Make Ethiopia Great Again

Make Ethiopia Great Again

Share

Ethiopian

27/10/2025

ለፈገግታ

አንዱ ሰውዬ ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ ያለቅሳል

ይህንን የተመለከተ አንድ ሰው ወደ እርሱ ይመጣና "ለምንድነው የምታለቅሰው?" ይለዋል

ሰውዬውም " አንድ ማንኪያ ሙሉ ስኳር እዚህ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ የወንዙን ውሃ ብቀምሰው ምንም አይጣፍጥም"ሲለው

፡ ሌላኛው ሰውዬ ሳቁን ይለቀዋል፡፡

ሰውዬው----"ምን ሆነህ ነው የምትስቀው?"ይለዋል

" " " " " " " "
አንተ ጅል! መጀመሪያ አታማስለውም ነበር ብሎ ቁጭ@ሼርካሜትሲያደርጉአዳዲስፓስታችበፍጥነትይደርሳቲል

27/10/2025

ከእናቱ ጋር ፊልም ሲያይ የቆየው ልጅ ወደ እናቱ ዞር ብሎ ''እናቴ አኔ ሳድግ እንደ አክተሩ 7 ሚስት ነው ማገባው" አላት እተተኮላተፈ።

እናት ፈገግ ብላ "ምን ያረጉልሀል ሰባት ምታገባው አንድ አይበቃህም? አለችው።

አይ እናቴ ሰባት ነው ማገባው።

የመጀመሪያዋ ምግብ ታበስልልኛለች፣ ሁለተኛዋ ልብሴን ታጥብልኛለች...እያለ ሲዘረዝር እናት ግራ ተጋብታ "ታድያ የትኛዋ ናት አብራህ የምትተኛው?' አለችው።

ልጁም ወዲያው ያለምንም ማንገራገር "የምተኛውማ ካንቺ ጋር ነው ከእናቴ ጋ" አላት 😍

እናት ደስ አላት የኔ ልጅ እያለች እቅፍ አርጋ ሳመችውና ታዲያ ሚስቶችህ ከማን ጋር ሊተኙ ነው? አለችው በስስት እያየችው።

እነሱማ ከአባቴ ጋር ይተኛሉዋ! አላት

ስራ ይዞ ወሬውን ሲከታተል የነበረው አባት ደሞ ብድግ ብሎ ልጁን አቀፈውና ተባረክ ልጄ ብሩክ ሁን ያሰብከው ይሳካልህ እያለ መረቀው ...🤪😂😂😂

© ከ fb መንደር 😍 #ሼርርርር

12/06/2025

If there is no peace, there is no tourism.

31/05/2025
21/05/2025

እናት ሀገር ዝምባዋብዌ አብይንም ...

07/05/2025

ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ ህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ ተጀመረ - የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን ስራ ፈጣሪ አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና "ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" የተባለ ኩባንያን ጨምሮ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን ለህዝብ በመሸጥ ገንዘብ ሲያሰባስቡ በነበሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በሰጠው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ህገወጥ የሰነድ ሽያጭን በመጠቀም ከህዝብ ገንዘብ በማሰባሰብ ተግባር ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በተለይም በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና በ"ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" ኩባንያ ላይ እየተካሄዱ ያሉት ምርመራዎች በህገ መንግስት የተረጋገጠ የመሰማት እና የመከላከል ሙሉ መብታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እንደሚከናወኑ ባለስልጣኑ አረጋግጧል።

በተጨማሪም ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ከካፒታል ገበያ ጋር በተያያዙ እንቅስቃሴዎች ላይ ሲሳተፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተለይም በንግድ ድርጅቶች ምስረታ ላይ ሲሳተፉ የንግድ ምዝገባ እና ምስረታ ሰነዶችን ከሚመለከተው አካል እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ገንዘብ ከመክፈላቸው በፊት በባለስልጣኑ ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ብቻ ምክር እንዲፈልጉ ጠቁሟል።

ባለስልጣኑ ፈቃድ ሳይኖራቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ ወይም ለማቅረብ የሚሞክሩ አካላት ካሉ ለባለስልጣኑ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል።
Via Capital Newspaper

03/05/2025

የማድቤት (የወጥ ቤት) ጠቃሚ ምክሮችና ዘዴዎች

1. ስልክ ውኃ ውስጥ ሲወድቅ... ባልበሰለ (ጥሬ) ሩዝ ውስጥ ይክተቱት። ሩዙ ውኃውን የመምጠጥ ባህሪ አለው።

2. ልብስዎ ላይ የብዕር ቀለም ከነካው፣ ለማጥፋት ነጭ የኮልጌት የጥርስ ሳሙና ወይም ሰርጂካል ስፕሪት (አልኮል) ይጠቀሙ።

3. የልብስ ካውያ ጥቁር እድፍ ከያዘ (ካረረ)፣ ካውያው ትኩስ እያለ የተሰባበረ ጠመኔ ወይም የተፈጨ ፓናዶል በማሸት ጥቁር ነገሩን ማስለቀቅ ይችላሉ።

4. ሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡
* ለቁስል የመጀመሪያ እርዳታ - የደም መፍሰስን ያቆማል።
* ለሚያመረቅዝ ቁስል - ኢንፌክሽንን ለመግታት ይረዳል።
* የአፍ መጉመጥመጫ - ከውኃ ጋር በመቀላቀል ፀረ-ባክቴሪያ የአፍ መጉመጥመጫ ማድረግ ይቻላል።
* ነጭ ልብሶችን ለማንጣት (እንደ ክሎሪን) ያገለግላል።

5. የፍሪጅን የምግብ ሽታ ለማስወገድ፣ ሎሚ አፍልተው ውኃውን ፍሪጅ ውስጥ ያስቀምጡ። ከሰል ማስቀመጥም ሽታውን ለመምጠጥ ይረዳል።

6. ቤኪንግ ሶዳ (Baking soda):
* የሸክላ ንጣፎችን (ታይልስ) ቆሻሻ ለማጽዳት - የማድቤት እቃ ማጠቢያ ገንዳን/ንጣፎችን በቤኪንግ ሶዳ እና በሆምጣጤ (ቬኒገር) ልጥፍ ይሹ ።
* ያረረ ምግብ ከድስት ላይ ለማስለቀቅ - ድስቱን በቤኪንግ ሶዳ እና ውኃ ድብልቅ ውስጥ ለ15 ደቂቃ ያህል ይዘፍዝፉ፤ ምግቡ በቀላሉ ይለቃል።
* ለጨጓራ አሲድ መብዛት - ቤኪንግ ሶዳ ከውኃ ጋር ቀላቅለው ይጠጡ።
* የጥርስ ሳሙና ካለቀብዎ፣ በቤኪንግ ሶዳ ጥርስዎን ማጽዳት ይችላሉ።

7. ልብስዎ ላይ ማስቲካ ከተያያዘ፣ በያዘው ቦታ ላይ በበረዶ ይሹት፤ ማስቲካው ይላቀቃል። ሌላው ዘዴ ደግሞ ማስቲካው ላይ ኬሮሲን በማፍሰስ ማስለቀቅና ከዚያም ልብሱን ማጠብ ነው።

8. ልብስዎ ላይ የሻማ ሰም ከፈሰሰ፣ ልብሱን በጋዜጣ ይሸፍኑና በጋዜጣው ላይ በካውያ ይተኩሱ። ሰሙ ቀልጦ ጋዜጣው ይመጠዋል። ሌላው አማራጭ ልብሱን ፍሪዘር ውስጥ ማስገባት ነው፤ ሰሙ በቅዝቃዜው ደርቆ ይሰበራል።

9. ማይክሮዌቭ ምድጃን ለማጽዳት፡ 1/4 (ሩብ) ሲኒ ሆምጣጤን ከአንድ ሲኒ ውኃ ጋር በመቀላቀል በመስታወት ሳህን ውስጥ አድርገው ማይክሮዌቩ ውስጥ ያስገቡ። ማይክሮዌቩን በከፍተኛው ሙቀት መጠን ላይ አድርገው ለአምስት ደቂቃ ያብሩት። ሳህኑ ከቀዘቀዘ በኋላ፣ በውኃው ውስጥ ጨርቅ ወይም ስፖንጅ ነክረው የውስጠኛውን ክፍል ለማጽዳት ይጠቀሙ።

10. የልብስዎ ቀለም እንዳይለቅ ለማድረግ፣ በሚያለቀልቁበት ውኃ ውስጥ ጥቂት ነጭ ሆምጣጤ ይጨምሩ። ልብሱ በፍጹም፣ በፍጹም ቀለም መልቀቁን ያቆማል!!!

