Fluent Language Center

Fluent Language Center Fluent Learning Solutions PLC

Phone number: 0786 28-42-90

MLS is a school teaching English for all levels of language proficiency from beginners to advanced and from kids to adults.

Fluent Language Center‘Our language is our world’ The Best inTeaching English PronunciationandTraining Speaking and Writ...
24/07/2026

Fluent Language Center
‘Our language is our world’

The Best in
Teaching English Pronunciation
and
Training Speaking and Writing Skills

በዕድሜና በቋንቋ ችሎታ ደረጃ ለይተን
በግልና በቡድን
በአካልና በኦንላይን እናሰለጥናለን!

ቃሊቲ፣ ማሰልጠኛ፣ ዴልታ ከምፕሌክስ
0786284290 / 0910284290

11/07/2026

TESTIMONY

የአዋቂዎች ኦንላይን
11/07/2026

የአዋቂዎች ኦንላይን

09/07/2026

ከምስጋና ሌላ የምሰጣችሁ ነገር የለኝም!!!

የኛ ሰው አስተዋይና ለልጆቹ የሚጠቅመውን ትክክለኛ የእንግሊዝኛ ስልጠና መምረጥ እንደሚችል ያረጋገጥሁት ሌሎቹ ገና ለክረምት ፕሮግራም ተመዝጋቢ አጥተው ማስታወቂያ እየሰሩ ባለበት በዚህ ሰዓት የኛ ማዕከል ሰልጣኞችን መቀበል በሚችልበት ሙሉ አቅም ተማሪዎቹን መዝግቦ መጨረሱን ሳይ ነው፡፡

ወላጆች ስላመናችሁብንና ልጆቻችሁን ስለሰጣችሁን እያመሰገንን እኛም ኃላፊነታችንን ተወጥተን ልጆቻችሁን ለውጠን ለማስረከብ ቃል እንገባለን!!!

ሁሉን ካደረገ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ምስጋናዬ ለእናንተ ይድረስ!!!

ሰኔ 29ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን የቻሉ ወላጆችና ዕድለኛ ተማሪዎች እኛን ተቀላቅለዋል!!የክረምት ስልጣናችን በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተጀመረ!ማዕከላችን በይዘትም በአቀራረብም በተለየ መንገድ ነው...
06/07/2026

ሰኔ 29

ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን የቻሉ ወላጆችና ዕድለኛ ተማሪዎች እኛን ተቀላቅለዋል!!

የክረምት ስልጣናችን በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተጀመረ!

ማዕከላችን በይዘትም በአቀራረብም በተለየ መንገድ ነው ያሰለጥናል!!!

05/07/2026

ምክር ለወጣት እንግሊዝኛ መምህራን!!!

አሁን የምታስተምሩበት ትምህርት ቤት እና አሁን የምታገኙት ገቢ ለእንተ የሚገባችሁ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ በወጣትነታችሁ ይህን ነገር ለመቀየር የማትሰሩ ከሆነ አሁን ካላችሁበት ደረጃ ንቅንቅ ሳትሉ እንደምታረጁ አትጠራጠሩ፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ እንዴት አድርጌ ነው ይህን ነገር የምለውጠው የሚል ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኔን ዕውቀትና ልምድ ላካፍላችሁ!

የመጀመሪያው የቤት ስራችሁ ሁለትም ይሁን ሦስት ዓመት ይፍጅባችሁ ጊዜ ወስዳችሁ የራሳችሁን የእንግሊዝኛ ክህሎቶች በትክክል መጠቀም በሚያስችል ደረጃ ለመገንባት ስሩ፤ በተለይ የመናገርና የመፃፍ ክህሎታችሁ ላይ ትኩረት ሰጥታችሁ ስሩና እናንተም በኩራት የምትጠቀሙበት ለሌሎችም ማሰልጠን የምትችሉት ትክክለኛ ክህሎት ገንቡ፡፡ ይህን በማድረግ ሂደት ጥንቅቅ ያለ ክህሎት እስክትገነቡ ሳትጠብቁ አጠገባችሁ ያሉ የእናንተን ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን እያገዛችሁ እያስተማራችሁ ተማሩ፤ እያሰለጥናችሁ ሰልጥኑ፡፡ ያኔ ክህሎታችሁ በተግባር የተፈተነ እና በልምድ የዳበረ ይሆናል፡፡

ቀጥሎ ደግሞ ጊዜ የለኝም፣ ድካሙስ የሚል የሰነፍ ሰበባችሁን ወደጎን አድርጉና ከመደበኛ ስራችሁ ውጭ ያለውን ጊዜ አሁን ወጣት እያላችሁ ድካማችሁን ተቋቁማችሁ በአካባቢያችሁ ያሉ ተማሪዎችን በማገዝ እራችሁንም ማሕበረሰባችሁንም የምትጠቅሙ ሁኑ፡፡ ይህን በምታደርጉ ጊዜ ለምትሰጡት አገልግሎት ለዕውቀታችሁ፣ ለጊዜያችሁና ለጉልበታችሁ የሚመጥን የማሕበረሰባችሁን አቅም ያገናዘበ ክፍያ ማስከፈል ጀምሩ፡፡ ይህን ማድረጋችሁ በዕውቀት፣ በክህሎትና በገቢ አቅም እያደጋችሁ እንድትሄዱና ስራችሁን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንድታሳድጉ ብርታት ይሰጣችኋል፡፡

እንደዚህ እየተሻሻላችሁ ስትሄዱ ሙሉ ለሙሉ እራሳችሁን ለመቻል ሽግግር ልታደርጉ ስትሉ ቋሚ ስራችሁን ትታችሁ ወደማያስተማምን ነገር የምትሄዱት ምን አቅብጡዋችሁ ነው የሚል ሙግት ከራሳችሁም ከምታውቋቸው ሰዎችም ይጠብቃችኋል፡፡ ለዚህም የኔን ዕይታ ላካፍላችሁ በመጀመሪያ ቋሚ የሚባል ነገር የለም! ቀጥሎ ሁሉም ነገር አንፃራዊ ነው! አሁን የምንወስነውን ውሳኔ የምንወስነው አሁን ባለን ዕውቀትና ልምድ ልክ ነው፡፡ ዕውቀታችንና ልምዳችን ሲጨምር ውሳኔያችንም አብሮ ይቀየራል፡፡ አሁን የሚከፈላችሁን ቋሚ ደመወዝ ሁለትና ሦስት እጥፍ በትርፍ ሰዓታችሁ እየሰራችሁ ማግኘት ከቻላችሁ የሙሉ ሰዓት ስራ አድርጋችሁ ብትሰሩት ምንድነው ሊፈጠር የሚችለው? ዓላማችሁ የጡረታ መብታችሁን ማስከበር ከሆነ እናንተ አቅም ፍጠሩና የራሳችሁን ተቋም ገንቡ እንጅ የራሳችው ተቋም ስራ አስኪያጅ ሆናችሁ በግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው እንደሚሰሩ ሰራተኞች የጡረታ መብታችሁን ማስከበር ትችላላችሁ፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የስጋት ጥያቄ ይሄ ሁሉ ባይሳካና እናንተ እንዳሰባችሁት ባይሆንስ ነው? አይገርማችሁም ምንም አይፈጠርም! የተሻለ ዕውቀትና ክህሎት ስላላችሁ በሙያችሁ የትም ተወዳድራችሁ የማሸነፍ አቅም ሲለሚኖራችሁ ወደተቀጣሪነት መመለስ ብትፈልጉ እጃችሁን ተስማችሁ የምትቀጠሩ በባትሪ ተፈልጋችሁ የምትገኙ ባለሙያ ሆናችሁ ነው የሚደመደመው፡፡

እንዴት ልጀምር ካላችሁ ከላይ በነገርኋችሁ መሰረት እራሳችሁን ገንቡ፡፡ ከዛ ያላችሁን ዕውቀትና ክህሎት ለሰዎች በማካፈል ሙያችሁን በደንብ ማስተዋወቅና መሸጥ ጀምሩ፡፡ ያኔ ሰዎች ወደናንተ መምጣት ይጀምራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ 900,000 ገደማ መምህራን ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በጣም በተጋነነ ስሌት ከጠቅላላ መምህራን 20% ወይም 180,000 እንግሊዝኛ መምህራን ናቸው ብንል በጣም በትንሹ ከ120,000,000 ሕዝብ ውስጥ 667 ሰዎች የእናነተን ድጋፍ ፈልገው እየጠበቋችሁ ነው ማለት ነው፡፡

እና ምን ትጠብቃላችሁ?

03/07/2026
02/07/2026

እንግሊዝኛ ስንማርም ሆነ ስናስተምር ሰዋሰው (Grammar) እና አውዳዊ ትርጉምን (Pragmatics) ብቻ መማር ወይም ማስተማር መሰረት የሌለው ቤት ላይ ግድግዳና ጣራ ለማቆም እንደመድከም ነው!

አንድ ቋንቋ ስድስት ዋና ዋና አምዶች ያሉት ሲሆን፣ ቋንቋውን በጥልቀት ለመረዳትና ለመጠቀም እነዚህን መዋቅሮች ደረጃ በደረጃ መገንባት ያስፈልጋል። ለግንዛቤ እንዲሆናችሁ የእያንዳንዱን አምድ ትርጉምና ጥቅም እንደሚከተለው በዝርዝር አብራራላችኋለሁ፡-

Phonetics /fəˈnetɪks/ፈኔድክስ / ድምፅ-ልሳን

ትርጉም፡ አንድን ቋንቋ በምንናገርበት ጊዜ የሚፈጠሩትን የንግግር ድምፆች (Speech Sounds) አካላዊ ባህሪ የሚያጠና ክፍል ነው። ድምፆቹ በአፍ፣ በጉሮሮና በሳንባ ጥምረት እንዴት እንደሚፈጠሩ፣ በነፋስ አማካኝነት በአየር ላይ እንዴት እንደሚጓዙና ወደአድማጩ ጆሮ እንዴት ዘልቀው እንደሚገቡ የምናጠናበት የመጀመሪያው አምድ ነው።
አገልግሎት (ጥቅም)
አንድን አዲስ ቋንቋ ስንማር ድምፆችን በትክክል እንዴት ማውጣት (pronounce) ማድረግ እንደምንችል ለመለማመድ ይጠቅማል
በቋንቋው ውስጥ ያሉትን ትርጉም ለዋጭ መሰረታዊ ድምፆች (Phonemes) ለይቶ ለማወቅ ይጠቅማል
የንግግር እክል ያለባቸውን ሰዎች ለመርዳት (Speech Therapy) ለመስጠት ይጠቅማል
የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የሰውን ድምፅ ለይቶ እንዲያውቅ (Voice Recognition) ለማድረግ ይጠቅማል

Phonology /fəˈnɑːlədʒi/ፈናለጂ / ስርአተ-ድምፅ

ትርጉም፡ በአንድ ቋንቋ ውስጥ የድምፆችን ህግና ስርዓት የሚያጠና ክፍል ነው። ድምፅ-ልሳን (Phonetics) የአንድን ቋንቋ ተናጠል ድምፆች የሚያጠና ሲሆን፣ ስርአተ-ድምፅ (Phonology) ግን በአንድ ቋንቋ ውስጥ ድምፆች ምን አይነት ሚና እንዳላቸውና ድምፆች ተጣምረው እንዴት ቃል እንደሚፈጥሩ (ለምሳሌ፡ በአማርኛ "ፕ" እና "ር" ተከታትለው ሊመጡ ይችላሉ፣ ፕሬዚዳንት (P-re-zi-da-nt) እዚህ ቃል ላይ "ፕ" እና "ር" በመካከላቸው ምንም አናባቢ ሳይገባ "ፕሬ" በሚለው ቤት ውስጥ ተከታትለው መጥተዋል። ነገር ግን "ኝ" በቃል መጀመሪያ ላይ አይመጣም የሚሉትን ህጎች) ያጠናል።

አገልግሎት (ጥቅም)
የቋንቋውን የፊደልና የፅህፈት ስርዓት (Orthography) ለመቅረፅ ይጠቅማል
በቋንቋው ውስጥ ያሉትን ትርጉም ሊለውጡ የሚችሉ ተለዋጭ ድምፆች (Allophones) አንድ ድምፅ ከሌላ ድምፅ የሚያደርገውን ቅንብር (Phonotactic Process) ለይቶ ለማወቅ ይጠቅማል


Morphology /mɔːrˈfɑːlədʒi/ሞርፋለጂ / የቃል ምስረታ

ትርጉም፡ ቃላት እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚገነቡ የሚያጠና ክፍል ነው። ትርጉም ያላቸው ትንንሽ የቃል ክፍሎችን (Morphemes) ያጠናል። ለምሳሌ "ቤቶች" የሚለው ቃል "ቤት" (ዋና ቃል) እና "ኦች" (የብዙ ቁጥር ማሳያ) ከሚሉ ሁለት ክፍሎች መገንባቱን ያስተምረናል።

አገልግሎት (ጥቅም)፦
በቋንቋው ውስጥ አዳዲስ ቃላት እንዴት እንደሚፈጠሩ ለመረዳት ይጠቅማል
መዝገበ-ቃላት (Dictionary) ለማዘጋጀትና በቃላት ውስጥ ስርዎ ቃሉን (stem) ቅድመና ድህረ ቅጥያዎችን (Prefix/Suffix) ለመለየት ይጠቅማል

Syntax /ˈsɪntæks/ስንቲአክስ / ሰዋሰው

ትርጉም፡ ቃላት ተቀናጅተው ትክክለኛ ዓረፍተ-ነገር የሚመሰረቱበትን ህግና መዋቅር የሚያጠና ክፍል ነው። በአማርኛ ስርዓት "ባለቤት + ተሳቢ + ግሥ" (ለምሳሌ፦ ሔለን እንጀራ በልታለች) የሚለውን የቃላት ቅደም-ተከተል ህግ የምናጠናበት ክፍል ነው።

