08/05/2026
በሊማ ከተማ ላይ ካሉ ሕንፃዎች አንዱ ላይ የተጫነ ካሜራ፣ ማንም ያልጠበቀውን ልብ የሚነካ ትዕይንት ቀረፀ…
በሕንፃው ጣሪያ ላይ በጣም የደከመች ግራጫ #ድመት፣ ከረሃብና ከድካም የተነሳ መንቀሰቀስ ተስኗት ተኝታ ነበር።
ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ፣ አንድ ቁራ በጣሪያው ጠርዝ ላይ አረፈ። በአፉም ትንሽ ቁራሽ ዳቦ ይዞ ነበር።
#ቁራ በተፈጥሮው ምግቡን ከሌላ ጋር አያካፍልም ምግቡን መብላት እና መብረር ነበረበት…
ግን ያ ቀን የሆነው ነገር ሰውን እንኳ የሚያስደንቅ ነበር…
ቁራው በቀስታ ወደ ድመቷ ቀረበ፣ የዳቦውን ቁራሽ ከፊቷ አሰቀመጠ። ከዚያም ትንሽ ወደ ኋላ ተመልሶ ጠበቃት
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ድመቷ በዝግታ መብላት ጀመረች።
ይህን የተመለከተ ቁራ በጣም እንደተራበች የተረዳ ይመስል በአንድ ሰዓት ውስጥ አራት ጊዜ እየተመላለሰ አዲስ ቁራሽ ዳቦ ይዞ ይመጣ ነበር።
በማግስቱ፣ አንዱ የሕንፃው ነዋሪ የካሜራውን ቅጂ አይቶ ወደ ጣሪያው ወጣ። ድመቷ በሕይወት ነበረች።
ከአጠገቧም ቁራው ቆሞ ነበር…
አሁን ድመቷ ወደ እንስሳት ሕክምና ክሊኒክ ተወስዳ ሕክምና እየተደረገላት ነው።
ከሁሉ የሚገርመው ግን… አሁንም ቁራው በየጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ ቁራሽ ዳቦ ይዞ ይመጣል።
♥
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦
وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم ۚ مَّا فَرَّطْنَا فِي الْكِتَابِ مِن شَيْءٍ ۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يُحْشَرُونَ
ከተንቀሳቃሽም በምድር (የሚኼድ)፤ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ፡፡
ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ ሰዎች
Hijra Tube ኢስላማዊ