Selsmanshep

Selsmanshep

Share

ሳልሳዊ

Photos from Selsmanshep's post 16/12/2025

ሚስቱ ለሀብት ብላ መንታ ልጆቹን ጥላለት ሄደች! አባታቸው አፈር ልሶ አስተማራቸው ! የግል ጀት ገዝተው ተመለሱ! ጥላቸው የሄደችው እናት ከተሳካላቸው በኋላ ተመለሰች ምን መልስ ሰጧት! አባት ልጆቹን ብቻውን ለማሳደግ ያየው መከራ እና ስቃይ በቃል የሚገለፅ አይደለም! ልጆቹ ስቃያቸውን ወደ ድል የቀየሩበት መንገድ ለሁላችንም ትምህርት የሚሰጥ ነው። አሁኑኑ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ

https://youtu.be/8SaBwdd5Jss

Photos from Selsmanshep's post 16/12/2025

ከትላንት ወዲያ አወስትራሊያ ሲድኒ ውስጥ ሁለት ታጣቂወች ቦንዲ የሚባል የባህር ዳርቻ ተኩስ ከፍተው በአል የሚያከብሩ አይሁዶችን መጨፍጨፍ ጀመሩ። (ሰምታችኋል ሌላ ምን ስራ አላችሁ እዚሁ አፍጥጣችሁ ነው የምትውሉት) እና አገሬው እግሬ አውጭኝ ሲልና እግሩ ያላወጣው በጥይት እየተመታ ሲወድቅ አንድ የ43 ዓመት ጎልማሳ፣ ያውም የሁለት ሴት ልጆች አባት፣ የሶሪያ ስደተኛ፣ ሙስሊም... ዘሎ አንዱን ተኳሽ አነቀው። ማነቅ ብቻ አይደለም መሳሪያውን ነጠቀው።

አህመድ አል አህመድ ይባላል። ራሱ ቆሰለ ግን ካርታ ሙሉ ጥይት ሊጨፈጭፈው የሚችለውን ህዝብ ታደገ። ይታያችሁ ይሄ ሰው ሙስሊም ነው፣ ሶሪያዊ ነው፣ አይሁዶች ሲባል መጀመሪያ አገሩ ላይ የተደረገውን ሙስሊሞች ላይ የሆነውን ሁሉ ማሰቡ አይቀርም፤ ግን የግፍ ጭፍጨፋ የትም በማንም ላይ ልክ አይደለም አለ ፣ ከእኔነት ወጥቶ ነፍሱን ሰጥቶ ህዝብ ታደገ! አወስትራሊያ በጠቅላይ ሚንስትሯ በኩል ብሔራዊ ጀግና አለችው። በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ከመላው አለም በዶኔሽን ጎረፈለት(ሆስፒታል ነው)

የገረረረረረረረመኝ ነገር ...ኔትንያሆ የሚባል እንጉልፋቶ ሰውየ ምን ቢል ጥሩ ነው?
"አንዱን ተኳሽ ተናንቆ ብዙሃን እንዳይገደሉ የታደገው ((( የኛው አይሁድ ነው)) ቪዲዮ ባይኖርና ልብሳቸውን ጥለው ሲሮጡ ባናይ እሽ። ይሄን ሰውየ እንዲህ ዓለም ያየውን ከካደ ጋዜጠኛም ምስክርም በሌለበት የፍልስጤምና ሶሪያ ንፁሐን ላይ በቲቪ እየቀረበ የሚቀባጥረውን ማን ያምናል?

Photos from Muaz Habib ሙዓዝ ሐቢብ's post 05/12/2025
Photos from ‎Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو‎'s post 01/12/2025
29/11/2025

🏆🏆🏆

አዶናይ “ Ethiopian 2025 Best motivational content “

አዋርድ አሸናፊ ሆኗል ::

እንኳን ደስ አለህ ወንድማችን

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

17/11/2025

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ‼

በመካና መዲና አውራ ጎዳና ላይ በደረሰ አሰቃቂ አደጋ የ42 ዑምራ ተጓዦች ሕይወት አለፈ።

ለሊት ዑምራ ተጓዦችን የጫነው አውቶቡስ ከነዳጅ ጫኝ ታንከር ጋር በመጋጨቱ፣ በታንከሩ ውስጥ ባለው ነዳጅ ምክንያት አውቶቡሱ በእሳት ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል። አደጋው የደረሰው ከመዲና 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሙፍሪሀት አቅራቢያ ነው።

በአደጋው ጊዜ አብዛኛው መንገደኞች አንቀላፍተው ስለነበር ከሞት መትረፍ አልቻሉም። በአውቶቡስ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ፣ አንድ ሰው ብቻ በሕይወት ተርፎ ጉዳቱ ከባድ መሆኑ ተገልጿል።

በሟቾቹ መካከል 11 ሴቶች እና 10 ሕፃናት ሊኖሩ እንደሚችሉ እየተዘገበ ነው፤ ሆኖም የመጨረሻው የማንነት ማረጋገጫ በፎረንሲክ ምርመራ እስኪረጋገጥ ድረስ አይታወቅም።

ይህንን የከፋ አደጋ ተከትሎ በስፍራው የደረሱት የማዳን ቡድኖች ባዩት አስደንጋጭ ሁኔታ ልባቸው እንደተሰበረ ገልጸዋል።

የሳውዲ ሲቪል ዲፌንስ እና የቀይ ጨረቃ ባለሥልጣናት የሬሳ ማንሳት ሥራውን አከናውነው መንገዱ ለብዙ ሰዓታት ተዘግቶ ነበር።

ለተሰዉት በሙሉ ከልብ የመነጨ ሀዘናችንን እየገለጽን፣ አላህ (ሱ.ወ) በራሕመቱ እንዲቀበላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውንም መፅናናትን እንዲሰጣቸው ይለግሳቸው።

17/11/2025

ከሸረሪት ድር በላይ በቀላሉ ለሚበተነው የውሃብያ አስተምህሮት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሸሪዓዊ ማስረጃዎችን በማጣቀስ አንድ በአንድ አየር ላይ ሲያስቀራቸው በአንፃሩ የመንጋው ተከታዮች ከግለሰብ እስከ ማህበራት የርሱን ስብዕና በማነወርና ማጠልሸት ላይ ተጠምደዋል እስኪ ካዋጣችሁ ይቀጥሉበት ሁሉም ቅርብ ነው ትውልድ ያያል ይሰማል ይፈርዳል።

እኔ እምለው የምትምኑበትን ነገር በሌላ ሰው አንደበት ሲነገራችሁ ለምን ታፍራላችሁ 🤔🙄

Ambassador/Ustaz Hasen Taju ሐያት ይገባዎት 💚🍂
Nazim Endris Ebrahim

16/11/2025

የምስጋና መልዕክት

የባቡል ኸይር ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው በማለት በረምዚ ሪል እስቴት አማካኝነት በተደረገ ቻሌንጅ በህዝብ በተሰበሰበ ድምጽ አሸናፊ በመሆን በድጋሚ በረምዚ ሪል እስቴት የተሰጠንን የአንድ ሚሊዮን ቻሌንጅ በድል ተወጥተናል። ይህ የሆነው በሁላችሁም የማይተካ ርብርብና ትጋት ፤ እንቅልፍ ማጣት እንዲሁም ቁጭት ነውና ለሁላችሁንም በያላችሁበት ምስጋናዬ እንዲደርስልኝ እጠይቃለሁ። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ፤ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ በባቡል ኸይር አመራሮች እና ተጠቃሚ ቤተሰቦቻችን ስም ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ።

ወ/ሮ ሃናን ማህሙድ
የባቡል ኸይር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ

ባቡል ኸይር “የመልካምነት በር”
ኑ በቅንነት ወደ መልካምነት

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa