26/10/2025
ሰላም ለሁላችሁ
ይህ ፌስ ቡክ ከብዙ የሀሳብ ውጣ ውረድ በኋላ የተከፈተ ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ጊዜያት ፈተናዎች ገጥሟታል በዚህም በጸሎት በምህላ በምእመናን እና በአገልጋይ በቅዱሳን ጸሎት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በመላእክት ጥበቃ በአምላካችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ምህረትና ቸርነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከነሙሉ ክብሯ እዚህ ዘመን ደርሳለች በአለም ፈተና የማይቀርና የክብር አክሊልን እንደሚያስገኝ ብናውቅም እጅግ አደገኛ የሆኑ ፈተናዎች ግን ትውልድን የሚመርዙ ስርዓት የሚያፋልሱ የሰው ልጅን ከተፈጠረበት ዓላማ የሚያስወጡ ከጽድቅ መንገድ የሚያርቁ ብዙ የሰው ልጅን ለሲኦል የሚያዘጋጁ ሆነው ሲገኙ እጅግ ከባድ ናቸው ስለዚህ በአፈታሪክ፣በመጽሐፍ፣በቃል የተሰበከልንን አንድ ሃይማኖታችንን ኦርቶዶክሳዊት ቀጥተኛዋና ዘላለማዊ ሕይወት የምታሰጠዋን እምነታችንን የውጭ ፈተናን ተቋቁማ እያለች በራሷ ልጆች እና ልጆቿ መስለው ውስጧ ባሉ አገልጋዮችና ምእመናን መፈተን ግን ከሁሉም የከፋ ነው ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት ቀኖና በተቻለን መጠን ከሊቃውንት አባቶች ጋር በመመካከር ከመጽሃፍ ቅዱስ በማመሳከር አካሄዳቸው ከስርዓተ ቤተክርስትያን ያፈነገጡ አገልጋዮችንና ምዕመናን የምንገስፅበት የምንማማርበት እንዲሆን በማሰብ ከፌስቡክ በተጨማሪ ‘’ስለ ጽዮን ዝም አልልም” በሚል ቲክ ቶክ የተለያዩ ምስሎችንና ድምጽን በማጋራት በመረጃ በቅንነት ለቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መከበር ለሚያስቡ ሁሉ አካውንቱ ክፍት ሆኖ ያገለግላል አብሮነታችሁ አይለየን።
ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አክብረን እናስከብር ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን።