Amana Model School

Amana Model School Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amana Model School, School, Amana Model Secondary School, XQV4+HVV, Addis Ababa.

Amana Model Secondary School is an academic institution with a mission to foster creativity, curiosity & social responsibility in a supportive learning environment!

አማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ለኢትዮጵያ አገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፋቸውን ሲያበስር ከፍተ...
24/08/2026

አማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ለኢትዮጵያ አገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፋቸውን ሲያበስር ከፍተኛ ኩራትና ደስታ ይሰማዋል!

ይህ አስደናቂ ስኬት የተማሪዎቻችንን፣ የመምህራኑን፣ የተማሪዎቻችን ወላጆችን፣ የትምህርት ቤታችንን አመራር እና መላውን የአማና ማኅበረሰብ ቁርጠኝነት፣ ጽናት እና ትጋት የሚያንፀባርቅ ነው።

ውድ ተማሪዎቻችን ለዚህ አስደናቂ ውጤት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! እንዲሁም ለትጉኃን የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ ለተማሪዎቻችን ደጋፊ ወላጆች፣ ለትምህርት ቤታችን አመራሮች እና ለዚህ አስደናቂ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ልባዊ አድናቆታችንን እንገልጻለን።

በጋራ ልህቀታችንን እያከበርን፣ በጋራ ለበለጠ ስኬት መትጋታችንን እንቀጥላለን!

አማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

💐💐💐 Congratulations! 💐💐💐Amana Model Secondary School (AMSS) is proud to announce a 100% pass rate in the 2018 (E.C.) Nat...
24/08/2026

💐💐💐 Congratulations! 💐💐💐

Amana Model Secondary School (AMSS) is proud to announce a 100% pass rate in the 2018 (E.C.) National Secondary School Leaving Examination!

This remarkable achievement reflects the dedication, perseverance, and hard work of our students, teachers, parents, school management, and the entire AMSS community.

Congratulations to our dear students on this outstanding achievement! We also extend our heartfelt appreciation to our committed teachers, supportive parents, dedicated school leadership, and everyone who contributed to this wonderful success.

Together, we celebrate excellence.

Together, we continue to strive for even greater achievemeAmana Model School School

የአማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ያበስራል!ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ምዝገባ አሁን ተጀምሯልለምን የአማና ሞዴልን ...
20/07/2026

የአማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ያበስራል!

ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ምዝገባ አሁን ተጀምሯል

ለምን የአማና ሞዴልን ይመርጣሉ?

◉ ተግባራዊ ትምህርት: በዘመናዊ የሳይንስ ላብራቶሪ የተደገፈ ጥራት ያለው ትምህርት።

◉ ምቹ አካባቢ: ለተማሪዎች ስብዕና እና ዕውቀት እድገት ተስማሚ የሆነ የስራ ከባቢ።

◉ ብቁ መምህራን እና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር የተመጠነ (አነስተኛ) መሆን

◉ ተማሪዎች አመቱን ሙሉ በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ የክለብ ተሳትፎዎች፣ የውድድር መድረኮች እና ከተለመደው የክፍል ትምህርት ውጪ በሆኑ እንቅስቃሴዎች (Extra-curricular activities) ላይ በመሳተፍ ክህሎታቸውንና ተሰጥኦአቸውን ያበለጽጋሉ።

የማመልከቻው ጊዜ ሳያልፍብዎ ልጆችዎን ያስመዝግቡ!

የስልክ ቁጥሮች:
📱 +251966333339
📱 +251966444449

ኢሜይል: [email protected]

አድራሻ: ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 04፣ የቤት ቁጥር 605 (አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ) ወይም የቀድሞ አልፋ ዩኒቨርስቲ የነበረበት ህንፃ

Job Vacancy AnnouncementAmana Model Secondary School is hiring!Position: Teachers (All Subjects)Location: Addis Ababa, E...
05/07/2026

Job Vacancy Announcement

Amana Model Secondary School is hiring!

Position: Teachers (All Subjects)
Location: Addis Ababa, Ethiopia
Deadline: July 31, 2026

We are looking for passionate and qualified High School Teachers to join our team.

Salary: Negotiable and as per the school’s scale

Minimum Requirements:
• Bachelor’s degree in the relevant subject area
• At least 5 years of teaching experience at high-school level
• Strong communication and classroom management skills
• Passion for teaching and student development

Working conditions

• Full time, permanent after prohibition period.

How to Apply?

