Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association

Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association

Share

Ethiopian Private Higher education and TVETs' Institution Association is established on 16th Octo. 2

Photos from Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association 's post 10/06/2026

የመውጫ ፈተና #በድጋሚ ተፈታኝ የሆናችሁ (Re-sitters) የፈተና መግቢያ ትኬታችሁን https://verify.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት አውርዳችሁ ፕሪንት ማለት ይኖርባችኋል።
(ከታች በምስል የተያያዘውን ቅደም ተከተል በመጠበቅ ያውርዱ።)

02/06/2026


#ባሉበት፤

በunified መሶብ አማካኝነት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዝርዝር ገለጻና እና ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
ስለሆነም በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚደረገው ገለጻ እና ውይይት ላይ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ እና ሬጅስትራር ኃላፊ አርብ፣ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ሀላፊዎች ተወካይ መላክ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

30/05/2026

*የሬሜዲያል ፈተና ፕሮግራም*

የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል (አቅም ማሻሻያ) ፕሮግራም ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ለአምስት ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በተጠቀሱት ቀናት በሁለት ፈረቃ በጠዋት እና በከሰዓት መርሐግብር የሚሰጠው የሪሚዲያል ፕሮግራም (የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች) የፈተና መርሐግብር ከታች ተያይዟል።

Photos from Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association 's post 26/05/2026

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__________

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥራችሁ ጋር አስተሳሰራችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት እየተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችሁም ተመዛኞች ከግንቦት 20 – 26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

▪ ለብቃት ምዘና ፈተና የመፈተኛ ጣቢያ መምረጥ የምትችሉት ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች ብቻ ይሆናል፡፡

▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

▪ ለበለጠ ማብራሪያ ከስር የተያያዘውን ቪዲዮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

21/05/2026

ማስታወቂያ

የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የምሰጥባቸው ቀናት እንደምከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

21/05/2026

🔔 #አስቸኳይ

የፊታችን ሰኞ መሠጠት የሚጀምረውን የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ተከታዩን ሊንክ (https://verify.ethernet.edu.et/) ከተጫኑ በኋላ Remedial Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Start Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 17-20/2018 ዓ.ም እእንደሚሰጥ ይታወቃል።

Ministry of Education Ministry of Education | Exit Exam Verification

17/05/2026
Photos from Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association 's post 20/04/2026

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና የቴ/ሙ/ስልጠና ተቋማት ማህበር ቅዳሜ ሚያዝያ 10ቀን 2018 ዓ/ም ከማህበሩ አባላትና ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በመጡ የስራ ሐላፊዎች አማካኝነት የምክክር መድረክና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አከናውኗል።

በምክክር መድረኩ በግል ትምህርት ዘርፉ ያሉ ዓበይት ጉዳዮችና የሚታዩ ተግዳሮቶች በተመለከተ በማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋይ እንዲሁም የማህበሩ የ6 ወር ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

Photos from Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions Association 's post 14/11/2025

ማህበራችን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ አፈፃፀም ዙርያ ቁርጠኝነቱን ገለፀ።
ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም

የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ የትግበራ ማስጀመርያ ፕሮግራሙን ህዳር 4 ቀን 2018 /ም በስካይላይት ሆቴል አከናውኗል።
የማህበራችን ፕረዚደንት ሞላ ፀጋይ (ዶ/ር) በስትራቴጂክ ስነድ ዝግጅቱ ላይ የTVT Think Thank በም/ሰብሳቢነት የተሳተፉ እና ለስነዱ መዳበር ብዙ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሲሆን በማስጀመርያ መርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የማህበሩ አመራርና አባል ተቋማት አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ አፈጻጸም ያለውን ቁርጠኝነት ለውጤታማነቱም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልፀዋል።

Contact us on:

Telegram: https://t.me/ephetveta
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61558414384952

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/105426252/

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Bole Subcity Woreda 14 Gerji Unity University.
Addis Ababa
251