ከማድረግ ይልቅ እግዚአብሔርን ተሳድበው መሞትን ይመርጣሉ ።
••••• (ዩሃንስ ራዕ 19 ፥ 19 - 21) እንዲህ ይላል :-
"በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎችንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገድታት ጭፍራዎችም ተከማችተው አየሁ ።
አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን ያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉም የሰገዱትን ያሳተ ሀሰተኛው ነብይም ተያዘ ፤ ሁለቱም በህይወት ሳሉ በዲን ወደ ሚቃጠለው እሳተ ባህርተጣሉ ። የቀሩትም በፈረስ ላይ በተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ ወፎችም ሁሉ ከስጋቸው ጠገቡ" ይላል ።
የሰይጣን የአርማጌዶን ጦርነት ተልእኮ ከክርስቶስ ጋር ተዋግቶ ክርስቶስን የማሸነፍ ተልእኮ እንዳልሆነ ሰይጣን ጠንቅቆ ማወቁን በራሱ ላይ የተናገረውን
ምስክርነት በቂ ነው ተመልከቱ ፦
••• "ተው የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ ፥ ከአንተ ምን አለን ? ልታጠፍን መጣህን ?
ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ አለ" ሉቃ 4 ፥ 34
ስለዚህ የሰይጣን የአርማጌዶን ጦርነት ተልእኮ ብዙዎች እንዲድኑ የሚታገሰው ኢየሱስ በምፅአቱ እንዲዘገይ ወይም ምፅአቱ እንዲሰናከል
የማድረግ ከንቱ ሙከራ ነው ።
መፅሀፉ "ጥበብ በዚህ አለ ... አእምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነው ቁጥሩም 666 ነው" ይላልና ... ራዕ 13 ፥
18
በዩሃንስ ራዕ 22 ፥ 11 - 13 ላይም እንዲህ ይላል ፦
••• " ዓመፀኛውም ወደፊት ያምፅ ፣ እርኩሱም ወደፊት ይርከስ ፣ ፃዲቁም ወደፊት ፅድቅ ያድርግ ፣ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ ... እነሆ በቶሎ እመጣለሁ
ለእያንዳንዱም እንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ" ይላል።
ማጠቃለያ ከፍም ሃሳብ ...
እንግዲህ ከላይ ከተለያዩ ቦታዎች ያገኘናቸውን መረጃዎች አዋቅረን አንድ ወጥ መረጃ አቅርበናል ... አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር አለም ወደ
"አርማጌዶን እያመራች ይሆን ?" ... ይህ የኛም ጥያቄ ነው።