Solomon Hailu Tilahun/ሰለሞን ኃይሉ

Solomon Hailu Tilahun/ሰለሞን ኃይሉ አስተማሪ፣ ለውጥ አምጪ እና ሚዛናዊ ጉዳዮችን ማስተላለፍ እንዲሁም ጠቃሚ ሥራዎችን ማስተዋወቅ

24/10/2025

በፈተና ውስጥ ሆነንም ማበብን እንቀጥላለን!!!
ከተባለልን በላይ ለመሆንም እድል አለን!!!

ሁሌም ተስፋ ያላት አገር!!!
17/10/2025

ሁሌም ተስፋ ያላት አገር!!!

በተግዳሮት ውስጥም ሆና የምትታይ፣ የምትደምቅና የማትቆም አገር - ኢትዮጵያ

ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች አይኤምፍ ኢትዮጵያ የተሻለ እድገት ማስመዝገቧን እንደምትቀጥል የተነበየበት ነው ከታች ያለው ሰንጠረዥ

Better to be grateful!!!
አመስጋኝ መሆን ይሻላል!!!

09/10/2025
ተስፋችን ብሩህ ነው!!ፈተናችን በድል ይታለፋል!!መንገዳችን ይቀናል!!ድላችን ይበሰራል!!ኢትዮጵያ*******
02/10/2025

ተስፋችን ብሩህ ነው!!
ፈተናችን በድል ይታለፋል!!
መንገዳችን ይቀናል!!
ድላችን ይበሰራል!!
ኢትዮጵያ
*******

ከኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ባለፈBeyond generating electricity******************************** # የትውልዶች ምኞት እውን ሲሆን # የሺዎች ዓመታት ፈተና ...
09/09/2025

ከኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ባለፈ
Beyond generating electricity
********************************

# የትውልዶች ምኞት እውን ሲሆን
# የሺዎች ዓመታት ፈተና በድል ሲቋጭ
# እንችላለን ከራዕይ አልፎ እውነታ ሲሆን
# የአዲስ ምዕራፍ ንጋት ለአገር ሲበሰር
# የሃይል ሚዛን ቀያሪው ህልም ሲጨበጥ
# የኢትዮጵያ ከፍታ አይቀረነት ህያው ምልክት
# ለሌሎች ጨዋታ ቀያሪ አገራዊ ራዕዮች አቅም የሚሆን

የታላቁ ህዳሴ ግድብ በእኔ ዘመን መሳካቱ ከእድልም በላይ በረከት ነው!!!
@ ለመራችሁና ለተሳተፍን ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!!

# When the wishes of generations comes true
# When the challenge of thousands of years ends in victory
# When 'we can' go beyond vision and become reality
# When the dawn of a new chapter is announced for a country
# When the dream that changes the balance of power comes true
# A living symbol of Ethiopia's rising
# Potential for other game changing country visions

The success of the Grand Ethiopian Renaissance Dam during my lifetime is more than a privilege and it is a blessing!!!
@ Congratulations to all of you who led and to all of us who participated!!!

የታመነ ወዳጅ              ***********በአንድ ወቅት የአንድ አገር ንጉሥ አገሩን ከወረራ ለመከላከል ጦሩን መርቶ ወደ ውጊያ መሄድ ነበረበት። ታዲያ ንጉሡ ቆንጆ ሚስቱን (ንግሥቲ...
19/10/2024

የታመነ ወዳጅ
***********
በአንድ ወቅት የአንድ አገር ንጉሥ አገሩን ከወረራ ለመከላከል ጦሩን መርቶ ወደ ውጊያ መሄድ ነበረበት። ታዲያ ንጉሡ ቆንጆ ሚስቱን (ንግሥቲቱን) በግል ክፍላቸው ውስጥ ቆልፎባት በጣም ለሚቀርበው ጓደኛው ቁልፉን በመስጠት እንዲህ ይለዋል:- "በአራት ቀን ጊዜ ውስጥ ካልተመለስኩ ቁልፉን ትከፍታለህ ንግሥቲቱም ያንተ ትሆናለች" ። ይህን ብሎ ንጉሡ ፈረሱ ላይ ይወጣና ወደ ውጊያው አቅጣጫ መጋለብ ይጀምራል።

ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሡ ከበስተጀርባው በከፍተኛ ፍጥነት አቧራ እያስነሳ በፈረስ ወደርሱ የሚጋልብ ሰው መኖሩን ያስተውላል። በዚህ ጊዜ ቆም ብሎ ሲመለከት አደራ የሰጠው ጓደኛው ነበር። ከዚያም ንጉሡ በድንጋጤ "ምን ተፈጠረ?" ብሎ ይጠይቀዋል። የቅርብ የተባለው ጓደኛውም "የሰጠሄኝ ቁልፍ የተሳሳተ ነው" ብሎ ይመልስለታል።
ምን????

ልብ በሉ የቅርብ ጓደኛው ቁልፉን ለመሞከር ቢያንስ አራት ቀን እንኳን መታገስ አልቻለም።
(ካነበብኩት ሃሳብ የተወሰደ ነው)

በጣም ያመናቸው፣ በቅርባችን ያሉ፣ ምስጢራችንን የሚያውቁ፣ ጓዳችንን የከፈትንላቸው፣ በሃብታችን ላይ ሃላፊነት የሰጠናቸው በርግጥ እነማን ናቸው?

ምክሩ ባይጠቅምም አይጎዳም!!

16/09/2024

ስራ እንደዚህ በሚያምርና በሚስብ ማስታወቂያ ሲታጀብ ለቀጣይ ተግባር አቅም ይሆናል።

ምንጭ: አአ ከተማ አስተዳደር

30/08/2024

ለሰዎች እየወደቅህ ያለህ ቢመስላቸውም ••••
አንተ ግን ለዓላማህና ለግብህ እየተጋህ መሆንህን አሳያቸው!!!

ቢታውቁትም ይህን አስተማሪ ቪዲዮ ተመልከቱት

ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ውይይት እንደሚከተለው ቀርቧል። Stay blessed!!!
26/08/2024

ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ውይይት እንደሚከተለው ቀርቧል። Stay blessed!!!

GMM TV International : ጂ.ኤም.ኤም ( ዓለም አቀፍ የተአምራት አገልግሎት ) ቴሌቪዥንThe GMM TV International offers programs that are entertaining and educational, promoting a hea...

ከመታወቅ ይልቃል!!!******************የሰው ልጅ ተመራምሮ ሊደርስበት ከማይችላቸው ነገሮች አንዱና ውስብስቡ ጉዳይ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ዓለም እውነታ ቢሆ...
23/08/2024

ከመታወቅ ይልቃል!!!
******************

የሰው ልጅ ተመራምሮ ሊደርስበት ከማይችላቸው ነገሮች አንዱና ውስብስቡ ጉዳይ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ዓለም እውነታ ቢሆንም በፍጥረታዊ ዓለም አይመረመርም ደግሞም በሙላት አይታወቅም፡፡ ፍጥረት ስለ ፈጣሪው ማወቅ የሚችለው ፈጣሪው እንዲያውቀው የገለጠለትንና የፈቀደለትን ያህል ብቻ ነው፡፡ እኛም እግዚአብሔርን እና አሰራሩን ማወቅ የምንችለው በተገለጠልን መጠን ብቻ ነው፡፡

ከ"የመንፈሳዊ ስጦታ አጠቃቀም አሁናዊ ገጽታ በኢትዮጽያ" መጽሐፍ የተወሰደ

Address

Addis Ababa
2445

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Solomon Hailu Tilahun/ሰለሞን ኃይሉ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category