14/07/2024
*የዓሹራ_ፆም ያለው ትሩፋት*
*فضل صوم يوم عاشوراء*
ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) በዘገቡት ሀዲስ ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በመጡ ግዜ የሁዶች ዓሹራን ሲፆሙ አይተዋቸው ለምን እንደሚፆሙት ሲጠይቋቸው "ይህ ቀን መልካም ቀን ነው፣ አላህ በኒ ኢስራኢልን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው፣ በዚሁ ምክንያት ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ፆሙት" በማለት መለሱላቸው። ነቢዩም (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) "እኔ ለሙሳ ከናንተ ይበልጥ የተገባው ነኝ" በማለት ፆሙት ሌሎችም እንዲፆሙት አዘዙ። (ቡኻሪ) በሌላ
በሙስሊም ዘገባ "ይህ ታላቅ ቀን ነው። ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበትና ፈርኦንንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት" በማለት ተዘግቧል።
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قَدِمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ المَدِينَةَ فَرَأَى اليَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، فَقَالَ: «مَا هَذَا؟» قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ، فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ: «فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ»، فَصَامَهُ، وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ. أخرجه البخاري في صحيحه.
وفي رواية مسلم- ((هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وغرّق فرعون وقومه))
فعَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ : مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ إِلا هَذَا الْيَوْمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَهَذَا الشَّهْرَ يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ . " رواه البخاري
ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) "ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከዓሹራእ እና ከረመዳን ሌላ አንድንም ፆም ከሌላው አስበልጠው ትኩረት የሰጡበት አላየሁም" ብሏል። (ቡኻሪ)
فعن عَبْدِ اللهِ بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قال: حِينَ صَامَ رَسُولُ اللهِ صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّهُ يَوْمٌ تُعَظِّمُهُ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ: «فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ إِنْ شَاءَ اللهُ صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ» قَالَ: فَلَمْ يَأْتِ الْعَامُ الْمُقْبِلُ حَتَّى تُوُفِّيَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ. أخرجه مسلم في "صحيحه"
አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው አሉዋቸው። እሳቸውም፦ "የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከደረስን ዘጠነኛውንም ቀን እንፃማለን" አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ሳይደርሱ ሞቱ።" (ሙስሊም)
09/06/2024
ክቡር ፕሬዚደንቱ መዲና ገቡ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ እና ምክትላቸዉ ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን እንዲሁም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ከማል ሐሩን መዲና ገቡ፡፡
ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም መዲና ሲገቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመዲና ተወካይ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ተጠሪና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ ፣የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም እዲሁም በመዲና የሐጃጆች መስተንግዶ ዋና አሥተባባሪ ቃሪእ አብድልሙኢን ኑረዲን ተቀብለዋቸዋል፡፡
ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም በመዲና እና ከዚያም በመካ በሚያደርጉት ቆይታ የሐጃጆችን መስተንግዶ በተመለከተ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የሑጃጅ መስተንግዶ ኃላፊዎች ገለጻ እንደሚደረግላቸውና፣ ሐጃጆችን በአካል አግኝተው በማነጋገር በመስተንግዶ ረገድ ያላቸውን አስተያየት እንደሚያደምጡ ይጠበቃል፡፡
05/06/2024
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጣም አስፈላጊ እና አስቸኳይ ማሳሰቢያ፣
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ለውድ የ1445 ዓ.ል. ሐጃጆች።
ከቀደሙት ዓመታት በተለየ፣ የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር፣ ለ1445 ዓ.ል. ሐጃጆች ኑሱክ የተሰኘ ልዩ የመታወቂያ ካርድ ወይም ባጅ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
ይህን ልዩ መታወቂያ አለመያዝ ሐጃጁን ከሐጅ ለመታገድና ተይዞ ያልተፈቀደለት ሐጃጅ ተብሎ ከሀገር ሊያስባርረው ይችላል።
በመኾኑም፣ የተከበራችሁ የአሏህ እንግዶች ይህን የሐገሪቱ ሕግ በማክበር፣ የኑሱክ ልዩ የመታወቂያ ካርድዎን በማንኛውም ጊዜ እንዲይዙ እናሳስባለን።
እናመሠግናለን።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
27/05/2024
