21/08/2026
ልቀት ኮሌጅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የውል ስምምነት ተፈራረመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች (ባለድርሻ አካላት) ጋር በትስስርና በትብብር መስራት በሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ያተኮረ የውል ስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።
ይህ ስምምነት የከተማዋን ባህላዊና ኪነ-ጥበባዊ እሴቶች የበለጠ ለማሳደግ፣ የፈጠራ ዘርፉን ለማጠናከር እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የቢሮው አመራሮችና የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ተወካዮች እንደገለጹት፤ የተደረገው ስምምነት ወደ ተግባር ተሸጋግሮ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።