አገልግሎት (ጥቅም)
ሰዋሰዋዊ ህጎችን ጠብቆ ትክክለኛና ግልፅ ዓረፍተ-ነገር ለመናገርና ለመጻፍ ይጠቅማል
ኮምፒውተርን በመጠቀም ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ የሚደረግን ትርጉም (Machine Translation) ትክክለኛ ለማድረግ ይጠቅማል

Semantics /sɪˈmæntɪks/ስሚአንትክስ / አፋዊ ፍች (ቀጥተኛ ትርጉም)
ትርጉም፡ የቃላት፣ የሀረጋትና የአረፍተነገሮችን ቀጥተኛና ቋሚ ትርጉም (Literal Meaning) የሚያጠና ክፍል ነው። ቃላቱ ብቻቸውን ወይም በአረፍተነገር ውስጥ ሲሆኑ የሚሰጡትን መዝገበ-ቃላታዊ ፍቺ ለመረዳት ያገለግላል።

አገልግሎት (ጥቅም)
በሰዎች መካከል የሚደረግ የሃሳብ ልውውጥ ግልፅና ቀጥተኛ እንዲሆን፣ የቃላትን ትክክለኛ ፍቺ ለመረዳት ይጠቅማል
በቃላት መካከል ያለውን ዝምድና (ተመሳሳይ ፍቺ፣ ተቃራኒ ፍቺ) ለመለየት ይጠቅማል

Pragmatics / ተግባቦታዊ ፍች (አውዳዊ ትርጉም)

ትርጉም፡ የአንድን ንግግር ትርጉም ከሁኔታውና ከአውዱ (Context) አንጻር የሚያጠና ክፍል ነው። ንግግሩ የተደረገበት ቦታና ጊዜ የተናጋሪውና የአድማጩ ግንኙነት እንዲሁም የተናጋሪው ድብቅ ፍላጎት ፍቺውን እንዴት እንደሚቀይረው ያጠናል። ለምሳሌ፦ አንድ ሰው "ክፍሉ በጣም ጨለመ" ሲል ቀጥተኛ ትርጉሙ (Semantics) ብርሃን ማነሱን ማሳየት ሲሆን፣ አውዳዊ ትርጉሙ (Pragmatics) ግን "መብራቱን አብራው" የሚል ትዕዛዝ ወይም ጥያቄ ሊሆን ይችላል።

አገልግሎት (ጥቅም)
ከሰዎች ጋር ስንነጋገር ማህበራዊ ጨዋነትን (Politeness) ለመጠበቅና የሰው ስሜት ሳንጎዳ ሃሳባችንን ለመግለፅ ይጠቅማል
በምሳሌያዊ አነጋገሮች፣ በቅኔ (ሰምና ወርቅ) እና በፌዝ/ቀልድ ውስጥ ያሉትን ድብቅ መልዕክቶች በቀላሉ ለመረዳት ይጠቅማል

ሃሳቤን ሳጠቃልለው አንድን ቋንቋ በአንድ ቤት ብንመስለው ድምፅ-ልሳን (Phonetics) እና ስርአተ-ድምፅን (Phonology) እንደመሰረት፣ የቃል ምስረታን (Morphology) እንደወለል፣ ሰዋሰውን (Syntax) እንደግድግዳ፣ አፋዊ ፍችን (Semantics) እንደጣራ እና ተግባቦታዊ ፍችን (Pragmatics) እንደኮርኒስ ወስደን በጥሩ ሆኔታ ብናዋቅራቸው አንድ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመ ቤት ማግኘት እንችላለን፡፡

በዚህ አንፃር አንድን አዲስ ቋንቋ ስንማርም ሆነ ስናስተምር ከታች በተቀመጠው ቅደም-ተከተል መሰረት እየገነባን መማርና ማስተማር ሲገባን መሰረቱን ዘለን ግድግዳውን ለማቆምና ጣራ ለመክደን የምንሞክር ከሆነ ከንቱ ድካም ነው የሚሆንብን፡፡

Phonetics /fəˈnetɪks/ፈኔድክስ / ድምፅ-ልሳን → Phonology /fəˈnɑːlədʒi/ፈናለጂ / ስርአተ-ድምፅ → Morphology /mɔːrˈfɑːlədʒi/ሞርፋለጂ / የቃል ምስረታ → Syntax /ˈsɪntæks/ስንቲአክስ / ሰዋሰው → Semantics /sɪˈmæntɪks/ስሚአንትክስ / አፋዊ ፍች (ቀጥተኛ ትርጉም) → Pragmatics / ተግባቦታዊ ፍች (አውዳዊ ትርጉም)

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fluent Language Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Fluent Language Center:

Share