19/11/2025
ሸሪዓዊ ልባስ!
🖌 ኢልያስ አሕመድ
{لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ}
––––––––––––
(ዝርዝር ማስረጃዎችን ለመናድ ጥቅል አንቀፆችን በማቅረብ ፍልስፍናዊ መነሻዎችን ሸሪዓዊ ልባስ የማልበስ ስልት)
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
በሰለፎች ምልአተ ድምፅ የተኮነነው የጀህሚያው የተዕጢል መስመር ጠንሳሾችንና አቀንቃኞችን በቁርኣንና በሐዲሥ በተደጋጋሚ የፀደቁትን የፈጣሪ ዝርዝር መገለጫዎችን መልእክት ለመቆልመም ያበቃቸው እውነተኛ መነሻ ፍልስፍናዊ እንጂ ሸሪዓዊ አይደለም። (ዝርዝሩን በሌላ ጊዜ እንመለስበት ይሆናል።)
ሆኖም አብዛኛዎቹ ብዙሃኑን ለመሸንገል በየአጋጣሚው የሚያነሷቸው አንዳንድ ጥቅል ጥቅሶች እንዳሉ ይታወቃል! አንድ የቁርኣን አንቀፅን በምሳሌነት እንውሰድ፦
{ لَیۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَیۡءࣱۖ وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡبَصِیرُ }
[سُورَةُ الشُّورَىٰ: ١١]
⇛«እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው።» [አሽ-ሹራ 11]
ለምሳሌ፡‐ አላህ በዐርሹ በላይ ከፍ ያለ መሆኑን የሚያረጋግጡ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ማስረጃዎች ይዘት ላለመቀበላቸው፣ በአንፃሩም «አላህ ያለ ቦታ ነው ያለው!» ለተሰኘው መጤ መፈክራቸው ማስረጃ ሲጠየቁ ይህን የማይገናኝ አንቀፅ ይጠቅሳሉ!
የዚህን የመረጃ አቀራረብ ግድፈትና የአንቀፁን ትክክለኛ መልእክት የሚያጎሉ በአጭሩ እነሆ፡‐
1⃣ ይህንና መሰል ጥቅል የቁርኣን አንቀፆችን ያወረደው ጌታ ሌሎች ባህሪያቱ የተረጋገጡባቸውን ዝርዝር አንቀፆችንም ያወረደው ጌታ ራሱ ስለሆነ የሚጋጩ መልዕክቶች ሊኖሯቸው አይችልም! ስለዚህ በሁሉም ማመን ግዴታ ነው። ይህ የሚቻለው ደግሞ ሁሉንም ባህሪያቱን ከምንም ጋር ሳያመሳስሉ ለርሱ ማንነት በሚገባ መልኩ በማፅደቅ ብቻ ነው።
ይህን የሚያፀናው ደግሞ፡‐
2⃣ ሰለፎች ከዚህኛውና ከመሰል ጥቅል አንቀፆች ለአላህ በማስረጃ የተረጋገጡትን የትኞቹንም ባህሪያት መልእክት በልዩ ዘይቤ መቀየር እንደሚያስፈልግ አልተረዱም፤ ይህንም አልተገበሩም! የሁሉንም ማስረጃዎች መልእክቶች አጣጥመው እምነታቸውን እንዳራመዱ በሚያሳዩ ዘገባዎች መዛግብት ተሞልተዋል። እነርሱ ስለ ቁርኣን መልእክትና ለአላህ ስለሚገባው መገለጫ ከኋለኞች የተሻለ እንደሚገነዘቡ ግልፅ ነው።
3⃣ ስለባህሪያቱ ሁኔታ ሳያነሱ መልዕክታቸውን ለርሱ ብቻ በሚገባ መልኩ ማፅደቅ አላህ ውድቅ ያደረገው ማመሳሰል (تشبيه) ውስጥ እንደማይካተት የታወቀ ነው፤
📌 አል-ኢማም አት-ቲርሚዚይ (279 ዓ.ሂ) እንደሚያስተላልፉት ታላቁ የሙስሊሞች ኢማም (161 – 238 ዓ.ሂ) እንዲህ ብለዋል፦
إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ. فَإِذَا قَالَ: سَمْعٌ كَسَمْعٍ أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ فَهَذَا التَّشْبِيهُ، وَأَمَّا إِذَا قَالَ- كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى-: يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلاَ يَقُولُ: كَيْفَ، وَلاَ يَقُولُ: مِثْلُ سَمْعٍ وَلاَ كَسَمْعٍ، فَهَذَا لاَ يَكُونُ تَشْبِيهًا. وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ}
«ማመሳሰል የሚሆነው “እንዲህ ያልለ ወይም እንዲህ አይነት እጅ”፣ “እንዲህ ያልለ ወይም እንዲህ አይነት መስማት” ሲባል ነው፤…ነገር ግን አላህ እንደተናገረው “እጅ፣ መስማት፣ ማየት” ብሎ “እንዴት” ካላለ፣ “እንዲህ አይነት፣ እንዲያ ያለ መስማት..” ካላለ ማመሳሰል አይሆንም! አላህ ራሱ በመፅሃፉ እንዳለው ‘እንደርሱ ያልለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው’ »
[“ሱነኑ’ት-ቲርሚዚይ”፤ ኪታቡ’ዝ-ዘካህ፤ ከሐዲሥ ቁጥር (662) ቀጥሎ]
4⃣ የስያሜ መገጣጠም የሁኔታና የይዘትን መመሳሰል አያመላክትም! አላህ አዋቂ ከመሆኑ ጋር ከፊል ፍጡራንን አዋቂ ሲል ጠርቷል፤ ሰሚና ተመልካች ከመሆኑም ጋር ሌሎችን በእነዚህ ስያሜዎች ጠርቷል… ሌሎች ለራሱ ያፀደቃቸውን ባህሪያትም ለፍጡራኑ አፅድቋል፤ ምሳሌዎቹ እጅግ ብዙ ናቸው።
እነኚህ የተዕጢል ወገኖቻችን በግርድፉም ቢሆን የሚያፀድቋቸው ጥቂት ባህሪያት ፍጡራንም ሊጠሩባቸው የሚችሉ ናቸው።
ታዲያ አላህ አምሳያ የለውምና እነኚህንም መገለጫዎቹን እናስተባብል? ወይስ የፍጡርን ባህሪ ለማንነቱ በሚገባ ሁኔታ እንደምናፀድቀው የፈጣሪን ባህሪይ ለማንነቱ በሚገባ ልዩ መልኩ አረጋግጠን እንለፍ?
በተጨማሪም፦
5⃣ በአንቀፁ مِثۡل «አምሳያ» ውድቅ መደረጉ የባህሪያቱን ጥቅል ቋንቋዊ መልእክት መጋራትን አይከለክልም። አላህ አምሳያ (مِثۡل) እንደሌለው እንደጠቀሰው ሁሉ ከፍጡራን መካከልም አምሳያ (مِثۡل) እንደሌላቸው በቁርኣን የተወሱ ነገሮች አሉ፤ ሆኖም በስያሜና በጥቅል መልእክት የሚጋሯቸው ፍጡራን መኖራቸው አይካድም። ለምሳሌ፦
إِرَمَ ذَاتِ ٱلۡعِمَادِ ٱلَّتِي لَمۡ يُخۡلَقۡ مِثۡلُهَا فِي ٱلۡبِلَٰدِ
⇛«ባለ ረጃጅም ምሰሶዎች የሆነችዋ ‘ኢረም’፤ #አምሳያዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ የሆነችዋ» [አል-ፈጅር 8-9]
ሌሎች ባለ ምሰሶ አገሮች መኖራቸው ግልፅ ነው። አገራቱ በዝርዝር ይዘት መለያየታቸው የየትኛውንም አገር አገርነት አይሽርም፤ የአገራቱንም መገለጫዎች ለማስተባበል ምክንያት ሊሆን አይችልም!