ግንቦት 18፣ 2016 ዓ.ል | ዙል ቂዳህ 18፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሐጃጆች በኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ከመካ እና ከመዲና ወደ ሀገር ቤት ስልክ መደወል በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |
የ1445 ዓ.ሒ. የአሏህ እንግዶች በሐጅ ምዝገባ ወቅት ያስመዘገቡትን የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ በመጠቀም ከመዲና እና ከመካ ወደ ቤተሰቦቻቸው ስልክ ደውለው በሰላም መግባታቸውን መግለጽ በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናገሩ።
በሐጅ ጉዞ ላይ ውጣ ውረድና ልፋት መኖሩ የኢባዳ አካል ቢኾንም፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለዘንድሮ የአሏህ እንግዶች ተገቢ አገልግሎት በመስጠት ከኢባዳቸው እንዳይዘናጉ ማድረግ በመቻሉ መደሰታቸውን ሐጃጆች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አገልግሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘመነ በመሄድ፣ የዘንድሮ የአሏህ እንግዶች የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዳቸውን በሳዑዲ ሲምካርድ መቀየር ሳያስፈልጋቸው፣ የሮሚንግ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን መዲና የተገኙት የመጅሊሱ የIT ክፍል ባልደረባ አቶ ጀማል ኢብራሂም ተናግረዋል።
ባለሙያው አያይዘው እንደጠቀሱት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ1445 ዓ.ሒ. ሐጃጆች ብዙ ጠቃሚ አሠራሮችን ሥራ ላይ እያዋለ ይገኛል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተስማማው መሠረት የ1445 ዓ.ሒ ሐጃጆች የሐጅ ምዝገባ ሲያካሂዱ ያስመዘገቡት ስልክ ቁጥር በሮሚንግ አገልግሎት የተመዘገበ በመሆኑ፣ ሲም ካርዳቸውን ይዘውት በመጓዝ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መኾን እንደሚችሉ አቶ ጀማል ተናግረዋል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተገባው ውል መሠረት የሮሚንግ አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች፣ 150 ደቂቃ የድምጽ እና 500 ሜጋ ባይት ፓኬጅ መጠቀም እንደሚችሉ አቶ ጀማል ተናግረዋል።
ብዙ ሐጃጆች ከመነሻው ቴሌብር ላይ ያለውን የሐጅ ፓኬጅ ገዝተው በመምጣት ስህተት እየሠሩ እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ጀማል፣ ይህን መጠቀም የሚችሉት ነባር የሮሚንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ሐጃጆች ብቻ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የሮሚንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልነበሩ ሐጃጆች፣ በሐጅ ምዝገባ ወቅት ያስመዘገቡት ቁጥር ያለበትን ሲም ካርድ ይዘው በመምጣት የፓኬጁ ተጠቃሚ እንደሚኾኑ ተናግረዋል።
በሐጅ ቆይታቸው በእርሱ ሲጠቀሙ ቆይተው የተሰጣቸው ፓኬጅ ሲያልቅ፣ ቴሌብር ላይ ያለውን የሐጅ ፓኬጅ የሚጠቀሙበት መንገድ እንደሚመቻች አቶ ጀማል ተናግረዋል።
ወደ መዲና ለመሳፈር ተራቸውን በመጠበቅ ላይ የሚገኙ የአሏህ እንግዶች፣ ለሐጅ ሲመዘገቡ ያስመዘገቡት ስልክ ቁጥር ያለበትን ሲም ካርድ ይዘው እንዲሳፈሩ አቶ ጀማል በአጽንዖት አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ሐጃጆችን የሮሚንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ያደረገው፣ አገልግሎቱን ከማዘመን ባሻገር ለራሳቸው ደኅንነት ሲል መኾኑንም ተናግረዋል።
የሮሚንግ (Roaming) አገልግሎት፣ በሐጅ ወቅት ብቻ ሳይኾን፣ በማንኛውም ጊዜ ከሀገር የሚወጡ ሰዎች ከየትኛውም የዓለም ሀገር ኾነው በሀገር ቤት ሲም ካርዳቸው መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር
25/05/2024
ግንቦት 14፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 14፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተገቢ ውክልና ሊያገኝና በንቃትም ሊሳተፍ ይገባል ተባለ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሐዋሳ |
በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአግባቡ ሊወከልና በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተነገረ።
ይህ የተነገረው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክርና በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ከክልሉ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ (ግንቦት 14) ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
መድረኩ በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሚጠበቀው የነቃ ተሳትፎ ዙርያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዓላማ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው አጀንዳ ዙርያ ባደረጉት ውይይት ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሠረት በመኾኑ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ድምጽ በአግባቡ ሊሰማበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለዚህም የሀገሪቱ ሙስሊሞች በሀገራዊ የምክክር መድረኩ ላይ ተመጣጣኝ ውክልናና የተሳትፎ ዕድል ሊያገኙ እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአጽንዖት ተናግረዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የምክክር መድረኮች በሙሉ አካታችና የተለያዩ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች በአግባቡ የሚወከሉበት መኾኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ተጠቅሷል።
የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ሐሳብ ላይ የጋራ መግበባት ላይ በመድረስ መድረኩ በስኬት ተጠናቅቋል።
በሐዋሳ ከተማ ፓራዳይስ ሆቴል አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችና አባላት፣ የዑለማ ምክር ቤት አባላት፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ዱዓቶች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
22/05/2024
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የመጀመሪያዎቹ 312 የ1445 ዓ.ሒ ሑጃጆች ወደ መዲነቱል ሙነወራ ተሳፈሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዘንድሮ የሐጅ ሥርዓትን ለመፈፀም ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ 312 የ1445 ዓመተ ሒጅራ ሑጃጆች በዛሬው ዕለት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲነቱል ሙነወራ አሸኛኘት ተደረገላቸው።
ዛሬ በተደረጉ ሁለት በረራዎች በሳዑዲ አየር መንገድ 45፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ 267 በድምሩ 312 የአሏህ እንግዶች ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲና ተጉዘዋል።
በ1445 ዓ.ሒ ተመዝግበው ዛሬ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲነቱል ሙነወራ ለተጓዙት የአሏህ እንግዶች በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ የተመራ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
የዛሬውን ሽኝት ምክንያት በማድረግ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የተሳካ እንዲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገውን ጉልህ አስተዋጽዖ ጠቅሰው፣ በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።
በዘንድሮ ዓመት ሐጅ ለማድረግ ከተመዘገቡ 12 ሺህ (አሥራ ሁለት ሺህ) ሑጃጆች ውስጥ 8 ሺህ 500 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ) የሚኾኑት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
ዛሬ ሽኝት የተደረገላቸው የተከበሩ የአሏህ እንግዶች መዲና ሲደርሱ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሼይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ በሚመራ የልዑካን ቡድን አማካኝነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ ተናግረዋል።
የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ መስተንግዶ "የዘምመነ መስተንግዶ ለአል-ረህማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሼይኽ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር መጀመሩን ተናግረዋል።
በዛሬው የሑጃጆች የአሸኛኘት ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ተገኝተዋል።
ከአሁን በፊት የሐጅ ምዝገባ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ብቻ ይከናወን እንደነበረና ከክልል የሚመጡ ሑጃጆች እንግልት ይደርስባቸው እንደነበር ኃላፊው አስታውሰዋል።
ካለፈው ዓመት ጀምሮ የሐጅ መስተንግዶ ምዝገባ፣ በ18 የምዝገባ ጣቢያዎች የተካሄደ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፣ ዘንድሮ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ጥያቄ መሠረት በማድረግ የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎች ቁጥር ወደ 30 እንዲያድግ መደረጉን ተናግረዋል።
ዛሬ በረራ ያደረጉት ሁሉም ሑጃጆች ቪዛና የአውሮፕላን ቲኬቶቻቸውን በተመዘገቡበት የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ እንዲቀበሉ መደረጉንም ኃላፊው ተናግረዋል።
የተከበሩ የአሏህ እንግዶች እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱና እንዲደጋገፉ ለማስቻልም በአንድ አሚር ስር 45 ሑጃጆችን የማደራጀት ሥራ መሠራቱንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዘንድሮው የአሏህ እንግዶች ከሌሎች ሀገራት ሑጃጆች የሚለዩበት መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ያዘጋጀ ሲኾን፣ የተከበሩ የአሏህ እንግዶች ዩኒፎርሙን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ኃላፊው አሳስበዋል።
የዘንድሮ የሐጅ መስተንግዶ የዘመነ እንዲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በየደረጃው የሚገኙ የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች፣ የIT ባለሙያዎች፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና የመንግሥትና የግል ባንኮችን ኃላፊው አመስግነዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
22/05/2024
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአል-ረህማን እንግዶችን መዲነቱል ሙነወራ ይዞ ገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳፈሩት የ1445 ዓ.ሒ የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲነቱል ሙነወራ ገቡ።
ሐጃጆቹ መዲና አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዲነቱል ሙነወራ የገቡት የአል-ረህማን እንግዶች 263 ሲኾኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 55 ያህል ሴቶች መሆናቸውን የአቀባበል አሥተባባሪው አቶ አብዲ ሲራጅ ተናግረዋል።
መዲነቱል ረሱል (ሶ.ዐ.ወ.) የገቡት ሐጃጆች በቆይታቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ እና ስለ ጤናቸው ጉዳይ አስፈላጊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
የ1445 ዓ.ሂ. የአል-ረህማን እንግዶች በመዲና በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ቆይታ መስጂድ ቂብለተይንን፣ ኡሑድ ተራራን፣ በዚሁ ስፍራ ሸሂድ የሆኑትን የነሐምዛን ቀብር ይዘይራሉ።
በመጨረሻም በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዳ በቡድን ኾነው ከዘየሩ በኋላ፣ ወደ መካ እንደሚጓዙ ከመስተንግዶ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
21/05/2024
ሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙን ያገለለ የተሳታፊ ልየታ እንደተደረገበት ተገለፀ!
በኢትዮጲያ በመጪው ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር የሙስሊሙ ቁጥር አነሳ በመሆኑ የተሳታፊዎች ልየታ በድጋሚ እንዲካሄድ እና በሙስሊሙ በኩል የቀረቡ አጀንዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ እንዲካተቱ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።
…
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባቀረበው ጥያቄ የሙስሊሞች ተሳትፎ በሕዝባችን ቁጥር ልክ መሆን ያለበት በመሆኑ የተሳታፊዎችና የአወያዮች ቁጥር በዚሁ መሠረት በኮሚሽኑ "የአካታችነት መርህ መሠረት ጠ/ም/ቤቱ ያቀረበውን የሕዝበ ሙስሊሙ የምክክር እጀንዳዎች ለጉባኤው ለማሰማት፤ ለማብራራት የሚችሉ ተገቢ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ተወካዮች እንዲካተቱ ይቻል ዘንድ የህዝብ ጥያቄዎች ከፍተኛ እየሆነብን በመምጣቱ ሥብጥሩ በፍትሃዊነት እንደገና እንዲቃኝ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የበላይ ጠባቂ ለሆኑት ለፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
…
በኢትዮጵያ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር ይችላል የተባለው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ውጪ እና ግጭት ባለባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልልች አንዳንድ አካባቢዎችን ሳያካትት በ10 ክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮች ለምክክሩ የሚሳተፉ አካላትን ልየታ ቢያካሂድም የሙስሊሙ ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
…
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተወካዮች ከሀገራዊ ምክክሩ "3"ኮሚሽነሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በባለሙያ በተሰጠ መግለጫ ላይም በተሳታፊና በአወያይ ደረጃ የሙስሊሞችን ተሳትፎ እንዲነገረን ብንጠይቅም ከምክክር ኮሚሽኑ ምላሽ እንዳልተሰጠ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡
…
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው እና በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት የቀረቡ የመስሊሙ አጃንዳዋች እንዲካተቱ እና ህዝበ ሙስሊሙም በቁጥሩ ልክ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
…
©ሀሩን ሚድያ
21/05/2024
«አንድነታችን ለሰላማችን» በሚል መሪ ቃል በአማራ ክልል በወሎዋ ኮምቦልቻ ከተማ ሀገር አቀፍ የአብሮነት የወንድማማችነት የሰላም ዝግጅት እየተጧጧፈ ይገኛል።
በፌዴራሉ እስልምና ጉዳይ የበላይ ጠባቂነት የሚያዘጋጀው ይኽ ታላቅ የአንድነትና የሰላም መድረክ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ በጂማ ከተማ በተለያዬ ቅርፅ ቀለም ሲደረግ የቆየ ሲሆን በሶስተኛ ግዜ በአማራ ክልል በኮምቦልቻ ከተማ የሚዘጋጀው ዝግጅት የክልሉን ተጨባጭ ባገናዘበና ወቅቱን በዋጀ ዝግጅት በሰደቃ በዱአ እንዲሁም በዓሊሞች፤ በሙህራንና በወጣቶች በፓናል ውይይት የታጀበ ልዩ ዝግጅት እንደሆነ አረጋግጠናል። ‼️
ዝግጅቱ ከቅዳሜ ግንቦት 17 የሚጀምር ሲሆን እሁድ ግንቦት 18 ደግሞ በኮምቦልቻ ስታዲየም ኳስ ሜዳ በሚኖረው ዝግጅት ይጠናቀቃል። ቅዳሜ የክልል እስልምና ጉዳይ መሪዎች ዓሊሞች ሙህራን የሀገር ሽማግሌችና ወጣቶች በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ጉዳይና በመሰል ሀገራዊ ጉዳዮች የፓናል ውይይት ሲደረግ፤ እሁድ ደግሞ የአብሮነት የሰደቃና የዱዓ እንዲሁም ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በኮምቦልቻ ስታዲየም ኳስ ሜዳ በድምቀት ይካሄዳል። በዝግጅቱ ለአዲስ ፕሮጀክት በተጠየቁ ቦታዎች የመሰረት ድንጋይ ይጣላል።
በዝግጅቱ
የፌዴራል መጂላስ ፕሬዝዳንት ሀጂ እብራሂም ቱፋና ስራ አስፈጻሚዎቻቸው
ኡለማዎች
ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች
የአዲስ አበባ እና የድሬ ደዋ የመጂሊስ ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የሁሉም የክልል መጅሊስ ፕሬዝዳንቶች
ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች
ዱአቶች ኡስታዞች ሙህራኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች ይሳተፉበታል ‼️
«አንድነታችን ለሰላማችን»
ግንቦት 18 ቀን ከወሎ ኮምቦልቻ አይቀርም ‼️
21/05/2024
ግንቦት 12፣ 2016 ዓ.ል. | ዙል ቂዳህ 12፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በመዲና የአሏህ እንግዶችን ተቀብለው ለሚያስተናግዱ ሠራተኞች የሥራ መመሪያ ተሰጠ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ግንቦት 12፣ 2016 (መዲና) - በሳዑዲ አረቢያ፣ መዲና የ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥርዓትን ለመፈፀም መዲና መሸጋገሪያቸው የኾኑ የአሏህ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊው ቅድመ-ዝግጅት መጠናቀቁ ተነገረ።
ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የኾኑት ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ ናቸው።
ሸይኽ አብዱልሃሚድ፣ መዲና መሸጋገሪያቸው የኾኑ ሐጃጆችን ለሚቀበሉ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች ቀደም ሲል በተደረገው የሥራ ክፍፍል መሠረት፣ የሥራ አቅጣጫ ተሰጥቷል ብለዋል።
ማክሰኞ ግንቦት 13፣ 2016 (ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.) የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲና ሲገቡ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሠራተኞች፣ ከምክር ቤቱ ጋር የሚሠሩ የመዲና ነዋሪ ወንድሞች እና የመዲና ኢስላሚክ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ትህትናና ቅንነት የተላበሰ መስተንግዶ ማድረግ እንደሚገባቸው ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሳስበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና እና የሐጅ ኮሚቴ የሲስተም ተጠሪ ኢንጂነር አንዋር ሙስጠፋ መጅሊሱ የሐጅ መስተንግዶን ለማዘመን የሚያደርገው ጥረት ለአል-ረህማን እንግዶች ያለውን ክብር የሚያሳይና እንደ ተቋም ትልቅ ኃላፊነቱ በመኾኑ በትጋት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱን የሐጅ መስተንግዶ ለማዘመን የተደረገው ጥረት ፍሬ እያፈራ መኾኑን የጠቀሱት ኢንጂነር አንዋር፣ የምዝገባ ሂደቱን ቀልጣፋ ለማድረግ የተሠራው ሥራ በጣም ውጤታማ በሚባል ደረጃ የተሳካ መሆኑን ተናግረዋል።
በ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ በየዘርፉና በየክፍሉ ከዚህ ቀደም የተስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ አዳዲስና ዘመናዊ አሠራሮች መጨመራቸዉን ኢንጂነር አንዋር ጠቅሰዋል።
"የአል-ረህማን እንግዶችን ለማስተናገድ የታጫችሁ ሠራተኞችና ከመዲና ዩንቨርሲቲ
የተካተታችሁ ጊዜያዊ ቅጥር ሠራተኞች ይህን ዕድል ማግኘት ትልቅ ክብር በመኾኑ ሐጃጆችን በየዘርፋችሁ የማገዝ አማና በእናንተ ላይ ተጥል" ብለዋል ኢንጂነር አንዋር።
የሐጃጆችን ችግር ለመቅረፍ ከተዘረጋው አሠራር አንዱ ሐጃጆችን አርባ አምስት አባላት ባሏቸው ቡድኖች አዋቅሮ፣ እርስበርስ ተዋውቀው በአሚር እየተመሩ እንዲንቀሳቀሱ መደልደሉ መሆኑን አስታውሰዋል።
ይህ የቡድን አሠራር የአል-ረህማን እንግዶች የሐጅ ሥርአተ-ክንዋኔን ጀምረው ወደ ሀገር ቤት አስከሚመለሱ ድረስ የሚዘልቅ በመኾኑ፣ የአል-ረህማን እንግዶች ሐሳባቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጡበት የሐጅ ጉዳይ ብቻ እንዲሆን ይረዳል ብለዋል።
ኢንጂነር አንዋር በመጨረሻም፣ "የሐጅን ሥራ የምታሳልጡ ሠራተኞች የአሠራሩን ተያያዥነት ከግምት በማስገባት በንቃት የእንግዶቻችሁ አገልጋይ ልትሆኑ ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc