Tourism Training Institute

Tourism Training Institute It is established as an autonomous legal executive entity of the Federal Government Ethiopia. The institute shall have the following
objectives:
1.

Providing skill-based and up to the standard
pre and on job training both in terms of
theory and practice to foster the
development of the tourism and hotel
sector.
2. Offering short, medium, and long-term
professional development training to
employees, leaders, and service providers in
the hotel and tourism sector.
3. Supporting the overall socio-economic
development endeavor of the coun

try
through the provision of training,
conducting research, consultancy, and
technology transfer as a center of
excellence.

21/08/2026
ከ500 በላይ ሰልጣኞች በኢንዱስትሪዎች  ለተግባር ስልጠና ተሰማሩቱ ማ ኢነሐሴ 14/2018 ዓ ምየፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያሰልጠናቸውን 592 ሰልጣኞ...
20/08/2026

ከ500 በላይ ሰልጣኞች በኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስልጠና ተሰማሩ
ቱ ማ ኢ
ነሐሴ 14/2018 ዓ ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያሰልጠናቸውን 592 ሰልጣኞች ከ100 በላይ በሚሆኑ ሆቴሎችና የቱሪዝም ድርጅቶች ውስጥ በመመደብ የተግባር (Cooperative Training) ስልጠና መስጠት መጀመሩን ገለጸ።
በትብብር ስልጠናው ወቅትም የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ሰልጣኞች በተመደቡባቸው ተቋማት በአካል በመገኘት የሥራ አፈጻጸማቸውንና የሥራ ሥነ-ምግባራቸውን በቅርበት የመከታተልና የመገምገም ሥራ ማካሄዳቸው ተጠቅሷል።
የኢንስቲትዩቱ የትብብር ስልጠና ክፍል አስተባባሪ አቶ ሳለአምላክ እንደገለጹት፤ ስልጠናው ሰልጣኞች በክፍል ውስጥ የቀሰሙትን የንድፈ-ሐሳብ (Theory) እውቀት በቀጥታ ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት የሙያ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የታለመ ነው።
በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በተግባር ስልጠና ላይ የሚገኙ ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ በኢንዱስትሪው ውስጥ ገብተው መሳተፋቸው የተሻለ የሥራ ልምድ እንዲያካብቱና ለሥራው ዓለም ዝግጁ እንዲሆኑ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

03/08/2026

በሆሳዕና ከተማ ለነገ ሀገር ተረካቢዎች የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

*የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆሳዕና ከተማ ለሚገነባው የመዋለ ህፃናት የከተማዋ ከንቲባ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሐምሌ 25/2018 ዓ/ም የግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብርን ከቱሪዝም መስህብ ጉብኝትና አካባቢ ጥበቃ ጋር በማቀናጀት በዛሬው ዕለት ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በሆሳዕና ከተማ በይፋ ማካሄድ ጀምሯል።

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት በበጀት ዓመቱ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ሰራተኞቹ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር ገምግመው በቀጣዩ በጀት ዓመት ዕቅድ ስኬታማነት ላይ በንቁ ተሳትፎ ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ተቋሙ ከዕቅድ ግምገማው በተጨማሪ ሰፊ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያካተተ ባለ ሶስት ቀናት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን፥ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሆሳዕና ከተማ ለሚገነባ የመዋለ ህፃናት የግንባታ የመሰረት ድንጋይ የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ በተገኙበት ተቀምጧል። በተያያዥም ለተማሪዎች የሚሆን የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና ቁሳቁስ ድጋፍ የማበርከት መርሃ ግብር ተከናውኗል።

የወጣው መርሃ ግብር እንደሚያሳየው ይህ በሆሳዕና ከተማ የተጀመረው እንቅስቃሴ በነገው ዕለት እሁድ በታዋቂው የሀንበርቾ ተራራ ላይ በሚደረግ ትምህርታዊ ጉብኝት የሚቀጥል ሲሆን፥ በሰኞው ዕለት ደግሞ በተራራው አካባቢ የአረንጓዴ አሻራን ለማሳረፍ የታለመ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን ፍጻሜውን ያገኛል።

Ethiopian Service የኢትዮጵያ ሰርቪስ ከሆሳዕና

5000 ችግኞች ተተከሉ።ቱ ማ ኢ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ተስ...
03/08/2026

5000 ችግኞች ተተከሉ።
ቱ ማ ኢ
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ተስፋን እንተክላለን" በሚል ሀገራዊ ራዕይ 5000 ችግኞች ተተከሉ።
በቦቢቾ ቀበሌ ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን ኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ተተክለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በሀምበሪቾ  ኢኮ ቱሪዝም  መዳረሻ ስፍራ ጉብኝት አደረጉ።የቱሪስት መዳረሻዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰው ሀይል ልማት ላይ...
02/08/2026

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በሀምበሪቾ ኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ ጉብኝት አደረጉ።

የቱሪስት መዳረሻዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰው ሀይል ልማት ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው:- የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

(ሆሳዕና ፣ሀምሌ 26/2018 ዓ.ም) የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች በሀበሪቾ ኢኮ-ቱሪዝም ስፍራ ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በጉብኝቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሀበሪቾ ኢኮ-ቱሪዝም ስፍራ ማራኪ መልክዓ-ምድራዊ ገፅታ ያለዉ ተራራ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢንስቲትዩት ከ50 ዓመት በላይ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ሲደግፍ የነበረ አንጋፋ ተቋም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በደረጃ አራትና በዲግሪ ደረጃ ሰልጣኞችን በማሰልጠን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ስራ ዕድል የሚያዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት በስልጠና ፣በማማከር ፣በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በባህላዊ ምግብና መጠጥ ልማት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በክልሉ የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችን እና መጠጦችን በማጥናት ለትውልድ እንዲተላለፍ እንዲሁም የምግብ ሜኖ ሆነው እንዲወጡ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በአዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረው ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ቱሪስቶች እንዲቆዩና ለሀገር ተጨማሪ ገቢ እንዲያስገኙ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ በርካታ የቱሪዝም ስፍራዎች ቢኖሩም የመጎብኘት ልምድ አናሳ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።

እንደዚ አይነት ጉዞዎች ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያን እውን በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር ብሄራዊ ትርክት ለማስረፅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ተቋሙ ለረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪውን የሰው ሀይል ፍላጎት ለሟሟላት ለዜጎች ሙያዊ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የጥናትና ምርምር በማድረግ አገልግሎቱ እንዲሻሻል እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቋሙን ሠራተኞች በማህበራዊ አገልግሎት በማሳተፍ አብሮት እና ወዳጅነት በማጠናከር በሀገር ግንባታ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አስታውቀው በትናትናው ዕለት በሆሳዕና ከተማ የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ መሠረት ድንጋይ መጣላቸውን አስታውሰዋል።

የከምባታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ ስዩም እንደተናገሩት በአካባቢው በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ይህንን መሸከም የሚችል የቱሪስት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የዞኑን የቱሪዝም መዳረሻዎ የማልማት ስራ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ ተጨማሪ ሁለት 777 ደረጃዎች በመገንባት የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከፍ ማድረግ ተችሏልም ብለዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሀምበሪቾን የኢትዮጵያዊያን መንደር ለማድረግ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ሎጆችን ጨምሮ በርካታ የቱሪስት አገልግሎቶችን የያዘ በመሆኑ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።
ሀምበሪቾ ተራራ ከምባታ ቀድሞ የሰፈረበትና የህዝቡ ታሪክ የተጠነሰሰበት፣ ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ማሳያ መሆኑንም ገልፀው ተራራው በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም መዳረሻነትን ዕውቅና አግኝቶ በጋራ የማልማት ሥራዎችም ተጀምሯል ብለዋል።

በኤልያስ ቲርካሶ

ከሴንትራል ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን

"የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው።''ኢንስቲትዩቱ በሆሳዕና ከተማ የመዋዕለ ህፃናት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረቱማኢሐምሌ 25/2018 ዓ.ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕ...
01/08/2026

"የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው።''
ኢንስቲትዩቱ በሆሳዕና ከተማ የመዋዕለ ህፃናት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ
ቱማኢ
ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናረሞ ቀበሌ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ መሠረት ድንጋይ የማኖር እና ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንስቲትዩቱ ተውልድን የመገንባት ሥራውን እያስቀጠለ መሆኑን እና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መሠረት ለሆኑ ህፃናት ዘመናዊ የመዋዕለ ህፃናት መገንባቱ በህፃናት አዕምሯዊ ዕድገት ላይ ሊኖር የሚችለውን ጉልህ ሚና አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ ደረጃውን የጠበቀ የመዋዕለ ህፃናት መገንባት ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ቁሳቁስ እንደሚሟላም አሳውቀዋል።

'' የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው።''በሚል የተቀመጠው የማዋዕለ ህፃናት ግንባታ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲውል አስፈላጊው ክትትል እደሚያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከግንባታው ባሻገር ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ለሆሳዕና ከተማ ከንቲባ ለአቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እና ለትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊው አስረክበዋል።

ክቡር ከንቲባው በከተማው የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ በመቀመጡ እና በክረምት የበጎ ተግባር አገልግሎት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማከናወን እዚህ በመምጣታችሁ የኢንስቲትዩቱን አመራርና ሠራተኞች ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል ። የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችም መርቀዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

01/08/2026

"ከፍትፍቱ ፊቱ!" ይላል የሀገሬ ሰው

| ​ቱሪዝም እጅግ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚከወን ረብጣ ቢሊየን ገንዘቦች የሚያንቀሳቅስ ዘርፍ ነው።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ''የመደመር መንግስት'' በተሰኘው መጽሐፋቸው ቱሪዝም የመንግስታቸው ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶ መሆኑን ገልጠዋል።

ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ ከግራም ከቀኝም የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የቱሪስት መዳረሻ ማዕከላትን መመልከት በቂ ይሆናል።

''ከፍትፍቱ ፊቱ'' እንዲል የሀገሬ ሰው ፤ እንግዶች ከአየር መንገድ ተነስተው ወደ ሁሉም መዳረሻዎች እስኪደርሱ ድረስ ከደረሱም በኋላ በሚያገኙት አገልግሎት ለስራ የተመደቡት ግለሰቦች ያለሆነ ፊት እንኳን ካሳዩ ቱሪስቶቹን ማስደንበራቸው አይቀርም።

በዚህ ዘመን ሰውን የመንከባከብ ነገር ሳይንስ ሆኗል።ሳይንስ ደግሞ በስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ አንዳች ለውጥ ለማምጣት ሰዎችን በማሰልጠን መርህ ማድረግ ይቻላል።

የሀገሩን ቱሪዝም ስልጠና የሚመራው የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆሳዕና ከተማ 2018 ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ፣ የበጎ አድራጎትና ማህበረሰብ አገልግሎት ማስጀመሪያ ዝግጅት እየተከናወነ ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተቋሙ ስልጠናን በላቀ ደረጃ በመስጠት የሀገሪቱን የቱሪዝም መስተንግዶ ጥራት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እየሰራ ነው ብለዋል።

​ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ከመደበኛው የስልጠና ማዕቀፍ ባለፍ በአገልግሎት ሰጪ ግለሰቦች የግንዛቤ ስልጠናዎች እየተሰጣቸው ነው።

በዚህም መሰረት በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች (በተለይም የሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች) የደንበኛ አያያዝ እና መስተንግዶ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ስራ አጥ ወጣቶች በዘርፉ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ታስቦ በርካታ ስራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።

በተጨማሪም ​ኢትዮጵያ በቅርቡ እንድታዘጋጅ የተመረጠችውን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ወደ ሀገር እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ከአየር መንገድ አቀባበል ጀምሮ እስከ ሆቴል መስተንግዶ ድረስ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሳደግ የዚህ ዓመት ትልቁ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አቶ ጌታቸው አብራርተዋል።

እንግዶች ወደ ሀገር ሲገቡ አየር መንገድ ላይ ከሚያገኙት የመጀመሪያ አቀባበል አንስቶ የሚስተናገዱበት ሁኔታ ሀገርን የሚወክል በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል።

ኢትዮጵያ ከአፍ የወደቀ ጥሬ ዋርካ የሚሆንባት ምድር ናት።ፈጣሪ ሁሉን ሰጥቶን ሲያበቃ ፀጋዎቻችንን ካክፋፋን ልክ አይሆንም።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ በሆኑት እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሀላላ ኬላ እና ጨበራ ጩርጩራ ባሉ አካባቢዎችም የዳሰሳ ጥናቶችን በማካሄድ በአካባቢው ላሉ ነዋሪዎች ጭምር የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

አቶ ጌታቸው ማህበረሰቡ ሀገሩን በማስተዋወቅ ረገድ የራሱን አምባሳደራዊ ሚና እንዲወጣና የእንግዳ ተቀባይነት ባህሉን ይበልጥ በማሳደግ ለታላቁ ነገር እንዲዘጋጅ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።

ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽን

ያፌት ገ/ህይወት

ከሀዲያ ዞን ፤ ሆሳዕና

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት  አፈፃፀሙን ገመገመ። ቱ ማ ኢሐምሌ 25/2018 ዓ ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸ...
01/08/2026

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ገመገመ።
ቱ ማ ኢ
ሐምሌ 25/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መድረክ በተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ባሉን የሥራ ክንውኖች እና የተገኙ ውጤቶች የሠራተኞችና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት የሰጠውን ትኩረት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ከመሠረተ ልማት ግንባታ ጎን ለጎን የሚሄድ የሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋል።
የተቋሙ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና አጠቃላይ ተቋማዊ እንቅስቃሴዎችን ገልጸዋል።
በዕለቱ ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ዳግም አዲሱ የቀረበ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች ተዳስዋል።
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ፡ የዕቅድና በጀት፣ ክትትልና ግምገማ ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ሽመልስ ማሰረሻ ለተሳታፊዎች ቀርቦ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኗል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

በምግብ  ቱሪዝም አህጉራዊ ስኬት  እንኳን ደሰ አለህ  ሼፍ ሄኖክ
31/07/2026

በምግብ ቱሪዝም አህጉራዊ ስኬት
እንኳን ደሰ አለህ ሼፍ ሄኖክ

አካታችነትን ያከበረ፤ ለስኬት የበቃ፤  ሐምሌ 13/2018 ዓ.ምቱ ማ ኢየሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ለአካል ጉዳተኝነት ቦታ አልነበረውም ይልቁንም ቁመት፣ ውብት ቅድሚያ ይሰጣቸው ነበር፤ በዚህ የ...
20/07/2026

አካታችነትን ያከበረ፤ ለስኬት የበቃ፤
ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም
ቱ ማ ኢ
የሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ለአካል ጉዳተኝነት ቦታ አልነበረውም ይልቁንም ቁመት፣ ውብት ቅድሚያ ይሰጣቸው ነበር፤ በዚህ የተነሳ ብዙዎች ከዚህ ኢንደስትሪ ተገልለው ይኖሩ እንደነበር ይነገራል፡፡
በፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ይህን አመለካከት የሰበረ አካታችነትን ያከበረ እና ለስኬት የበቃ ሥራ እውን ሆነ፡፡
ወ/ሮ መስታዎት ጌታቸው ከጊዜ በኋላ በገጠማት ችግር የአካል ጉዳተኛ ሆናለች፤ ነገር ግን በአዲስ መንፈስ ራሷን አጠንክራ በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቅዳሜና የእሁድ ( የእረፍት ቀናት) መርሃ ግብር በሆቴል ማኔጅመንት ትምህርቷን ተከታትላ ለመመረቅ በቅታለች፡፡
በትምህርት ጊዜዋ ምቹ ሁኔታዎች በማይኖሩበት ጊዜ መምህራኑ እና የትምህርት አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረጉላት ስልጠናዋን ማጠናቀቋን ገልጻለች፡፡
የሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ለሁሉም ክፍት መሆኑን እና ሙያውን ይዘው በዘርፉ የሥራ እድል ተጠቃሚ መሆን ለሚፈልጉ አካል ጉዳተኞች ሁሉ ማሳያ የሆነችውን መስታዎትን እንኳን ደስ አለሽ ማለት እንወዳለን፡፡

ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

Address

Near Guenet Hotel
Addis Ababa
4350

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tourism Training Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share