16/03/2026
የሜትር ታክሲ ድርጅቶች "የቴክኖሎጂ አውታር ወይንስ የገንዘብ መሰብሰቢያ?" ከአሽከርካሪዎች የቀረበ ከባድ ወቀሳ
በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ አብዮት የፈጠሩት የሜትር ታክሲ ድርጅቶች፣ በአሁኑ ወቅት በአሽከርካሪዎችና በባለንብረቶች ዘንድ "ቸልተኞች" የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው ነው። ድርጅቶቹ ከእያንዳንዱ ጉዞ ኮሚሽን ከመሰብሰብ ባለፈ፣ አሽከርካሪው በየመንገዱ ለሚገጥሙት መዋቅራዊ ችግሮች ድምጽ ለመሆን ፍቃደኛ አይደሉም የሚሉ ቅሬታዎች በዝርዝር እየቀረቡ ነው።
📍የመቆሚያና የመጫኛ ቦታ እጥረት
አሽከርካሪዎች ከሚያነሱት ዋነኛ ችግር አንዱ ተሳፋሪ ለመጫንና ለማውረድ፣ እንዲሁም ትዕዛዝ እስኪመጣ ቆመው የሚጠብቁበት ቦታ አለመኖሩ ነው።
ድርጅቶቹ በሺዎች የሚቆጠሩ መኪኖችን ወደ ስራ ቢያሰማሩም፣ እነዚህ መኪኖች የት ቆመው ትዕዛዝ እንደሚጠብቁ ከአስተዳደሩ ጋር ተነጋግረው መፍትሄ አላመጡም።
ተሳፋሪ ለመጫን ለአፍታ የቆመ አሽከርካሪ በትራፊክ ፖሊሶች "ህገ-ወጥ ማቆም" ተብሎ ለከፍተኛ ቅጣት ይዳረጋል። ድርጅቶቹ ግን ይህንን የአሰራር ችግር ለመፍታት ከመንግስት ጋር ድርድር ሲያደርጉ አይታዩም።
📍የበዙ ቅጣቶችና የአሽከርካሪው መከላከል አቅም ማጣት
በአሁኑ ወቅት የትራፊክ ቅጣቶች ከመጠን በላይ መጨመራቸው ይታወቃል። አሽከርካሪዎች እንደሚሉት፦
"ተሳፋሪው በፈለገበት ቦታ ቁም ይላል፤ እምቢ ካልን መጥፎ ደረጃ (Rating) ይሰጡናል። ከቆምን ደግሞ ፖሊስ ይቀጣናል።"
ድርጅቶቹ አሽከርካሪዎቻቸው በስራ ላይ እያሉ ለሚገጥማቸው አድሏዊ ቅጣት የህግ ከለላ ወይም ድምጽ የመሆን ዝንባሌ የላቸውም።
📍"የሚቆጥረው አይቆጥርም" የቴክኖሎጂ ስህተቶችና የታሪፍ ኢ-ፍትሃዊነት
ሌላው አሳሳቢ ቅሬታ በድርጅቶቹ መተግበሪያ (App) ላይ የሚታየው የርቀትና የዋጋ ስሌት አለመጣጣም ነው።
መተግበሪያዎቹ ብዙ ጊዜ የሚሰላው በኪሎሜትር እንጂ በትራፊክ መጨናነቅ ውስጥ ለሚባክነው ጊዜ እና ርቀት ተገቢውን ክፍያ አያካትቱም።
"አፕሊኬሽኑ የሚቆጥረው ርቀትና መኪናው በትክክል የሄደበት ርቀት አይጣጣምም፤ በዚህም የተነሳ አሽከርካሪው የሚገባውን ክፍያ አያገኝም" ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ።
📍የታክስ ጫና እና የኮሚሽን ግትርነት
የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው ቢጨምርም፣ ድርጅቶቹ የሚወስዱት የኮሚሽን መቶኛ ግን ዝቅ እንዲል አይደረግም።
ባለንብረቶች እንደሚሉት ድርጅቶቹ ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ለአሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ወይም የቀለለ የታክስ ስርዓት እንዲዘረጋ ግፊት ማድረግ ሲገባቸው፣ ትኩረታቸው ኮሚሽን መሰብሰብ ላይ ብቻ ሆኗል።
📍ማጠቃለያ
አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ድርጅቶቹን "ፕላትፎርሙን ብቻ ዘርግቶ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ ለአሽከርካሪው መብትና ለስራው ምቹ ሁኔታ መፈጠር ግድ የማይላቸው ከሆነ፣ ዘርፉ ወደ ቀውስ ሊያመራ ይችላል" ሲሉ የዘርፉ ተዋንያን ያስጠነቅቃሉ።
01/03/2026
መኪና ሲሸጥ በሀገራችን ገበያው የሚመራው ስለመኪና እውቀት በሌላቸው ደላሎች ነው የሚመራው ለምን?
መግዛት ሲፈልጉ ያማክሩን ሀሳቦን እንጋራለን ያለንን እውቀት እናካፍላለን
04/06/2025
Checking-in on the 2025/26 table for the very first time 👀
02/05/2022
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን 1443ኛው ኢድ-አልፈጥር በዓል
በሠላም አደረሳችሁ!
SAMI automotive
25/04/2022
አውቶሜትድ ትራንስሚሽን
አውቶሜትድ ግር ቦክስ ያላቸው ትሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ማኑዋል ሆነው ነገር ግን ማርሹን ለመቀየር የሚረዳ ተጨማሪ አክችወተር በመጠጠቀም ከ ክላች ጋር ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠተር የሚረዳ ኮሚፒውተር ጋር የተገናኜ ሲስተም አለዉ ይሔም የሚሰራው በኤሌክትሪክ ሞተር,በሀይድሮሊክ ስይስተም እና በንፋስ የሚሴራ ነው ከመሆኑም ባሻገር የተልያዩ ሴንሰሮች አሉት።አውቶሜትድ ግር ቦክስ ልክ እንደ አዉቶማቲክ ትራንስሚሽን ፍሪስዮን አይኖረውም ስለዚህ በሾፈሩ ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል በተጨማሪም ጥሩ የነዳጅ ፍጆታ እንዲኖረን ያደርጋል።
25/04/2022
አውቶማቲክ ማርሽ ላይ ምልክቶች እና ጥቅማቸው።
አውቶማቲክ ማርሽ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገራችን እየጨመሩ መምጣታቸውና እንዲሁም በከባድ ተሽከርካሪዎች አሁን ላይ የምናገኛቸው ናቸው ለ አብነትም የከተማችን የህዝብ ማመላለሻ የሆኑ ተሽከርካሪዎች አንበሳ እና ሸገር የከተማ አውቶብሶች ላይ የምናገኘው ነው።
ውድ የዚህ ገጽ ተከታታዮች አውቶማቲክ ማርሽ ላይ እንደተሽከርካሪዉ ሞደል 1,2,3,D,N,R,P ባንዳንዳንዶቹ ደግሞ L,1,D,N,R,P እንደ ተሽከርካሪዉ ሞደል እና ካምፓኒ ከነዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ምልክቶች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን የነዚህን ጥቅም እና የተኛዉን በምን ግዜ እንጠቀማለን የሚለዉን በትክክል አውቆ መጠቀምና ተግባራዊ ማድረግ ነው በሃገራችን ያሉ አብዛኛው አሽከርካሪ ማለት በሚቻል መልኩ የሚጠቀሙት ወይም የሚያሽከርክሩት D ላይ ብቻ በማድረግ ነው ይህም ለአውቶማቲክ ማርሽ ካለው የንዛቤ እጥረት ይመስለኛል በማንዋል ተሽከርካሪ የሚገረጉ ጥንቃቄዎች በሙሉ በአውቶማቲክ ተሽከርካሪዎችም መደረግ አለበት ለምሳለ ቁልቁለት የሚወርድ ተሽከርካሪ በተልይ የጫነ ተሽከርካሪ በከባድ ማርሽ መውረድ እንዳለበት ይታወቃል ይህ በተመሳሳይ አውቶማቲክ ማርሽ ያላቸው ተሽከርካሪዎችም መደረግ አለበጥ. Automatic ላይ ከባድ የምንላቸዉ ማርሾች የምንላቸው L,1,2 ናቸው ነገር ግን አብዛኛው አሽከርካሪ ይህን ሲጠቀሙ አይታይም ቁልቁለት ሲሆን ከባድ ማርሽ ላይ ካልሆነ የተሽከርካሪው ፍሬን ላይ ጫና ያደርሳል በማርሽ አስረን መውረዳችን ፍሬናችንም ያግዛል ከዚህም ባሻገር በከተማ ውስጥ ስናሽከረክር የትራፍክ መጨናነቅ የበዛበት ቦታ ላይ ስናሽከረክር L,1,2 ብንጠቀም ይመረጣል ይህ ማለት ተሽከርካሪው የሚጉዋዘው ለ ትራፍክ ፍሰቱ በሚመጥን ፍጥነት ነው ይህ ማለት 1,2ኛ ማርሽ ብቻ ይሆናል ማለት ነው ስለዚህ አስፈላጊውን ማርሽ በተለይ ጭነት የጫነ ቁልቁለትና ዳገት የሚወጣ አውቶማቲክ ማርሽ ያላችሁ አሽከርካሪዎች አስፈላጊው ማርሽ በተገቢው ቦታ መጥቀም አለብን እያልኩ በአውቶማቲክ ማርሽ ላይ የምታዩትን ያልገባችሁ ነገር ካለ inbox በቂ ማብራሪያ የምሰጣችሁ ይሆናል አመሰኛለሁ።