ሌላ ምሳሌ፡‐
وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ يَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُونُوٓاْ أَمۡثَٰلَكُم [محمد: 38]
⇛ «(በእንቢታ) ብትዞሩ ከናንተ ሌላ ህዝቦችን ይተካል፤ ከዚያም #አምሳያዎቻችሁ አይሆኑም።» [ሙሐመድ 38]
ተኪዎቹም፣ ተተኪዎቹም እጅግ ብዙ ባህሪያትን በጥቅሉ የሚጋሩ ፍጡራን (ሰዎች) ከመሆናቸው ጋር ከፊሎቹ የሌሎቹ አምሳያዎች እንዳልሆኑ በግልፅ ተወስቷል። ሆኖም ይህ ሁሉም ሰዎች የመሆናቸውን እውነታና የሚጋሯቸውን ጥቅል መገለጫዎች ለማስተባበል ምክንያት አይሆንም።
ስለዚህ ውድቅ የተደረገው “አምሳያ” (مِثۡل) ወይም “መመሳሰል” ለሁሉም ማንነቱን የሚመጥን ባህሪን እንድናፀድቅ ያደርገናል እንጂ የአንደኛውን ባህሪይ መሰረታዊ መልእክት እንድናዛባ አያስገድደንም።
6⃣ የላይኛው አንቀፅ ሁለት ዋና ዋና መልእክቶችን አዝሏል፦
«እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» የሚለው የአንቀፁ የመጀመሪያ ክፍል ፈጣሪን ከፍጡር ጋር በምንም መልኩ ማመሳሰል ውድቅ መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን፤
«እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው» የሚለው መቋጫ ደግሞ መስማትና ማየትን ጨምሮ ለአላህ በመረጃ የተረጋገጡትን ስሞችና ባህሪያት ተቀብሎ ማፅደቅ የግድ መሆኑን ይጠቁማል።
📌 አቡ መንሱር አል‐አስበሃኒይ (በ418 ዓ.ሂ ያለፉ) የአንቀፁን ትክክለኛውን መልእክት ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡‐
فـ{لَیۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَیۡءࣱۖ} يَنْفِي كلَّ تَشْبِيه وتمثيل، {وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡبَصِیرُ} يَنْفِي كلَّ تَعْطِيل وَتَأْويل، فَهَذَا مَذْهَب أهل السّنة وَالْجَمَاعَة والأثر
«{እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም፤} = ሁሉንም የማመሳሰል ደረጃ (ተሽቢህ እና ተምሢል) ውድቅ ያደርጋል። {እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው} = ሁሉንም የባህሪውን መልእክት ያለመቀበልና የመቀየር ስልትን (ተዕጢልና ተእዊል) ውድቅ ያደርጋል! ይህ የሱንና እና የጀማዓህ እንዲሁም የአሠር (የትክክለኛ ትውፊት) ተከታዮች መንገድ ነው።»
[“አል‐ሑጅ‐ጃህ ፊ በያኒል‐መሐጅጀህ” (1/260)]
ስለሆነም የአንቀፁ መረጃነቱ ለኛ እንጂ ለነርሱ አይደለም! የዚህን አንቀፅ መልእክት ራሱ በትክክል ተግባራዊ አድርገው ቢሆን ወደ እውነተኛው ጎዳና በተመሩ ነበር! ይህን የሚያብራራው ደግሞ የሚቀጥለው ነጥብ ነው፦
7⃣ አንድ ነገር የሚወደሰው በመገለጫዎቹ ምጥቀት እንጂ በባህሪ-አልባነቱ እንዳልሆነ ግልፅ ነው! «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» ማለቱ ውዳሴ በመሆኑ የመለያ ባህሪያቱን ብዛት እንጂ ተቃራኒውን ሊያመላክት አይችልም! ምክንያቱም ቃሉ የሚያሳየው ባህሪያት እንደሌሉት ቢሆን ኖሮ ባዶነትን የሚጠቁም ይሆን ነበር፤ ባዶነት ደግሞ እንደስያሜው ባዶነትን እንጂ ምሉዕነትን የሚያስጨብጥ አይደለም።
8⃣ እንደነሱ አባባል አላህ እጅግ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ስልቶች ራሱን የገለፀባቸውን ጉልህ መልዕክቶች መቀበል እንደሌለብን የሚያመላክተን እንዲህ በደፈናው አምሳያ እንደሌለው በመንገር ብቻ ከሆነ ንግግሩ በብዙኃኑ ሙስሊሞች የማይፈታ የቅኔ ቋጠሮ ነው ማለት ነው!! ቃሉ ከእንዲህ ያለ መድበስበስ ፍፁም ለጠራውና ለላቀው ጌታችን ምስጋናና ውዳሴ የተገባ ነው!
ለመሆኑ! የላይኛውን ጥቅል አንቀፅ እንደ መረጃ አጣቅሶ አላህ ራሱን በተደጋጋሚ የገለፀበትን እዝነት፣ ቁጣ፣ መውደድ፣ መጥላት፣ መናገር፣ በዐርሹ ላይ መሆን፣ ፊት፣ እጅ.. እና ሌሎች በጣም ብዙ መገለጫዎችን በአንድ ስንዝር መደምሰስ እኮ አላህ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ለኛ እንደፈጠረልን የተናገረበትን ጥቅል አንቀፅ (አል‐በቀራህ 29) ተመርኩዞ እንደ ስርቆት፣ ዘረፋ፣ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥ፣ የአሳማ ስጋን መብላት.. ያሉ ግልፅ ሸሪዓዊ ክልከላዎችን ከማስተባበል የከፋ ነው። ምክንያቱም አላህ ስለራሱ የገለፀባቸው አንቀፆች ስለ ሐላልና ሐራም ህግጋት ከገለፀባቸው ይበልጥ የጐሉና የበዙ ናቸውና!
……………………
በጥቅሉ በተለያዩ ቁርጠኛ ማስረጃዎች የተረጋገጡትን የአላህን መገለጫዎች ቀጥተኛ መልእክት ለመቆልመም አላህ አምሳያ እንደሌለው የሚያስገነዝቡ ጥቅል ማስረጃዎችን ማቅረብ ግልፁን ትቶ አሻሚን የማፈላለግ ውጤት ነው! ይህ ደግሞ ልባቸው በጥመት በሽታ የተወረሰ ሰዎች ምልክት ነው። በተቃራኒው የእውቀትና የፅኑ እምነት ባለቤቶች ምልክት ከጌታቸው ዘንድ ለሚመጣ ማንኛውም ማስረጃ እጅ መስጠታቸው ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۡهُ ءَايَٰتٞ مُّحۡكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلۡكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٞۖ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمۡ زَيۡغٞ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنۡهُ ٱبۡتِغَآءَ ٱلۡفِتۡنَةِ وَٱبۡتِغَآءَ تَأۡوِيلِهِۦۖ وَمَا يَعۡلَمُ تَأۡوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُۗ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِي ٱلۡعِلۡمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلّٞ مِّنۡ عِندِ رَبِّنَاۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ [آل عمران: 7]
⇛ «እርሱ ባንተ ላይ መፅሐፉን ያወረደው ነው፤ ከርሱ ፍፁም የሆኑ (ግልፅ) አንቀፆች አሉ፤ እነሱም የመፅሐፉ ‘እናት’ (መሠረትና ዋነኛ መገለጫ) ናቸው፤ ሌሎች (ደግሞ) ”ሙተሻቢህ” (በአንፃሩ አሻሚ ገፅታ ያላቸው) ናቸው፤ እነዚያ በልባቸው ጥመት ያልለ ፈተናን በመፈለግና “ተእዊሉን”( ) በመፈለግ የተመሳሰለውን (አሻሚውን) ይከታተላሉ፤ "ተእዊሉን" ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም፤ በእውቀት ውስጥ የሰረፁትም “ ፤ ” ይላሉ..» [ኣሊ ዒምራን 7]
ተወዳጁ መልእክተኛ (ﷺ) ይህንን አንቀፅ አንብበው እንዲህ ብለዋል፦
إِذَا رَأَيْتُمُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ، فَأُوْلَائِكَ الَّذِينَ سَمَّى اللهُ؛ فَاحْذَرُوهُمْ
⇛«አነዚያ ከርሱ (ከቁርኣን) የተመሳሰለውን (አሻሚ ሆኖ ያገኙትን) የሚከታተሉትን ካያችሁ አላህ (በአንቀፁ) የጠቀሰው እነሱኑ ነውና ተጠንቀቋቸው!»
[አል-ቡኻሪይ (4547)፣ ሙስሊም (2665) ላይ ከእናታችን ዓኢሻህ እንደተላለፈው።]
አላህ ቀናውን መንገድ ይምራን!
©: በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1391785995651967&id=100044617380985&mibextid=Nif5oz
ሸሪዓዊ ልባስ!
{لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ}
––––––––––––
(ዝርዝር ማስረጃዎችን ለመናድ ጥቅል አንቀፆችን በማቅረብ ፍልስፍናዊ መነሻዎችን ሸሪዓዊ ልባስ የማልበስ ስልት)
🖌 ኢልያስ አሕመድ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
በሰለፎች ምልአተ ድምፅ የተኮነነው የጀህሚያው የተዕጢል መስመር ጠንሳሾችንና አቀንቃኞችን በቁርኣንና በሐዲሥ በተደጋጋሚ የፀደቁትን የፈጣሪ ዝርዝር መገለጫዎችን መልእክት ለመቆልመም ያበቃቸው እውነተኛ መነሻ ፍልስፍናዊ እንጂ ሸሪዓዊ አይደለም። (ዝርዝሩን በሌላ ጊዜ እንመለስበት ይሆናል።)
ሆኖም አብዛኛዎቹ ብዙሃኑን ለመሸንገል በየአጋጣሚው የሚያነሷቸው አንዳንድ ጥቅል ጥቅሶች እንዳሉ ይታወቃል! አንድ የቁርኣን አንቀፅን በምሳሌነት እንውሰድ፦
{ لَیۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَیۡءࣱۖ وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡبَصِیرُ }
[سُورَةُ الشُّورَىٰ: ١١]
⇛«እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው።» [አሽ-ሹራ 11]
ለምሳሌ፡‐ አላህ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ መሆኑንና ሌሎች መገለጫዎቹን የሚያረጋግጡ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ማስረጃዎች ይዘት ላለመቀበላቸው፣ በአንፃሩም «አላህ ያለ ቦታ ነው ያለው!» ለተሰኘው መጤ መፈክራቸው ማስረጃ ሲጠየቁ ይህን የማይገናኝ አንቀፅ ይጠቅሳሉ! አላህ እጅ እንዳለው የሚያረጋግጡ ግልፅ ማስረጃዎችን ላለመቀበል የሚያቀርቡትም ማመካኛ ይህን አንቀፅ ነው። እንደመቆጣት፣ መደሰት፣ መውደድ፣ መጥላት… ያሉ ዝርዝር መገለጫዎችን መልእክት ለመቆልመም ዘወትር የሚገቡበት መሸሸጊያም ይኸው ጥቅል አንቀፅ ነው!
የዚህን የመረጃ አቀራረብ ግድፈትና የአንቀፁን ትክክለኛ መልእክት የሚያጎሉ በአጭሩ እነሆ፡‐
1⃣ ይህንና መሰል ጥቅል የቁርኣን አንቀፆችን ያወረደው ጌታ ሌሎች ባህሪያቱ የተረጋገጡባቸውን ዝርዝር አንቀፆችንም ያወረደው ጌታ ራሱ ስለሆነ የሚጋጩ መልዕክቶች ሊኖሯቸው አይችልም! ስለዚህ በሁሉም ማመን ግዴታ ነው። ይህም አላህ እንደገለፀው የአዋቂዎች መንገድ ነው፡‐
{ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِي ٱلۡعِلۡمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلّٞ مِّنۡ عِندِ رَبِّنَاۗ }
«በእውቀት ውስጥ የሰረፁትም “ ፤ ” ይላሉ..» [ኣሊ ዒምራን 7]
ይህ ተግባራዊ የሚደረገው ደግሞ ሁሉንም ባህሪያቱን ከምንም ጋር ሳያመሳስሉ ለርሱ ማንነት በሚገባ መልኩ በማፅደቅ ብቻ ነው።
ይህን የሚያፀናው ደግሞ፡‐
2⃣ ሰለፎች ከዚህኛውና ከመሰል ጥቅል አንቀፆች ለአላህ በማስረጃ የተረጋገጡትን የትኞቹንም ባህሪያት መልእክት በልዩ ዘይቤ መቀየር እንደሚያስፈልግ አልተረዱም፤ ይህንም አልተገበሩም! የሁሉንም ማስረጃዎች መልእክቶች አጣጥመው እምነታቸውን እንዳራመዱ በሚያሳዩ ዘገባዎች መዛግብት ተሞልተዋል። እነርሱ ስለ ቁርኣን መልእክትና ለአላህ ስለሚገባው መገለጫ ከኋለኞች የተሻለ እንደሚገነዘቡ ግልፅ ነው።
3⃣ ስለባህሪያቱ ሁኔታ ሳያነሱ መልዕክታቸውን ለርሱ ብቻ በሚገባ መልኩ ማፅደቅ አላህ ውድቅ ያደረገው ማመሳሰል (تشبيه) ውስጥ እንደማይካተት የታወቀ ነው፤
📌 አል-ኢማም አት-ቲርሚዚይ (279 ዓ.ሂ) እንደሚያስተላልፉት ታላቁ የሙስሊሞች ኢማም (161 – 238 ዓ.ሂ) እንዲህ ብለዋል፦
إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ. فَإِذَا قَالَ: سَمْعٌ كَسَمْعٍ أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ فَهَذَا التَّشْبِيهُ، وَأَمَّا إِذَا قَالَ- كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى-: يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلاَ يَقُولُ: كَيْفَ، وَلاَ يَقُولُ: مِثْلُ سَمْعٍ وَلاَ كَسَمْعٍ، فَهَذَا لاَ يَكُونُ تَشْبِيهًا. وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ}
«ማመሳሰል የሚሆነው “እንዲህ ያልለ ወይም እንዲህ አይነት እጅ”፣ “እንዲህ ያልለ ወይም እንዲህ አይነት መስማት” ሲባል ነው፤…ነገር ግን አላህ እንደተናገረው “እጅ፣ መስማት፣ ማየት” ብሎ “እንዴት” ካላለ፣ “እንዲህ አይነት፣ እንዲያ ያለ መስማት..” ካላለ ማመሳሰል አይሆንም! አላህ ራሱ በመፅሃፉ እንዳለው ‘እንደርሱ ያልለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው’ »
[“ሱነኑ’ት-ቲርሚዚይ”፤ ኪታቡ’ዝ-ዘካህ፤ ከሐዲሥ ቁጥር (662) ቀጥሎ]
4⃣ የስያሜ መገጣጠም የሁኔታና የይዘትን መመሳሰል አያመላክትም! አላህ አዋቂ ከመሆኑ ጋር ከፊል ፍጡራንን አዋቂ ሲል ጠርቷል፤ ሰሚና ተመልካች ከመሆኑም ጋር ሌሎችን በእነዚህ ስያሜዎች ጠርቷል… ሌሎች ለራሱ ያፀደቃቸውን ባህሪያትም ለፍጡራኑ አፅድቋል፤ ምሳሌዎቹ እጅግ ብዙ ናቸው።
እነኚህ የተዕጢል ወገኖቻችን በግርድፉም ቢሆን የሚያፀድቋቸው ጥቂት ባህሪያት ፍጡራንም ሊጠሩባቸው የሚችሉ ናቸው።
ታዲያ አላህ አምሳያ የለውምና እነኚህንም መገለጫዎቹን እናስተባብል? ወይስ የፍጡርን ባህሪ ለማንነቱ በሚገባ ሁኔታ እንደምናፀድቀው የፈጣሪን ባህሪይ ለማንነቱ በሚገባ ልዩ መልኩ አረጋግጠን እንለፍ?
በተጨማሪም፦
5⃣ በአንቀፁ مِثۡل «አምሳያ» ውድቅ መደረጉ የባህሪያቱን ጥቅል ቋንቋዊ መልእክት መጋራትን አይከለክልም። አላህ አምሳያ (مِثۡل) እንደሌለው እንደጠቀሰው ሁሉ ከፍጡራን መካከልም አምሳያ (مِثۡل) እንደሌላቸው በቁርኣን የተወሱ ነገሮች አሉ፤ ሆኖም በስያሜና በጥቅል መልእክት የሚጋሯቸው ፍጡራን መኖራቸው አይካድም። ለምሳሌ፦
إِرَمَ ذَاتِ ٱلۡعِمَادِ ٱلَّتِي لَمۡ يُخۡلَقۡ مِثۡلُهَا فِي ٱلۡبِلَٰدِ
⇛«ባለ ረጃጅም ምሰሶዎች የሆነችዋ ‘ኢረም’፤ #አምሳያዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ የሆነችዋ» [አል-ፈጅር 8-9]
ሌሎች ባለ ምሰሶ አገሮች መኖራቸው ግልፅ ነው። አገራቱ በዝርዝር ይዘት መለያየታቸው የየትኛውንም አገር አገርነት አይሽርም፤ የአገራቱንም መገለጫዎች ለማስተባበል ምክንያት ሊሆን አይችልም!
ሌላ ምሳሌ፡‐
وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ يَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُونُوٓاْ أَمۡثَٰلَكُم [محمد: 38]
⇛ «(በእንቢታ) ብትዞሩ ከናንተ ሌላ ህዝቦችን ይተካል፤ ከዚያም #አምሳያዎቻችሁ አይሆኑም።» [ሙሐመድ 38]
ተኪዎቹም፣ ተተኪዎቹም እጅግ ብዙ ባህሪያትን በጥቅሉ የሚጋሩ ፍጡራን (ሰዎች) ከመሆናቸው ጋር ከፊሎቹ የሌሎቹ አምሳያዎች እንዳልሆኑ በግልፅ ተወስቷል። ሆኖም ይህ ሁሉም ሰዎች የመሆናቸውን እውነታና የሚጋሯቸውን ጥቅል መገለጫዎች ለማስተባበል ምክንያት አይሆንም።
ስለዚህ ውድቅ የተደረገው “አምሳያ” (مِثۡل) ወይም “መመሳሰል” ለሁሉም ማንነቱን የሚመጥን ባህሪን እንድናፀድቅ ያደርገናል እንጂ የአንደኛውን ባህሪይ መሰረታዊ መልእክት እንድናዛባ አያስገድደንም።
6⃣ የላይኛው አንቀፅ ሁለት ዋና ዋና መልእክቶችን አዝሏል፦
«እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» የሚለው የአንቀፁ የመጀመሪያ ክፍል ፈጣሪን ከፍጡር ጋር በምንም መልኩ ማመሳሰል ውድቅ መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን፤
«እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው» የሚለው መቋጫ ደግሞ መስማትና ማየትን ጨምሮ ለአላህ በመረጃ የተረጋገጡትን ስሞችና ባህሪያት ተቀብሎ ማፅደቅ የግድ መሆኑን ይጠቁማል።
📌 አቡ መንሱር አል‐አስበሃኒይ (በ418 ዓ.ሂ ያለፉ) የአንቀፁን ትክክለኛውን መልእክት ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡‐
فـ{لَیۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَیۡءࣱۖ} يَنْفِي كلَّ تَشْبِيه وتمثيل، {وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡبَصِیرُ} يَنْفِي كلَّ تَعْطِيل وَتَأْويل، فَهَذَا مَذْهَب أهل السّنة وَالْجَمَاعَة والأثر
«{እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም፤} = ሁሉንም የማመሳሰል ደረጃ (ተሽቢህ እና ተምሢል) ውድቅ ያደርጋል። {እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው} = ሁሉንም የባህሪውን መልእክት ያለመቀበልና የመቀየር ስልትን (ተዕጢልና ተእዊል) ውድቅ ያደርጋል! ይህ የሱንና እና የጀማዓህ እንዲሁም የአሠር (የትክክለኛ ትውፊት) ተከታዮች መንገድ ነው።»
[“አል‐ሑጅ‐ጃህ ፊ በያኒ'ል‐መሐጅ‐ጃህ” (1/260)]
ስለሆነም የአንቀፁ መረጃነቱ ለኛ እንጂ ለነርሱ አይደለም! የዚህን አንቀፅ መልእክት ራሱ በትክክል ተግባራዊ አድርገው ቢሆን ወደ እውነተኛው ጎዳና በተመሩ ነበር! ይህን የሚያብራራው ደግሞ የሚቀጥለው ነጥብ ነው፦
7⃣ አንድ ነገር የሚወደሰው በመገለጫዎቹ ምጥቀት እንጂ በባህሪ-አልባነቱ እንዳልሆነ ግልፅ ነው! «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» ማለቱ ውዳሴ በመሆኑ የመለያ ባህሪያቱን ብዛት እንጂ ተቃራኒውን ሊያመላክት አይችልም! ምክንያቱም ቃሉ የሚያሳየው ባህሪያት እንደሌሉት ቢሆን ኖሮ ባዶነትን የሚጠቁም ይሆን ነበር፤ ባዶነት ደግሞ እንደስያሜው ባዶነትን እንጂ ምሉዕነትን የሚያስጨብጥ አይደለም።
8⃣ እንደነሱ አባባል አላህ እጅግ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ስልቶች ራሱን የገለፀባቸውን ጉልህ መልዕክቶች መቀበል እንደሌለብን የሚያመላክተን እንዲህ በደፈናው አምሳያ እንደሌለው በመንገር ብቻ ከሆነ ንግግሩ በብዙኃኑ ሙስሊሞች የማይፈታ የቅኔ ቋጠሮ ነው ማለት ነው!! ቃሉ ከእንዲህ ያለ መድበስበስ ፍፁም ለጠራውና ለላቀው ጌታችን ምስጋናና ውዳሴ የተገባ ነው!
እናስተውል! የላይኛውን ጥቅል አንቀፅ እንደ መረጃ አጣቅሶ አላህ ራሱን በተደጋጋሚ የገለፀበትን እዝነት፣ ቁጣ፣ መውደድ፣ መጥላት፣ መናገር፣ በዐርሹ ላይ መሆን፣ ፊት፣ እጅ.. እና ሌሎች በጣም ብዙ መገለጫዎችን በአንድ ስንዝር መደምሰስ እኮ አላህ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ለኛ እንደፈጠረልን የተናገረበትን ጥቅል አንቀፅ (አል‐በቀራህ 29) ተመርኩዞ እንደ ስርቆት፣ ዘረፋ፣ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥ፣ የአሳማ ስጋን መብላት.. ያሉ ግልፅ ሸሪዓዊ ክልከላዎችን ከማስተባበል የከፋ ነው። ምክንያቱም አላህ ስለራሱ የገለፀባቸው አንቀፆች ስለ ሐላልና ሐራም ህግጋት ከገለፀባቸው ይበልጥ የጐሉና የበዙ ናቸውና!
……………………
በጥቅሉ በተለያዩ ቁርጠኛ ማስረጃዎች የተረጋገጡትን የአላህን መገለጫዎች ቀጥተኛ መልእክት ለመቆልመም አላህ አምሳያ እንደሌለው የሚያስገነዝቡ ጥቅል ማስረጃዎችን ማቅረብ ግልፁን ትቶ አሻሚን የማፈላለግ ውጤት ነው! ይህ ደግሞ ልባቸው በጥመት በሽታ የተወረሰ ሰዎች ምልክት ነው። በተቃራኒው የእውቀትና የፅኑ እምነት ባለቤቶች ምልክት ከጌታቸው ዘንድ ለሚመጣ ማንኛውም ማስረጃ እጅ መስጠታቸው ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۡهُ ءَايَٰتٞ مُّحۡكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلۡكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٞۖ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمۡ زَيۡغٞ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنۡهُ ٱبۡتِغَآءَ ٱلۡفِتۡنَةِ وَٱبۡتِغَآءَ تَأۡوِيلِهِۦۖ وَمَا يَعۡلَمُ تَأۡوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُۗ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِي ٱلۡعِلۡمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلّٞ مِّنۡ عِندِ رَبِّنَاۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ [آل عمران: 7]
⇛ «እርሱ ባንተ ላይ መፅሐፉን ያወረደው ነው፤ ከርሱ ፍፁም የሆኑ (ግልፅ) አንቀፆች አሉ፤ እነሱም የመፅሐፉ ‘እናት’ (መሠረትና ዋነኛ መገለጫ) ናቸው፤ ሌሎች (ደግሞ) ”ሙተሻቢህ” (በአንፃሩ አሻሚ ገፅታ ያላቸው) ናቸው፤ እነዚያ በልባቸው ጥመት ያልለ ፈተናን በመፈለግና “ተእዊሉን” (ገሀዳዊ ሁኔታውን) በመፈለግ የተመሳሰለውን (አሻሚውን) ይከታተላሉ፤ "ተእዊሉን" ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም፤ በእውቀት ውስጥ የሰረፁትም “ ፤ ” ይላሉ..» [ኣሊ ዒምራን 7]