New Africa society

New Africa society

Share

በ ህግ ለፍትህ

20/08/2024

የሞት ቅጣት የሚወሰንበት እና የሚፈፀምበት ሁኔታዎች
=========================
1. መግቢያ

በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውስጥ ወንጀልን ከመከላከል እና የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ መሰረት ሰዎች በእውቀት ማነስ ምክንያት ጥፋት እንዳይፈጽሙ እና በወንጀል እንዳይጠየቁ ለማድረግ ወንጀል የሆኑና የተከለከሉ ተግባራት እንዲያውቁት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ ሰዎች ካላቸው ያላግባብ የመጠቀም እና ሌላውን የመጉዳት ሀሳብ ወይም ቸልተኛነት በሚመነጭ ተግባር ክልከላውን ተላልፈው ወይም በህግ የተጣሉባቸውን ግዴታዎች ባለመወጣት የወንጀል ህጉን ጥሰው ሲገኙ እርምት መውሰድ ዋነኛው አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

በወንጀል ህጋችን ላይ በወንጀል የሚያስቀጡ ህገወጥ ተግባራት ተዘርዝረዋል ለእነኚህም የወንጀል ድርጊቶች እንደየወንጀሉ ባህሪ እና ክብደት በተበዳይ፣ በህዝብ እና በመንግስት ላይ ሊያስከትል ከሚችለው የጉዳት መጠን አንጻር የተለያዩ የቅጣት አይነቶችን አስቀምጧል፡፡ በ1996 ዓ.ም የወጣዉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 90 እና ተከታዮቹ መሰረት በሀገራችን ህግ ስርዓት እውቅና ያገኙት መደበኛ የቅጣት አይነቶች የሞት፣ የእስራት፣ የመቀጮ እና የግዴታ ስራ ናቸው፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል ባይደነገጉም በህጉ ጠቅላላ ክፍል የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው በተገኙ ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆኑ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ማስጠንቀቅያ፣ ወቀሳ፣ ተግሳጽ፣ ተበዳይን ይቅርታ ማስጠየቅ እና የወንጀል አድራጊውን የተለያዩ መብቶች መሻር የሚያካትቱ ተጨማሪ ቅጣቶች የወንጀል ህግ አንቀጽ 121 እና ተከታዮቹ ተደንግገዋል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ከመደበኛ የቅጣት አነቶች ዉስጥ ስለሞት ቅጣት ምንነትና አፈጻጸም የምንመለከት ይሆናል፡፡

2. የቅጣት ምንነት፣ አስፈላጊነት/አላማ እና አይነት

ቅጣት ወንጀል መፈጸማቸው በፍርድ ቤት በተሰየመው ችሎት ፊት ቀርበው በተሰሙ ምስክሮች ወይም በቀረቡ ማናቸውም ማስረጃዎች በተረጋገጠ እና ፍርድ ቤቱ የጥፋተኛነት ውሳኔ በሰጠባቸው ሰዎች ላይ በዳኞች የሚተላለፍ የእርምት እርምጃ ነው፡፡ ቅጣት የተከለከሉ ድርጊቶችን በማድረግ ወይም ማድረግ ግዴታ የሆኑትን ባለማድረግ የወንጀል ህጉን የተላለፉ ሰዎች ላይ የሚጣል የእርምት እርምጃ ሲሆን አላማውም ወንጀል አድራጊዎችን ማስተማር እና ድጋሚ ሌላ ወንጀል እዳይፈጽሙ ለማድረግ እና ሌሎችም በሌሎች ላይ የተወሰነውን ቅጣት በማየት ወንጀልን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ለማድረግ ነው፡፡

ቅጣት ወንጀል አድራጊዎችን በማስተማር መልካም ዜጋ እንዲሆኑ እና ካለፈው ጥፋታቸው ትምህርት ወስደው ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ወንጀልን የሚጠየፉ እና ለሌሎችም ተምሳሌት የሚሆኑ ዜጎች እንዲሆኑ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ሰዎች በህግ የበላይነት ከመገዛት ይልቅ አሸናፊነታቸውን በመጠቀም በሌሎች ላይ ተጽዕኖዎችን ማድረሳቸው እና ጉልበት የሌላቸውን ሰዎች መብቶች በመጣስ በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዳያብብ እና ከስጋት ያልጸዳ ኑሮን እንዲኖሩ መንገድ ይከፍታል፡፡

3. ከወንጀል ህጋችን አንቀጽ 1 እንደምንረዳዉ ቅጣት የሚከተሉት አላማዎች አሉት፡፡ እነዚህም ፡-
1. ማስተማር (deterrence)
2. መቅጣት (retribution)
3. ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል (prevention, incapacitation, disabling) እና
4. ማረም (reformative, rehabilitation) ናቸዉ፡፡
እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩት አላማዎች አካሄዳቸው ወይም እሳቤያቸው ይለያይ እንጂ የመጨረሻ ግባቸው ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ነው፡፡

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የቅጣት አይነቶች የሞት፣ የእስራት፣ የመቀጮ እና የግዴታ ስራ እንዲሁም ማስጠንቀቅያ፣ ተግሳጽ፣ ተበዳይን ይቅርታ ማስጠየቅ እና የወንጀል አድራጊውን የተለያዩ መብቶች መሻር ሊሆን ይችላሉ፡፡
የሞት ቅጣት ታሪካዊ ዳራ

