03/04/2026
የአሏህ ነን አሏህ የወደደውን እንወዳለን ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ነጅብ ረመዷን ማገባደጃ ላይ ልዘይራቸው ባቀናሁበት ጊዜ ልዩ አቀባበል አድርገውልኝ የማረሳ ቆይታም አድርገን ነበር እነሆ ዛሬ ወደማይቀረው ሀገር መሻገራቸውን ሰማሁ ሐዘኑ እግጅ የበረታ ነው። በቆይታችንም ስለ ታላላቅ የዳና ከዋክብቶች ታሪክ ፤ ስለ ዑለሞቻችን አይተኬ የዲን ሚና ፤ ስለከፈሉት ተጋድሎና አበርክቶ በሲፊው አጫውተውኝ ነበር።
ሸይኽ ሙሐመድ ነጅብ የታላቁ ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዳና ልጅ ሲሆኑ የታላቁ ዳና ሐሪማ አምስተኛ ኸሊፋም ነበሩ የዑለማዎች ማለፍ ለዑማው ትልቅ ህዘን ብሎም የዕውቀትና የተርቢያ አባቶችን ማጣት ነውና ሁላችንም ዱዓእ እንድናደርግ እያስታወስኩ ለሸይኻችን አሏህ የመልካም ስራዎቻቸውን ምንዳ እጥፍ ድርብ አድርጎ በሰፋው እዝነቱ በጀነት ያስደሳልን ዘንድ እማጸናለሁ። ለቤተሰቦቻቸው ፤ ለደረሶቻቸው ፤ ለወዳጅ ዘመድና ለመላው ሙስሊም መጽናናትን እመኛለሁ።
የደጋጎጎች የታላላቆች መሸኘት ለኛ ትልቅ መልክት አለውና ወደ አሏህ እንመለስ ምትካቸው ይበዛ ዘንድ ወንድም እህቶቼም ጣት ማታ በዱዓእ እንበረታ።
أعظم الله أجرنا وأحسن عزائنا وغفر لميتنا.إنا لله وإنا إليه راجعون .
ሸይኽ ዑመር ኢማም /Sheikh Umar Imam