Any interested applicant can apply via [email protected] or in person in our address:

Lancha Alpha university building, kirkos subcity, woreda 04 ,addis ababa for more information contact us 0966333339


02/07/2026

በ2018 የትምህርት ዘመን የተጀመረው የአማና ስታርት አፕ ውድድር የመጨረሻ ዙር ፕሮግራም

የ2019 የትምህርት ዘመን የአዲስ ተማሪዎች ቅድመ-ምዝገባ!​ለ2019 የትምህርት ዘመን በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የቅድመ-ምዝገባ ቅጽ (Pre-R...
01/07/2026

የ2019 የትምህርት ዘመን የአዲስ ተማሪዎች ቅድመ-ምዝገባ!

​ለ2019 የትምህርት ዘመን በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የቅድመ-ምዝገባ ቅጽ (Pre-Registration Form) ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

https://forms.gle/3dCJfmQzuX1183D18

የ2018 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ!ዛሬ በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓት በታላቅ ድምቀት ተካ...
28/06/2026

የ2018 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ!

ዛሬ በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።

በ Behavior እና Academic Progress የተሻለ ውጤት ላመጡ፣ ከየክፍሉ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ተማሪዎቻችን የሜዳሊያና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቷል።

ከትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ኮከቦቻችን፦

1️⃣ ዘይነብ ጀማል (10ኛ ክፍል) — 99.35% 🥇🏆

2️⃣ ሰልማን የህያ (11ኛ ክፍል) — 98.67% 🥈

3️⃣ ኒያ ሰኢድ (11ኛ ክፍል) — 98.43% 🥉

የእነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ኮከብ ተማሪዎቻችን የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በዕለቱ በተገኙት የክብር እንግዶቻችን በ አቶ ኢብሳ ዳሚና፣ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና በፕሮፌሰር አህመድ ሙስጠፋ እጅ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቻችንም ሽልማታቸውን በታላቅ ኩራትና ደስታ ተቀብለዋል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በዌብ ዲዛይን (Web Design & Development) እና በማርኬቲንግ (Marketing & Sales Management) በሙያ ትምህርት ደረጃ 1 (Level 1) ተመርቀዋል።

በዕለቱም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ መሀመድ ከማል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የዓመቱን አጠቃላይ የሥራ ሪፖርትም አቅርበዋል።

ለመላው የአማና ሞዴል ማኅበረሰብ፣ ለተሸላሚ ተማሪዎቻችንና ለወላጆች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

[ሰኔ 21/2018]

በአማና የተካሄደው የመጀመሪያ የ'ስታርት አፕ' ውድድር ፍጻሜ በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ!ሰኔ 8/2018በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ እና ሥራ ፈጣ...
16/06/2026

በአማና የተካሄደው የመጀመሪያ የ'ስታርት አፕ' ውድድር ፍጻሜ በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ!

ሰኔ 8/2018

በአማና ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ እና ሥራ ፈጣሪነትን ለማበረታታት ሲካሄድ የቆየው የ'ስታርት አፕ' ውድድር የመጨረሻ ዙር ፍፃሜ ዛሬ በትምህርት ቤቱ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።

በትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ኢሳም መሐመድ አበረታች ንግግር የተጀመረው ይህ መድረክ፣ የማጣሪያ ውድድሩን ያለፉ ስድስት ምርጥ ቡድኖች ማኅበረሰብ-ተኮር የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዳኞችና ለታዳሚዎች ያቀረቡበት ነበር።

ተማሪዎቹ ከዳኞች ለቀረቡላቸው ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ምላሾችን በመስጠት የታዳሚውን ቀልብ ስበዋል።

የውድድሩ አሸናፊዎችና የተሰጣቸው ሽልማት፦
🥇 1ኛ ደረጃ፦ Pulse ID (የጤና ዘርፍ) — የ2018 የስታርትአፕ ዋንጫ 🏆፣ የወርቅ ሜዳሊያ እና 50,000 ብር።