የሞት ቅጣት ሕጎች ቀደምት ታሪክ የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን እሱም በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኮድ (የሃሙራቢ ህግ/ኮድ) ውስጥ ይገኛሉ። በዓለም ላይ የመጀመሪያው የተመዘገበው ግድያ (የሞት ቅጣት) የተፈፀመው በጥንቷ ግብፅ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2627 ዓመተ አለም ነዉ፡፡ የሞት ቅጣት በመካከለኛው ዘመን በስፋት ይሠራበት የነበረና ብዙ ጊዜ በመንግስት ወይም በቤተክርስቲያን ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን ለመቅጣት የሚያገለግል ነዉ፡፡

በታሪክ ውስጥ የሞት ቅጣት በተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ውሏል። እንደ ግድያ፣ የሀገር ክህደት እና ስለላ የመሳሰሉ ወንጀሎችን ለመቅጣት ጥቅም ላይ ውሏል። በተጨማሪም እንደ መናፍቅ ወይም ክህደት (heresy or apostasy) ላሉ ሀይማኖታዊ ጥፋቶችም እንደ የቅጣት አይነት አገልግሏል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ የሞት ቅጣት እንደ ስርቆት ያሉ ቀላል ወንጀሎችን ለመቅጣት ጥቅም ላይ ውሏል።

በ18ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮፓ ዉስጥ የሞት ቅጣትን ለማስወገድ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን በዚሁ መሰረት ብዙ አገሮች ይህን አንቅስቃሴ አስቀጥለዋል፡፡ ለምሳሌ በዩናይትድ ስቴትስ እ.ኤ.አ በ1786 ፔንስልቬንያ የሞት ቅጣትን የሻረች የመጀመሪያው ግዛት ናት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሌሎች በርካታ ግዛቶች ውስጥ የሞት ቅጣት ተከልክሏል፡፡

4. ስለሞት ቅጣት የሚነሱ ክርክሮች እና ቅጣቱ የሚጣልበት ወንጀል አይነት

የሞት ቅጣት በተለየ ሁኔታ ከባድ ተብለው የተደነገጉ ወንጀሎችን ፈጽመዉ በተገኙ ወንጀለኞች ላይ ሕይዎታቸዉን አንዲያጡ የሚፈረድ ፍርድ ነዉ፡፡ የሞት ቅጣት ክቡር የሆነዉን የሰውን ህይወት የሚያሳጣ የቅጣት አይነት በመሆኑ ሁለት ተቃራኒ አቋሞች ያሉትና በብዙ መንግስታት እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሀገራት አከራካሪ ጉዳይ ነዉ።

ከሞት ቅጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳዉ የመጀመርያዉ ሀሳብ በብዛት ከሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች አንጻር የሚነሳ ሲሆን እሱም የመኖር መብት የሠው ልጆች በተፈጥሮ የተጎናጸፉት መብት በመሆኑ ምንም እንኳን ሰዎች ከባድ ወንጀል ቢፈጽሙ ይህንን መብታቸውን በተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር በሌላ ሰው እጅ ሊያጡ የማይገባ ነው የሚል መከራከርያ ነው፡፡ በተቃራኒዉ የሚነሳዉ ሁለተኛዉ ሀሳብ ደግሞ የመኖር መብት የሰው ልጅ ሰው ሆኖ በመፈጠሩ ብቻ የተገኘ መብት ቢሆንም ከባባድ ለሆኑ ወንጀሎች የሞት ቅጣትን መጣል ሌሎችን ለማስተማር እና ወንጀል እንዳይፈጸም ለመከላከል በልዩ ሁኔታ የመኖር መብት ላይ ገደብ ሊጣልበት ይገባል የሚል ነዉ፡፡

አብዛኛዉ አገራት ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሞት ቅጣት አንዳይፈጸም እያገዱ ወይም ከህጋቸዉ ዉስጥ እያወጡ በመሆኑ ቅጣቱ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ እንደ ዎረልድ አትላስ (World Atlas) ሪፖርት አሁን ላይ በሞት ቅጣት የሚቀጡ አገሮች ከዓለም አገሮች አንድ ሦስተኛ ያህሉ ብቻ ሲሆኑ አገራችንን ጨምሮ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ቻይና፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ (የተወሰኑ ግዛቶች ከህጋቸዉ ዉስጥ ሰርዘዉታል)፣ አፍጋኒስታን፣ የመን፣ ሱዳንን እና ሌሎችም ይገኙበታል። በአንጻሩ ደግሞ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ሁሉም የአውሮፓ ምክር ቤት አባላት የሞት ቅጣትን ከህጋቸዉ ዉስጥ ሰርዘዋል፡፡

አብዛኛዎቹ የሞት ቅጣትን በሚፈጽሙ አገሮች ውስጥ ቅጣቱ ለከባድ ወንጀሎች ላይ የሚጣል ሲሆን ከእነዚህ ወንጀሎች መካከል ግድያ፣ ሽብርተኝነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ አፈና እና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገወጥ ዕፅ ዝዉዉር እና ሙስና ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ የአረብ አገሮች እንደ ሴተኛ አዳሪነት፣ ግብረ ሰዶም እና ዝሙት ያሉ አንዳንድ የወሲብ ወንጀሎች በሞት ቅጣት ያስቀጣሉ።

በሞት ቅጣት ላይ ያለዉ ልዩነት አንዳለ ሆኖ በጊዜ ሂደት አለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚከተሉትን ጨምሮ የሞት ቅጣትን የሚከለክሉ በርካታ አለማቀፍ ሰምምነቶችን አዉትቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
• አለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት ላይ የሞት ቅጣትን ለማስወገድ ታልሞ የወጣዉ ሁለተኛው አማራጭ ፕሮቶኮል (The Second Optional Protocol to the International Covenant on Civil and Political Rights)፡፡
• የሞት ቅጣትን ስለማስወገድ ለአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት ፕሮቶኮል ቁጥር 6 እና ለአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት ፕሮቶኮል ቁጥር 13 በሁሉም ሁኔታዎች የሞት ቅጣትን ለመሰረዝ የወጡ (Protocol No. 6 to the European Convention on Human Rights, and Protocol No. 13 to the European Convention on Human Rights)።
• የሞት ቅጣትን ለማስወገድ የአሜሪካ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት ፕሮቶኮል (The Protocol to the American Convention on Human Rights to Abolish the Death Penalty)።

5. የሞት ቅጣት አፈጻጸም አይነቶች

የሞት ቅጣት የአፈፃፀም ዘዴዉ በብዛት በህግ የሚወሰን ይሆናል፡፡ የሚተገበረዉ የሞት ቅጣት በወንጀል አድራጊው ላይ አላስፈላጊ ስቃይና እንግልት ማምጣት የለበትም። አሁን ላይ በተለያዩ አገራት ከሚተገበሩት የአፈፃፀም ዓይነቶች መካከል የኤሌክትሪክ ወንበር ወይም ኤሌክትሮይክ፣ ገዳይ መርፌዎች፣ መታነቅ፣ አንገት መቁረጥ እና በተኩስ መገደል ይገኙበታል።

6. የሞት ቅጣት በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን በወንጀል ህጓ ዉስጥ እዉቅና በመስጠት ተግባራዊ እያደረገች ያለች ሀገር ናት፡፡ በወንጀል ህጋችን ዉስጥ የሞት ቅጣት በተለዬ ሁኔታ ከባድ ተብለው ለሚገመቱ ወንጀሎች የሚደነገግ የቅጣት ዓይነት ነው፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 117(1) መሰረት የሞት ቅጣት በአጥፊዎች/ጥፋተኛ በተባሉ ሰዎች ላይ የሚፈረደው የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው፡፡ እነኚህም፡-
1. የወንጀል ድርጊቱ በሞት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ወንጀሉን በሚያቋቋመው የህጉ ልዩ ክፍል በግልጽ ተደንግጎ ሲገኝ፣
2. ወንጀሉ ፍፃሜ ያገኘ ማለትም በሙከራ ደረጃ ላይ ያልተገታ ሲሆን፣
3. ቅጣቱን የሚያቀልለት ምንም አይነት ማቅለያ ምክንያት የሌለ እንደሆነ፣
4. የተፈፀመው ወንጀል እጅግ በጣም ከባድና ወንጀለኛው በተለይ አደገኛ ሲሆን እና
5. አጥፊው የቅጣት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ እድሜው 18 የሞላዉ ከሆነ ነዉ፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ የተላለፈዉ የሞት ቅጣት ለመጽናትና ተፈጻሚ ለመሆን የአገሪቱን ርዕሰብሔር ፈቃድ አስፈላጊ ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ ምንም እንኳን በህግ የሞት ቅጣት ያለ ቢሆንም በርዕሰብሄሩ መፅናት የሚገባው በመሆኑ እና በሌሌች እንደ ይቅርታና ምህረት ምክንያቶች በአገራችን ተፈፃሚነቱ ዝቅተኛ ነዉ፡፡

በሌላ በኩል አፈጻጸሙን ስንመለከት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች ፍርዱ በህዝብ ፊት በአደባባይ፣ በስቅላት ወይም በማንኛውም ኢ-ሰብዓዊ መንገድ ሊፈጸምባቸው እንደማይገባ በአንቀጽ 117(3) ስር በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ቅጣቱ የሚፈጸመዉ የሚመለከተዉ ማረሚያ ቤት አስተዳደር የበላይ ሃላፊ በሚወስነዉ የአፈጻጸም ዘዴ/ሁኔታ በማረሚ ቤቱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ይሆናል፡፡ የሞት ቅጣቱ ከመፈጸሙ በፊት በተቀጪዉ ላይ ምንም አይነት የበቀል እረምጃ፣ የአካል ጉዳትና ስቃይ ማድረስ በፍጹም የተከለከለ ነዉ፡፡

7. የሞት ቅጣት ታግዶ የሚቆይበት ሁኔታ (አንቀጽ 119)