11. ቆሻሻ የያዘ ፔርሙዝን ለማጽዳት፡ በሙቅ ውኃ እና በ1/4 (ሩብ) ሲኒ ሆምጣጤ ይሙሉት፣ ጥቂት ጥሬ ሩዝ ይጨምሩበት፣ ይክደኑትና በደንብ ያለቅልቁት። ከዚያም በደንብ አጥበው አየር ላይ እንዲደርቅ ያድርጉት። እንደ አማራጭ፣ እንደ ኦሞ ባለ ሳሙና ውኃ ውስጥ ዘፍዝፈው ማጽዳት ይችላሉ።

12. ቆሻሻ የያዘ የኤሌክትሪክ ማንቆርቆሪያን ለማጽዳት፣ ውኃ ውስጥ ትንሽ ሲትሪክ አሲድ (citric acid) ጨምረው ያፍሉት።

13. ሻማ ቶሎ ቀልጦ እንዳያልቅ ለመከላከል፣ ሲበራ ትንሽ ጨው በላዩ ላይ ይነስንሱበት።

14. ምግብዎ ላይ ጨው ከበዛ፣ አንድ ወይም ሁለት ጥሬ ድንች ከትተው አብረው ለጥቂት ጊዜ ያብስሉት። ድንቹ ጨዉን ይመጣል። ከዚያም ድንቹን አውጥተው መጣል ይችላሉ።

15. ባቄላ በሚቀቅሉ ጊዜ ሙሉ ካሮት አንድ ላይ ይጨምሩ፤ ይህም ጋዝን ለመቀነ

03/04/2025


የሲዳማ ክልል ፕሬዘዳንት ከአገር ሸሽተው እንዳያመልጡ ለአገሪቷ ኢሚግሬሽን ትእዛዝ ተሰጠ።
በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌደራሉ መንግስት ግምገማ ላይ ያሉት አቶ ደስታ ሌዳሞ ምርመረቻው ተጣርቶ ሲጠናቀቅ በክልሉ አዲስ የአመራር ሹም ሽር ይካሄዳል ተብሏል።
አርቲስት ቶክቻው ለሲዳማ ህዝብ በመቆርቆር ያደረገው ትግል የሚደነቅና የሚያስመሰግነው ነው።

ለሆድ ከመኖር ይልቅ ለህዝብ መታገል እንደሚያስከብር አንዳንድ የኦሮሞ አርቲስቶች ከአርቲስት ቶክቻው ሊማሩ ይገባል!

Photos from ጉርሻ page's post 12/03/2025
12/03/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Daniel Desalegn, Akbal Muhammed

07/03/2025

በኢትዮጲያ የአዞ ስጋ ሽያጭ ሊጀመር ነው ፡

የአዞ ስጋን የሚያዘጋጅ እና የሚሸጥ ምግብ ቤት በአርባምንጭ ሊከፈት ነው

የአርባምንጭ አዞ እርባታ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዳኜ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በሰጡት ማብራሪያ፤ በአርባምንጭ ከተማ የአዞ ስጋ ምግብ ቤት ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።

የውጪ ሃገር ቱሪስቶች የአዞ ስጋ ለመመገብ የሚጠይቁ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳዊት፤ ጥናት ተደርጎ ከአንድ ዓመት በኋላ ሬስቶራንቱን ለመክፈት እንደታሰበም ተናግረዋል።

የውጭዎቹ ቱሪስቶች ጋር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ዳዊት አንስተው ፤ አሁን ላይ በሃሳብ ደረጃ ነው ያለው ጉዳዩ ወደተግባር አልተገባም ብለዋል፡፡

በአካባቢው አዞዎቹን የሚንከባከቡ ሰዎች የአዞ ስጋ እንደሚመገቡ የሚናገሩት አቶ ዳዊት ይህም በስፋት እንደተለመደ እና አዲስ ነገር እንዳለሆነ አስተውሰዋል፡፡

የአዞ ስጋ በጣም ጣፋጭ እና መድሃኒትም መሆኑንን በጥናት አረጋግጠናል እናም በቅርቡም የአዞ ስጋ ሽያጭ በይፋ እንደሚጀመርም ገልጸዋል፡፡

2ሺ5መቶ ኦዞዎች እንዳሏቸው እና አሁንም ሰፋ ባለ መልኩ እየተፈለፈሉ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Addis Ababa