🥈2ኛ ደረጃ፦ CozyCore (የጤና ዘርፍ) — የብር ሜዳሊያ እና 30,000 ብር።

🥉 3ኛ ደረጃ፦ Fresh Vault (የግብርና ዘርፍ) — የነሐስ ሜዳሊያ እና 20,000 ብር።

🎖 የማበረታቻ ተሸላሚዎች፦ Cognscia፣ Eco-Sentinel እና Opal Travellers — ለእያንዳንዳቸው 10,000 ብር ተበርክቶላቸዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ኢብሳ ዳሚና በተማሪዎቹ ብቃት መደሰታቸውን ገልጸው፣ የፈጠራ ሥራዎቻቸው ወደ ገበያ እንዲወጡ በቀጣይነት የሙያ እገዛ (Consult) ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውድድር፣ በቀጣይ በበለጠ ጥራት ተጠናክሮ የሚቀጥል የትምህርት ቤታችን ትልቅ መለያ ይሆናል።

ለተሸላሚዎችና ለተሳታፊ ተማሪዎቻችን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

የኢዘዲን ካሚል የአማና ትምህርት ቤት ጉብኝት | ግንቦት 6/2018 |አማና ታዋቂውን ወጣት ኢትዮጵያዊ የፈጠራ ባለሙያ እና ስራ ፈጣሪ ኢዘዲን ካሚልን እንግዳ በማድረግ "AI and The Fu...
14/05/2026

የኢዘዲን ካሚል የአማና ትምህርት ቤት ጉብኝት | ግንቦት 6/2018 |

አማና ታዋቂውን ወጣት ኢትዮጵያዊ የፈጠራ ባለሙያ እና ስራ ፈጣሪ ኢዘዲን ካሚልን እንግዳ በማድረግ "AI and The Future Generation" በሚል ርዕስ ለተማሪዎች ልዩ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አዘጋጅቷል።

በዕለቱ ኢዘዲን ካሚል ለተማሪዎች ባደረገው ንግግር፣ ከልጅነት የፈጠራ ህይወቱ አንስቶ እስከ አሁን የደረሰበት የፈጠራ እና የስራ ፈጠራ (Entrepreneurship) ጉዞው በዝርዝር አጋርቷል።

በተለይም የእናቱ ካፌ በመዘረፉ ምክንያት አንድ አሮጌ ሞባይል በመጠቀም የመጀመሪያውን የደህንነት ማንቂያ ደወል (Security Alarm) እንዴት እንደሰራ ያስታወሰው ታሪክ በተማሪዎች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።

"AI and The Future Generation" በሚለው ርዕስ ስር፣ ተማሪዎች AI ን እንዴት ለበጎ ተግባር እና ለፈጠራ ስራዎቻቸው መጠቀም እንዳለባቸው ገልጿል።

AI አሁን ላይ የእርሱን የፈጠራ ስራዎች ለማቀላጠፍ እና ምርታማነቱን ለመጨመር እንዴት እያገዘው እንደሚገኝ በተግባር አስረድቷል።

ቴክኖሎጂው ተማሪዎች በሳይንስ እና በፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ መሆኑን ጠቁሟል። ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም መክሯል።

ከቀረበው ገለፃ በኋላ ከተማሪዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ኢዘዲን ዝርዝር ምላሾችን ሰጥቷል።

የታላላቅ አእምሮዎች ፍልሚያ በአማና ሞዴል ት/ቤት!​በአማና በአዲስ መልኩ የተጀመሩት “Amana Maths Champion” እና “Amana Logic Master” ውድድሮች በተሳካ ሁኔታ በመካሄ...
10/05/2026

የታላላቅ አእምሮዎች ፍልሚያ በአማና ሞዴል ት/ቤት!

​በአማና በአዲስ መልኩ የተጀመሩት “Amana Maths Champion” እና “Amana Logic Master” ውድድሮች በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

​እነዚህ መድረኮች ተማሪዎች በሒሳብ፣ በሎጂክ፣ በፈጣን አስተሳሰብ እና በችግር ፈቺነት ክህሎት እርስ በርስ የሚወዳደሩባቸው ልዩ መድረኮች ናቸው።

ተማሪዎቻችን ሁለት ፈታኝ ዙሮችን በብቃት አጠናቀው፣ አሁን ወደ መጨረሻው እና ወሳኙ ምዕራፍ (Final Round) ተሸጋግረዋል!

​በየዓመቱ ከእያንዳንዱ የክፍል ደረጃ፦
➜ 1 Amana Maths Champion
➜ 1 Amana Logic Master
ተለይተው የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ይሆናሉ።

​ውድድሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርት ባሻገር የማሰብ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና ጠንካራ የፉክክር መንፈስ እንዲያዳብሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

#አማና

Address

Amana Model Secondary School, XQV4+HVV
Addis Ababa

Opening Hours

08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amana Model School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category