ነብሰ ጡር ሴቶች እና ኢ-ሀላፊ እና ከፊል የወንጀል ሀላፊነት ላይ የሚገኙ እና የታመሙ ሰዎች ምንም እንኳን የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ቢሆንም ከዚሁ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው እስኪገኙ ድረስ የሞት ፍርዱ ሳይፈጸም ተንጠልጥሎ ይቆያል፡፡ ነብሰ ጡሯ ፍርደኛ በሰላም ከተገላገለች እና ህጻኑን ማሳደግ እንዳለባት ፍ/ቤቱ ሲያምን የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊለውጥላት ይችላል፡፡
ከዚህ ሌላ ይህ አይነቱ ቅጣት በምህረት ወይም በይቅርታ ሊለወጥ ወይም ቀሪ ሊሆን እንሚችል የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 120 (1 እና 2) ስር በግልጽ ይደነግጋል፡፡

8. የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰዉ ቅጣቱ እስኪፈጸም የሚቆይበት ሁኔታ

የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰዉ ቅጣቱ እስኪጸናና እስኪፈጸም ድረስ ጽኑ እስራት የተፈረደበት እስረኛ እስራቱን በሚፈጽምበት ሁኔታ የማረሚያ ቤት አስተዳደር አስፈላጊዉን የደህንነት ጥበቃ እያደረገለት ታስሮ የሚቆይ ይሆናል፡፡

Source:- Ministry of Justice

21/11/2021

It is time for African to fight Western as one

17/07/2021

በጠዋቱ አፍሪካ ሳጠግበዉ ስለተነጠቀችዉ ምርጡ ፖትሪስ ሉምባባ እናዉራለን

እንደ "Belgium" አፍሪካ ላይ የተጫወተ አንድም ሃገር የለም! የቤልጂየሙ ንጉስ "Leopold II" እ.ኤ.አ 1884 ላይ አውሮፓ አፍሪካን ለመቀራመት ስትወስን "Congo" የእርሱ እጣ ሆነች!

ተዝቆ በማያልቅ የተፈጥሮ ሃብቷ የምትታወቀው "Congo" ወርቅ፣ አልማዝ፣ የዝሆን ጥርስ፣ መዳብ፣ ዩራንየም፣ ኮልታን እና ኮባልት ምናምን የሚባሉ ሃብቶቿ እና መዓድኖቿ ለዘረፋ ተመቻቹ!

"Leopold II" አውሮፓውያኖችን እንዲህ አላቸው!

"....ያለኝን የግል ሃብት "Congo" የምትባል አንዲት የአፍሪካ ሃገር ውስጥ ማፍሰስ እፈልጋለሁ! እዛች ሃገር ውስጥ ያለውን ምስኪን፣ ደሃ እና አሳዛኝ ህዝብ የተሻለ ህይወት እንዲኖ ማድረግ እሻለሁ! ሃይማኖት የላቸውም! ስለዚህ ሚሽነሪዎችን ከዚህ ልኬ ክርስትናን እንዲቀበሉ አደርጋለሁ፣ አሰለጥናቸዋለሁ፣ ከአውሬነትም እታደጋቸዋለሁ! ስለዚህ እቺን ሃገር እንደ "personal Properly" (የግል ንብረቴ) አድርጌ ወስጃታለሁ!...." ብሎ ተረከበ!

በሃገሪቷ የሚገኙ የሃገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎችን ሰብስቦ "Congo" የግል ግዛቱ(ንብረቱ) እንደሆነች የሚደነግግ ስምምነት አስፈረማቸው! ሃገሪቷንም "Congo Free State" ብሎ ሰየማት!

በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ አረመኔ ንጉስ የህዝቡን እጅ እና እግር እየቆረጡ አስገድዶ ያሰራው ጀመር! የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብትም እያጋዘ ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደጉድ ነገደው!

ይህ ሰው "Congo"ን የግል ንብረቱ አድርጎ ሲሸምታት የህዝብ ቁጥሯ ወደ 20 ሚልዮን ይጠጋ ነበር! ጌታዬ! ብታምንም ባታምንም ከዚህ ውስጥ 10 ሚልዮን የሚሆነውን ህዝብ ቅርጥፍ አድርጎ ገድሏል!

"...እንዴት አልተወራለትም? እንዴት ሳላውቀው?" ካልከኝ ደግሞ፣ መልሱ! "...ሟቾቹ አውሮፓውያን፣ አይሁዳውያን ወይንም አሜሪካውያን ሳይሆኑ እንደ አውሬ የሚታዩት "አፍሪካውያን" ስለሆኑ ነው!

ይህ ንጉስ ወደ 200 የሚጠጉ ኮንጎዋዊያንን ወደ ሃገሩ ቤልጄየም በመውሰድ "የሰው ልጅ Zoo" ከፍቶ አፍሪካውያን እንደ እንስሳ እንዲጎበኙ ያደረገ ሰው ነው! አባዬ! ጥቁሮች በሽቦ የታጠረ "Zoo" ውስጥ ሆነው አውሮፓውያን እንደ ብርቅዬ እንስሳ እየጎበኟቸው ከውጪ ሙዝ ሲወረውሩላቸው ዝም ብለህ አስበው!

ከግዜያት በኃላ!

ይህ ንጉስ ሞተ! አፍሪካውያንም እ.ኤ.አ ከ 1950ዎቹ በኃላ ነፃነታቸውን ማግኘት ጀመሩ! ከፍተኛ ውስጣዊ ጫና እና የህዝብ ተቃውሞ የቤልጄየም መንግስት ላይ እየደረሰ ሲመጣ ተተኪው ንጉስ ኮንጎዋዊያን የራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች መመስረት እንዲችሉ እና ምርጫ እንዲያደርጉ ፈቀደች! ከምርጫው በኃላም ኮንጎ ነፃነቷን እንደምታገኝ ቃል ገባች!

በዚህ መሃል ኮንጎ ተዝቆ የማያልቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት፣ ህዝቦቿ የተሻለ ኑሮ እንደሚገባቸው የሚያስብ፣ አፍሪካን የሚወድ፣ ስለ አፍሪካ አንድነት የሚጨነቅ፣ የተሻለች አፍሪካን ማየት የሚያልም፣ የተማረ፣ የሰለጠነ፣ ስርዓት ያለው፣ ግርማ ሞገሱ የሚያምር፣ መልከ መልካም ጎልማሳ "Congolese National Movement (የኮንጎ ብሄራዊ ንቅናቄ)" የሚባል የፖለቲካ ፓርቲን መስርቶ ምርጫ ተወዳደረ! አብላጫ ድምፅ አግኝቶም አሸነፈ! እ.ኤ.አ 1960 ላይ የመጀመርያው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ የኮንጎ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነ!

ሰውየው "Patrice Lumumba" ይባላል! ከነፃነት በኃላ የኮንጎ የመጀመርያው ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ሲመረጥ ገና 34 ዓመቱ ነበር!

ከዛስ?

እ.ኤ.አ ሰኔ, 30,1960 ላይ ቀኝ ገዢዎቹ በተገኙበት መድረክ ይህንን ንግግር አደረገ!

"....የዛሬዋ ቀን በልባችሁ ፀንታ ትቆይ! ሃገራችን ነፃ ወጥታለች! ስለዚች ቀን ለልጆቻችሁ እና ለልጅ ልጆቻችሁ በኩራት ወደፊት ታወራላችሁ! ሃገራችን አሁን ላይ በገዛ በራሷ ልጆች እጅ ትገኛለች! ወንድሞቼ እና እህቶቼ! ከዚህ በኃላ አዲስ ትግል ይጠብቀናል! ይህ ትግላችን ሃገራችንን ወደ ሰላም፣ እድገት እና ታላቅነት መውሰድ ነው! በጋራ ሆነን ማህበራዊ ፍትህን እናሰፍራለን! እስከዛሬ ጥቁር በመሆናችን ተዋርደናል፣ ተሰድበናልን፣ ተንቀን ኖረናል! የገዛ መሬታችንን ተዘርፈናል! የሃገራችን ህግ ለነጮች ያደላ ነው! ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው እና በእምነታቸው ብቻ ታስረዋል፣ ተገድለዋል! ከተማዎቻችን በቅንጡ የነጮች ቤትና በጥቁሮች የዳስ መኖርያ ቤትተወሯል! ጥቁሮች በገዛ ሃገራቸው የተለያዩ ሬስቶራንቶች እና ሲኒማ ቤቶች እንዳይገቡ ተከልክለዋል። ይህንን ድል ያገኘነው በከባድ ትግል ነው። በግኝ ግዛት ወቅት በነበርንባቸው 80 ዓመታት የደረሰብን ቁስል አሁንም እንዳመረቀዘ ነው! አሁንም ያመናል! በቂ ምግብ ሳይሰጡን ጉልበታችን በዝብዘዋል! እንደ ሰው ልጅ እንኳ የምንለብሰውን አሳጥተውናል! ልጆቻችንን በቅጡ ማሳደግ እንኳን አልቻልንም!

ረጅም እድሜ ለነፃነት ላበቁን የነፃነት ታጋዮቻችን! ረጅም እድሜ ለነፃነት እና ለአፍሪካ አንድነት! ረጅም እድሜ ለነፃ እና ሉዓላዊት ሃገር ኮንጎ! ..."

ከምዕራቡ ዓለም የተቀዳ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምን ፍፁም የማይደግፈው እና "Positive neutralism" በሚባል መርህ የሚመራው "Lumumba" ከነጮቹ ተፅእኖ ነፃ የሆነች ኮንጎን ለመገንባህ "ሀ" ብሎ ጀመረ!

ነገር ግን ከገዛ የሃገሩ ህዝቦች እና የሃገሪቱ ጦር ከባድ ፈተና ገጠመው!

ዋናው ፈተና!

"Katanga" የሚባል የሃገሪቷ ክፍል ከፍተኛ የመዓድን ክምችት አለ! ዓለም አቀፍ መዓድን አውጪ ተቋማት ያሉትም እዚህ ነው! ምዕራባውያኑ ሃብት የሚያግዙት ከዚህኛው የሃገሪቱ ክፍል ነው! "Patrice Lumumba" ደግሞ ይህንን የሚያስቆም አይነት መሪ ሆነ!

ታክስ ሊጨምርባቸው ወይ ደግሞ ጭራሹኑ ሊያባርራቸው እንደሚችል የገመቱት ቤልጄየሞች እዚሁ የሃገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚገኙ አማፅያንን ረድተው የመገንጠል ጥያቄ እንዲያቀርቡ አደረጉ! በአሜሪካ እና ቤልጄየም የሚረዱት እነዚህ አማፅያን ሰውየውን አላስቀምጥ አሉት!

ወደ ስልጣን ከመጣ ወራት እንኳን ያላስቆጠረው "Lumumba" ፊቱን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) አዙሮ የቤልጄም ወታደሮች አማፅያኑን እየረዱ እንደሆነ ፣ የአማፅያኑን የመገንጠል እና ሃገር የመበታተን ፍላጎትም ቤልጄየም እየደገፈች እንደሆነ እና የቤልጄም ወታደሮች ከዚህ ክልል እንዲወጡ፣ በምትኩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሃይል ገብቶ ሃገሪቷን የማረጋጋት ስራ ይስራልኝ ብሎ ለመነ!

ጌታዬ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን ከምንም ሳይቆጥረው ዝምታን መረጠ!

ያኔ "Lumumba" ራሽያ ጋር ሄዶ በር አንኳኳ! በወቅቱም ራሽያ አፍሪካ ላይ ያላትን ተፅህኖ ማጠናከር አጥብቃ ትፈልግ ስለነበር ጥያቄውን ሳታቅማማ ተቀብላ "Lumumba"ን መርዳት ጀመረች!

አንደምታውቀው ወቅቱ አሜሪካ እና ራሽያ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ውስጥ የነበሩበት ግዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ራሽያ ፊቷን ወደ ኮንጎ ማዞሯ አሜሪካ እጅግ እንድትሰጋ አደረጋት!

አሜሪካ እና ቤልጄየም ለዘመናት ተባብረው ሲበዘብዟት እና እንደ ልባቸው ጠፍጥፈው የሰሯት ኮንጎ ከእጃቸው ልትወጣ እንደሆነ ገባቸው! የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለምን የሚያቀነቅኑ መንግስታት አፍሪካ ውስጥ መመስረት መጀመራቸው እና በራሽያ መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸው ያሳሰባት አሜሪካ "Patrice Lumumba" መወገድ እንዳለበት ወሰነች!ሰውየውን አሜሪካ፣ "CIA"፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ቤልጄየም፣ በሃገሪቷ ውስጥ ያሉ አማፅያን እና የገዛ ከስሩ ያፈነገጡ ባለስልጣናት ወጥረው ያዙት!

የሃገሪቱ መከላከያ ውስጥ ያሉ ጥቁሮች የእርከን እድገት በፍጥነት እንደሚያገኙ፣ ደሞዝ እንደሚጨመርላቸው፣ ከነጮቹ ሃብት ንብረት ተቀምቶ ለነሱ እንደሚሰጣቸው እና ሃገሪቱ በአንዴ እንደምትለወጥ ጠብቀው ነበርና እነርሱም ፊታቸውን ያዞሩበት ጀመር!

እንዴት ገደሉት?

አሜሪካ እና ቤልጄየም "Katanga" ያሉትን አማፅያን በጦር መሳርያ ረድተው ለራሳቸው እንዲመች አድርገው የሰሩትን መንግስት ስልጣን እንዲቆናጠጥ አደረጉ! "Mabutu Sese seko" የሚባል ቀውስ አምባገነንን ስልጣን ላይ አስቀመጡ! "Lumumba" ሃገሪቷን ሰባት ወር እንኳን በቅጡ ሳይመራ በቁጥጥር ስር አውለው አሰሩት! የገዛ ሚስቱ እና ልጁ እያዩ የሃገሪቱ ወታደሮቹ የፊጥኝ በገመድ አደባባይ ላይ ጠፍረው ፀጉሩን እየጎተቱ ወሰዱት! በመጨረሻም በቤልጄየም መንግስት ትዕዛዝ ብዙ ተስፋ ሰንቆ ወደ ስልጣን የመጣው "Lumumba" እንደ ወንጀለኛ ዛፍ ላይ ታስሮ እንዲረሸን ተደረገ!

አሳዛኝ ነገር!

"Lumumba"ን ከገደሉት በኃላ ሬሳው ላይ "ሰልፈሪክ አሲድ" በማፍሰስ ሰውነቱ እንዲበጣጠስ እና ፈፅሞ እንዳይገኝ አድርገዋል! በዚህ ግዜ አንድ ቤልጄማዊ ወታደር ሁለት ጥርሶቹን ነቅሎ ወደ ሃገሩ ቤልጄም ወስዷል!

አሁን ላይ!

የ "Lumumba" ግድያ ተፈፃሚ እንዲሆን የአሜሪካ መንግስት ሃላፊነት ሰጥቶት የነበረው የ "CIA" ኤጀንት "Larry Devlin" ቃል በቃል እንዲህ ይላል!

"....."Lumumba" ለኮንጎ ብቻ ሳይሆን ለዓለማችንም አደጋ ነበር! አደጋ እንዲሆን ያደረገው ራሽያን ወደ ኮንጎ እንድትገባ ማድረጉ እና የነርሱን ወዳጅነት መምረጡ ነው! ይህ ለኛ ትልቅ ስጋት ነበር! ቀስ በቀስ ራሽያ ኮንጎን ከኛ ቁጥጥር ውጪ ታደርግብን ነበር!..."

በነገራችን ላይ "CIA" የመረጠው ሰውየውን ማስወገጃ መንገድ መርዞ መግደል ነበር! በወቅቱ "CIA" ውስጥ ኬሚስት እና የ"poison Expert" የነበረ "Sidney Gottlieb" የሚባል ሰው የጥርስ ሳሙና ውስጥ መርዝ ቀምሞ በመክተት "Lumumba"ን መርዞ ለመግደል ወደ ኮንጎ አቅንቶ የነበረ ቢሆንም አልተሳካም! ጌታዬ! ካላመንከኝ "Sidney Gottlieb" ብለህ ብትፈልግ እውነታውን ትረዳለህ!

ይፋዊ (declassified) የ "CIA" ዶክመንቶችን ብትመለከት ደግሞ "Lumumba"ን አስገድሎ ስልጣን ላይ የወጣው "Mobutu Sese Seko" ከአሜሪካ የገንዘብ ስጦታ እና የጦር መሳርያ ድጋፍ እንደተደረገለት በግልፅ ያትታል!

በአንድ ወቅት "Malcolm X" እንዲህ ብሎ ነበር!

"...."Lumumba" አፍሪካ በታሪኳ አይታው የማታውቀው ድንቅ መሪ ነው! እርሱ ማንንም አይፈራም! ነጮቹ እጅግ በጣም ይፈሩት ስለነበር ነው ያስገደሉት! ሊገዙት እና ሊደልሉት ሞክረው አልቻሉም! ሊያስፈራሩት ሞክረው ሊፈራቸው አልቻለም!....."

እናም!....ብዙዎች አሁን ኮንጎ ያለችበት የላሸቀ ሁኔታ ካዩ በኃላ... "Lumumba's assassination was Congo's original sin" ብለው ይደመድማሉ!

13/11/2019

evil
አንድ ምስኪን አባት በቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ እንቁላሎችን ለመሸጥ ወደ መንገድ ዳር ይዘው ይዘልቃሉ
በዛም መንገድ ዳርቻ ላይ አንድት ወጣት ሴት መጥታ
አባባ እንቁላሉ ስንት ነው ብላ ትጠይቃቸዋለች ?
እሳቸውም አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው ልጄ ብለው ይመልሱላታል።
እሷም እንድህ ስትል ድጋሜ ጠየቀቻቸው
አባባ አምስቱን እንቁላል በ አስር (10)ብር ልውሰደው ?
እሳቸውም አይጎዳም ብለሽ ነው ልጄ በማለት ደከም ባለ ድምፅ መለሱላት ።
ከፈለጉ ይሽጡ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው አለች ጠንከር ባለ ድምፅ
እሳቸውም ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት
እስካሁን ምንም አልሸጥኩም ባያዋጣኝም እንደመጀመሪያ
ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ ፣ የፈለግሽውን ያህል በፈለግሽው ዋጋ ውሰጅ ሲሉ በደከመ ድምፅ" ተናገሩ"
ዘንቢሏን አውጥታ 5ቱን እንቁላል አስገባች ከበርካታ መቶ ብሮች መካከል አስር ብር አውጥታ ወረወረችላቸው
እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች
የሚያሳዝነው ግን በእንድህም እንዳለች የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል ~~~
ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው የሚፈልጉትን አዘዙ ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ፣ ተዝናኑ
እና ሒሳብ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል
እሷ ግን ከቦርሳዋ 1500 ብር አውጥታ ሰጠች መልሱን ለ ሬስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ እንደሆነ ነግራው ወጥተው ሄዱ።
አስቡት ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አድስ አይደለም
ለእንቁላል ሻጩ አባት ግን አስደንጋጭ እና በጣም ልብ ሰባሪ ነበር።
ከድሆች እና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማግኘት የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምድነው?
የእኛን እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን እንፈልጋለን ?
እንኳን ይህን ግብይት ይቅርና የእግዚአብሔር ቃል እኮ ምስኪኖችን ስትጎበኙ ያላችሁን በቀኝ እጃችሁ ስትሰጡ ግራ እጃችሁ አይየው ነው የሚለው
እግዚአብሔር የቃሉ ሰሚ ያድርገን የሰማነውን ደግሞ በልቦናችን ያሳድርልን አሜን ፫
አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት share አድርጉት

12/11/2019

Evol

አንድ ወጣት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱን መምህር በጓደኛው ሠርግ ላይ ያገኘዋል ፡፡
ለመምህሩ በአክብሮት እና በአድናቆት ሰላምታን አቀረበለት ፡፡
እንዲህም አለው እኔ የትላንቱ ተማሪዎት ነበርኩ አለው ለእውቀት አባቱ።
መምህሩ “ኦ እሺ እንግዲህ እባክዎን እራስዎን ያስተዋውቁን
አለው በፈገግታ ፡፡
ተማሪውም ያኔ የ3ኛ ክፍል ተማሪ በነርኩበት ጊዜ ፣ በክፍል ውስጥ የልጁን የእጅ ሰዓት የሰረቅኩት እኔው ነበርኩ አለ፡፡
ታሪኩንም በእንዲህ መልኩ ይተርክ ጀመር
በክፍል ውስጥ ካሉት ወንዶች መካከል አንዱ የሚያምር ሰዓት ነበረው ፣ ወድኩት በሰአቱ በመማረኬ ለመስረቅ ወሰንኩ ሰረኩትም ፡፡
ልጁም ሰው ሰዓቱን እንደተሰረቀበት ወደ እርሶ እየጮኸ መጣ ፡፡
ኪሳችንን ለመፈተሽ እንድንቆም ጠየቁን ፡፡
ነውሬም በተማሪዎች እና በመምህራን ፊት እንደሚታይ ተገነዘብኩ።
እኔም ሌባ ተብዬ ልጠራ ነው ፣ ማንነቴንም በባህሪዬ ለዘላለሙ ሊጠፋም ነው ስል የምይዘው የምጨብጠው አጣሁ ፡፡
እኛም ግድግዳ ይዘን እንድንቆም እና ዓይኖቻችንን ሁላችንም ሙሉ በሙሉ እንድንጨፍን ተደረግን ነበር ፡፡
እርሶም ከኪስ ኪስ ፍለጋን ተያያዙት ፣ እናም እጆት ኪሴ ውስጥ ሲገባ ሰዓቱን አገኙት ከኪሴ ውስጥ አውጥተው የመጨረሻውን ተማሪ እስኪ ፈትሹ ድረስ መፈተሹን ቀጠሉ ፡፡
በመጨረሻም ፍተሻዎን ከጨረሱ በኋላ ዓይኖቻችንን እንድን ከፍት እና ወንበሮቻችን ላይ እንድንቀመጥ ጠይቀው ነበር ፡፡
በተማሪዎቹ ፊት እንዳያጋልጡኝ ፈርቼ ተጨንቄም ነበር ፡፡
እርሶ ግን ሰአቱን ለክፍሉ ተማሪዎች አሳዩን እና ለልጁ ሰጡት እናም ሰዓቱን የሰረቀውን ሰው ስም በጭራሽ አላሳወቁም ፡፡
አንድም ቃል አልተነፈሱም ነበር እና ታሪኩን ማንም አላወቀም ፡፡
በትምህርት ቤት ባሳለፍኩት ዕድሜዬ ሁሉ ከአስተማሪዎቼም ሆነ ከተማሪዎች መካከል ማንም ሰዓቱን መስረቄን የጠየቀኝ የለም ።
ያን ቀን ክብሬን የማጣ አድርጌ አስቤ ነበር አለ ፡፡
መምህሩም እኔም “አይኖቼን ጨፍኜ ስለነበር የሁላችሁን ኪሶች ሁሉ የፈተሽኩት በዚያን ቀን ሰዓቱን የሰረቀው ልጅ ማን እንደሆነ አላወኩምትም ነበር” አለው ፡፡
ተምልከቱ እንግዲህ ወገኖቼ ትምህርት ጥበብ ይፈልጋል ፡፡
አስተማሪዎች ፣ ወላጆች እና መሪዎች ፣ እርምጃችን እና ስሜታዊ የሆኑ ውሳኔዎቻችን የሚያስከትሉትን ውጤቶች መረዳት መቻል አለብን።
ዛሬ ዛሬ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በእውቀት ልእልና ከፍ ብሎ መመረቅ ስጋት ሆናል ተስፈኛ ልጅን ልኮ በድን ሙት ገላን መቀበል እየተለመደ መጥቷል እየቆየ ሲሄድ ልጅን ወደ የኒቨርሲቲ መላክ ጦር ሜዳ እንደመላክ ተቆጥሮ ሙሾ ማውረድ ሳይ ጀመር ሁላችንም የድርሻንን እናድርግ።
ዘረኝነትን መስበክ እና በሀይማኖቶች መካከል ጥላቻን መስበክ እልቂት ሳያስከትልብን በትክክለኛው የሰውነት ልኬት ላይ እንቁም ያንግዜ አንዱ የአንዱን ነብስ ይታደጋል ።
ዛሬ የታደግናት ነብስ ለነገው ህይወታችን እርካታ እና ስኬት ነው
ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ የተረጋጉና የሰከኑ ነገሮችን ከማንኛውም ጊዜ በተለየ ዛሬ ላይ ከኛ ትፈልጋለች ።

22/04/2019

Kendezich aynetwa gar tekotren nw 100.... mnamn yetebalnw🤔

Photos 05/07/2017

don't trust anyone

11/09/2016

መልካም አዲስ ዓመት የ ፔጃችን ተከታዮች በ አሮጌው ዓመት ያየነው
ጥሩ ነገር :-
1, ቃና ቲቪ ብቻ ሲሆን
መጥፎ ነገር ግን :-
1, ቃና ቲቪ
2,የ ኢንትራንስ ፈተና መሰረቅ
3, መንግሥት ሕዝቦቹን መረሸን
4,አላስፈላጊ ብጥብጥ
5,የማይቆጠር ብዙ ነገር
አዲሱ ዓመት ከዚህ ሁሉ የ ፀዳ እንዲሆን እመኛለሁ !

Photos 14/08/2016

እውነት ሀሰት

Photos 08/07/2016

Messi : ronaldo pls help me am going to jail
ronaldo:ow mesi i have a match with grizman on sunday
messi:plz ronaldo
ronaldo:ok you must be going out of spain
mess:what
ronaldo:is their therir another choice ?
messi: you are right
ronaldo :good by my friend
messi: good luck for the match

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa