General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Share

ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የ ISO 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት። for any support inbox us

welcome to General wingate poly technique college page.

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 24/04/2026

አርብ:- ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የክህሎትና የትብብር ድልድይ፦ 16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በታላቅ የፓናል ውይይት ደመቀ!!

የሀገርን ምጣኔ ሀብት በዕውቀትና በክህሎት ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍን ከኢንዱስትሪው ጋር ማስተሳሰር የውዴታ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ሆኗል። ይህንን ታላቅ ዓላማ ስንቅ ያደረገው 16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ‹‹የቴክኖሎጂ እድገት ለአገር ብልጽግና›› በሚል መንፈስ ደማቅ የፓናል ውይይትን አስተናግዷል።

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ፣ የዘርፉን ትንፋሽ የሚወስኑ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሲቪክ ማህበራት እና ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተገኝተዋል። ይህ ውይይት በራሱ በዘርፉ ላይ ያለውን ከፍተኛ ተስፋና ትኩረት የሚያሳይ ነበር።

የፓናል ውይይቱ በሁለት መሳጭና ወቅታዊ መነሻ ፅሁፎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢትዮጵያ ፓወር አካዳሚ መሪ ዶ/ር ወንድወሰን ካሳ "ከፕሮጀክት ወደ አጋርነት መሸጋገር" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥንካሬ ያለው ሃሳብ፤ ትብብሮች በጊዜያዊ ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይታጠሩ እንዴት ወደ ዘላቂና ስልታዊ አጋርነት ማደግ እንዳለባቸው በስፋት ዳስሰዋል። በዚህም ትብብር ለጋራ ስኬት የሚገነባ ድልድይ እንጂ ለጊዜው የሚቆም ጥላ አለመሆኑን አሳተዋል፡፡

በሌላ በኩል የፌደራል ቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ ዶ/ር ገነነ አበበ በበኩላቸው "የአጠቃላይ ትምህርትን በሙያ ስልጠና ማዳበር" በሚለው ሃሳባቸው መደበኛው ትምህርት ከተግባር ተኮር ክህሎት ጋር ሲዋሃድ የሚፈጥረውን ብቁ ዜጋ ለተሳታፊው አሳይተዋል።

መድረኩ በሁለቱ ምሁራን ሃሳብ ላይ ተመስርቶ በጋለ ጥያቄና መልስ እንዲሁም ገንቢ በሆኑ አስተያየቶች የበለጸገ ውይይት ተካሂዶበታል።

ከቃላት ባለፈ ተግባርን ምስክር ያደረገው የቴክኖሎጂ ኤግዚቪሽን የዕለቱ ሌላኛው ድምቀት ነበር። በኮሌጁ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በላብና በጥበብ የተሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን አጋር አካላትም አገልግሎቶቻቸውንና ምርቶቻቸውን አስተዋውቀዋል። ይህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለኢንዱስትሪው የሚበጁ የፈጠራ ውጤቶች ምንጭ መሆናቸውን በተጨባጭ ያረጋገጠ መድረክ ሆኖ አልፏል።

‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 21/04/2026

ማክሰኞ:- ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮሌጁ ከቻይናው ሻንዚ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና ከCCCC ኩባንያ ጋር አዲስ የታረክ ምዕራፍ ጀመሩ፡፡

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በቻይናው ሻንዚ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና በቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ካምፓኒ (CCCC) መካከል የተመሰረተው የሶስትዮሽ ጥምረት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ወደ ላቀ ዓለም አቀፋዊ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ታውቋል፡፡

"ይህ ስምምነት በሀገራት፣ በተቋማትና በባህሎች መካከል የሚገነባ ጠንካራ ድልድይ ነው፡፡›› ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ናቸው። ኃላፊው አክለውም የሰልጣኞቻችንን የክህሎት ክፍተት በመሙላት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም ከፕሮጀክት ተኮር አሰራር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገራችን ለሀገራችን ብቁ የሰው ኃይል ግንባታ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል "ከሻንዚ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር የጀመርነው ወዳጅነት ወደ ተጨባጭ የሥራ ምዕራፍ የተሸጋገረ ሲሆን ትብብራችን ከእውቀት ሽግግር ባለፈ ፈጠራንና የልህቀት ጉዞን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡" ያሉት ደግሞ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡

የቻይና ኢምባሲና የCCCC ካምፓኒ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በባህል ትስስር ውጤታማ ስራ እንደሚከናወን ገልፃዋል፡፡

የትብብሩ ዋና ዋና ፋይዳዎች የኢንዱስትሪ ትስስር ለማድረግ፣ ዓለም አቀፋዊ የእውቅ ሽግግር ለመፍጠር እና ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ውድድር የቋንቋ ክህሎት ክህሎትን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

.............................................................................

Tuesday: April 21, 2026

The college started a new chapter of cooperation with China's Shaanxi University College and CCCC Company.

The tripartite partnership established between General Wingate Polytechnic College, Shaanxi University College of China and China Construction Communication Company (CCCC) is known to bring technical and vocational education to a higher international level.

"This agreement is a strong bridge that will be built between countries, institutions and cultures," said Mr Million Mathewos, who is the head of Addis Ababa's Labor and skills Bureau with the rank of deputy mayor.

On the other hand, "the friendship we started with Shanxi University College has turned into a concrete phase of work, and our cooperation has gone beyond the transfer of knowledge to innovation and a journey of excellence." said Mr. Melese Yigzaw Dean of General Wingate Polytechnic College.

Chinese Embassy and CCCC Company's senior officials stated that effective work will be done through job creation, technology transfer and cultural connection.

The main benefits of the collaboration are aimed at industrial networking, creating global knowledge transfer and enhancing language skills for global job market competition.

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 09/04/2026

ሐሙስ:- ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

የታዳሽ ኃይል ስትራቴጂን የሚያግዝ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከልነት ጉዞ

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የጀመረችውን አገራዊ ግስጋሴ በዕውቀትና በላቀ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንዲያስችል ኮሌጁ የስልጠና አሰጣጡን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያሸጋግሩ እጅግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አስገባ።

ኮሌጁ የአካባቢውን የመልማት ፀጋ እና የአገሪቱን ስልታዊ የልማት አቅጣጫ መሰረት አድርጎ በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) ለመሆን እየሰራ ያለውን መጠነ ሰፊ ስራ ይበልጥ የሚያፋጥን ኢንቨስትመንት በኤሌክትሪካል ፓወር ሲስተም ዲፓርትመንት ስር እያከናወነ ነው።

አዲስ የገባው የቴክኖሎጂ ግብዓት በዓለም አቀፍ የጨረታ ሂደት አሸናፊ ከሆነው ከታዋቂው የጣሊያን የቴክኖሎጂ ገበያ የተገዛ ሲሆን ለዚህም 912,524 ዩሮ ወይም በአሁኑ የምንዛሬ ተመን ከ160 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል። ይህ ግዙፍ በጀት ኮሌጁ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለሰው ኃይል ብቃት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ወደ ተቋሙ የገቡት ግብዓቶች ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 ያሉ የስልጠና እርከኖችን የሚሸፍኑ ዘመናዊ ማሽኖች፣ ልዩ ልዩ ስማርት ቴክኖሎጂዎችና ዲጂታል መሣሪያዎች፣ የላቁ የጥገና ማሽኖች እና የክፍል ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ያካተቱ ናቸው።

ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይልን የሚያበረታታ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርፃ በቁርጠኝነት እየተገበረች ባለችበት በዚህ ወቅት ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም ይህንን አገራዊ ራዕይ የሚሸከም፣ በዘመናዊ መሣሪያዎች የሰለጠነና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችለውን "ቅንጡ" ግብዓት ማሟላቱ ለዘርፉ ትልቅ እመርታ ነው።

በተለይም በኤሌክትሪካል ፓወር ሲስተም ዘርፍ የተከናወነው ይህ የግብዓት ማሟላት ስራ ኮሌጁ ለአካባቢው ልማትና ለኢንዱስትሪው ሽግግር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ተቋሙ በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ የቴክኖሎጂ ማዕከል የመሆን ግቡን በእጅጉ ያቃርበዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግዙፍ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ መዋዕለ ንዋይ ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከዘመኑ ጋር እኩል የሚራመድ፣ ለገበያ የሚመጥን ባለሙያ የሚያፈራና በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የአገሪቱ የኩራት ምንጭነቱን ይበልጥ የሚያጸናው ታሪካዊ እርምጃ ነው።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

03/04/2026

ለአጫጭር ጊዜ ስልጠና
ፈላጊዎች በሙሉ

ሁለተኛው ዙር ስልጠና አሁንም እንደቀጠል፤ እንደተቀጣጠለ ነው፡፡

እርስዎም ይምጡ፤ ይመዝገቡ፤ መርጠው ይሰልጥኑ፡፡

በገበያ ፍላጎት የተመራ፣ በትብብር የሚሰራ በአዲስ መንገድ የተቀረጸ ስልጠና እንሆ

🌟 ለበለጠ መረጃ የስልክና ቴሌግራም አድራሻችን፦

✅ ስልክ ቁጥር
👉 0933884400
👉 0911972393

✅ ቴሌግራም
👉 https://t.me/WWETC1
👉 https://t.me/WWETC1

Photos from የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau's post 27/03/2026
Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 26/03/2026

ሐሙስ:- መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም

በኮሌጁ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሊቋቋም ነው፡፡

በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴክኒክና ሙያ ተቋም የሆነው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከቻይናው ሱዙ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ኮሌጁን የዓለም አቀፍ የልህቀት ማዕከል የሚያደርግ አራት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ማዕከላትን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ ስምምነት ኮሌጁን በቴክኖሎጂ ሽግግርና በክህሎት ልማት ረገድ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ አራት ዘርፎችን ያቀፈ ነው፡፡

በልህቀት ማዕከሉ የሚደራጁት ዘርፎች የኢትዮ-ቻይና አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ትብብርና ፈጠራ ማዕከል፣ የሱዙ ስታይል የእደ-ጥበብና ዓለም አቀፍ አሰልጣኞች ማፍሪያ ማዕከል፣ የኢትዮ-ቻይና ስማርት ማኑፋክቸሪንግ የቨርቹዋል ምርምርና ትምህርት መድረክ እና የሱዙ-ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪና ትምህርት ትስስር ማዕከል ናቸው፡፡

"የጀነራል ዊንጌትና የሱዙ ዩኒቨርሲቲ አጋርነት ተራ ትስስር ሳይሆን 'የክህሎት ዲፕሎማሲ' ማሳያ ነው፡፡ ዓላማችንም ሰልጣኞቻችንን በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪና ተመራጭ ማድረግ ነው፡፡›› ያሉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ናቸው፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ይህ በጀነራል ዊንጌት የተጀመረው የልህቀት ተሞክሮ ወደ ሌሎች የከተማችን ኮሌጆች እንዲሰፋ በማድረግ አዲስ አበባን የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በቢሮው የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚዴክሳ ከበደ በበኩላቸው "ይህ የልህቀት ማዕከል መቋቋም በኮሌጁና በኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ክፍተት በቴክኖሎጂ ድልድይነት ያገናኛል።

ማዕከሉ የሚያመነጫቸውም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ኢንተርፕራይዞቻችን በመሸጋገር አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በፈጠራ የታገዘ ምርት እንዲያመርቱና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ለወጣቶች የንግድ ስራ ፈጠራና ለቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረታዊ መነቃቃትን ይፈጥራል" ብለዋል።

ይህ ታሪካዊ አጋርነት እውን እንዲሆንና የኮሌጁ ዓለም አቀፍ ትስስር እንዲጠናከር የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ ቢሮው የትብብር መስኮችን በማመቻቸትና ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ ያሳየው ቁርጠኝነት ለዚህ ስኬት ዋና ሞተር ነው፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 26/03/2026

የክህሎት ድልድይ፦ ጀነራል ዊንጌት እና የሱዙ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሰረቱ፡፡

የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የማዕዘን ድንጋይ የሆነው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከቻይናው ግዙፍ ተቋም ሱዙ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የቴክኒክ ስልጠናን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ታሪካዊ ስምምነት ተፈራረመ።

የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ከሱዙ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን በደመቀ ሁኔታ ባስተናገዱበት ወቅት እንደገለጹት ይህ አጋርነት ተራ የሰነድ መፈራረም ሳይሆን በሁለቱ ተቋማት፣ ባህሎች እና በአህጉራት መካከል የሚገነባ ጠንካራ የክህሎት ድልድይ ነው ብለዋል።

ዲኑ አክለውም "ዛሬ እስክሪብቶቻችንን ስናነሳ ስማችንን በገጽ ላይ ብቻ እየጻፍን አይደለም፤ ለተቋሞቻችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየቀረጽን ነው" ሲሉ ስምምነቱ ያለውን ፋይዳ አጉልተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በሁለቱም ወገኖች የተቋሞቻቸውን ነባራዊ ሁኔታና የወደፊት ራዕይ የሚያሳዩ ገለጻዎች ቀርበዋል። ጀነራል ዊንጌት ያለውን የበለጸገ ታሪካዊ ቅርስ ከዘመናዊ ሥርዓተ-ትምህርት ጋር በማጣመር ብቁ የሰው ኃይል እያፈራ መሆኑ ሲገለጽ የሱዙ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በቴክኖሎጂና በምህንድስና ዘርፍ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ አጋርቷል።

ሁለቱ ተቋማት ለአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ ለሰልጣኞች የክህሎት ማጎልበቻ መርሃ ግብሮች፣ ዘመናዊ የሥርዓተ-ትምህርት እና የማስተማሪያ ግብዓቶች ዝግጅት ላይ አብረው ለመስራት ቃል ኪዳን አስረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የሙያ ዘርፍ ማሰልጠኛ ወርክሾፖችን የጎበኙ ሲሆን በጀነራል ዊንጌት እየተሰጠ ያለውን የተግባር ተኮር ስልጠና ተመልክተዋል። እንግዶቹ በኮሌጁ ያለው የቴክኒክ አቅም እና ለፈጠራ ስራ የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን አድንቀዋል።

ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሙያ ትምህርትን ጥራት በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተመራቂዎችን ለማፍራትና የኢትዮጵያን የልማት ግብ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 19/03/2026

ሐሙስ:- መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮሌጁ የግልና የመንግስት አጋርነትን ለስልጠና ጥራትና ለውስጥ ገቢ ዕድገት በሚገባ እየተጠቀመበት መሆኑ ተመሰከረ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግሉ ዘርፍ ጋር የፈጠረው ጠንካራና በእኩል ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለሌሎች ተቋማትም አርአያ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ።

በኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢዲአይ (EDI) አሰልጣኞች ቡድን በኮሌጁ ባደረጉት የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ ወቅት የኮሌጁን ውጤታማነት አድንቀዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲተገበሩ የቀረፃቸው "የስልጠና ዘረመሎች" (DNAs) በጀነራል ዊንጌት ቀድመው በተግባር ላይ መዋላቸውና ውጤት ማምጣታቸው ተረጋግጧል።

ይህ ስኬታማ አሰራር የኮሌጁን የውስጥ ገቢ ከማሳደግ ባለፈ ለሰልጣኞች ጥራት ያለው የተግባር ትምህርት እንዲያገኙ ትልቅ አቅም ፈጥሯል። ይህ ተሞክሮ በሁሉም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ሊሰፋና ሊተገበር እንደሚገባ የአሰልጣኞች ቡድኑ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

EDI (Entrepreneurship Development Institute) ማለት የሥራ ፈጠራ ልማት ኢንስቲትዩት ሲሆን የሥራ ፈጠራ ባህልን ለማስፋፋት፣ ንግድን የማስፋፋት አቅምን ለመገንባት፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር እና የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 13/03/2026

አርብ:- መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስኬቶች ላይ ያተኮረው "ዥረቱ" የተሰኘው ትያትር በኮሌጁ ቀረበ!!

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና (TVET) ዘርፍ የታዩ ውጤታማነቶችንና በመዲናችን አዲስ አበባ የተመዘገቡ የልማት እምርታዎችን የሚዘክር "ዥረቱ" የተሰኘ ልዩ የቲያትር ድግስ በትናንትናው ዕለት በኮሌጁ መድረክ ለተመልካች ቀርቧል።

በአቆልቋይ ኢንተርቴመንት ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ትያትር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ አጋዥነትና በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ይሁንታ የተሰናዳ ነው።

የትያትር ስራው በዘርፉ ያለውን ለውጥ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጫ በሚረዳ መልኩ በአዝናኝና በአስተማሪ አቀራረብ የተቀመረ መሆኑ ተገልጿል።

ለ45 ደቂቃዎች በመድረክ ላይ የቆየው ይህ ትያትር በታዋቂና አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች የተሞላ ነበር። በዝግጅቱ ላይ አርቲስት ሽመልስ ለጋስ እና ደራሲና ተዋናይ ካሳዬ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት የመድረክ ፈርጦች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተውበታል።

ትያትሩ በደራሲና ተዋናይ ካሳዬ ገበየሁ ተደርሶና በአርቲስት ተሻለ ወርቁ ተዘጋጅቶ ለዕይታ በቅቷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሁሉም ኮሌጆች ዲኖችና የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የቀረበው ስራ በይዘቱም ሆነ በአቀራረቡ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።

ይህ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረገው "ዥረቱ" ትያትር በኮሌጁ መቅረቡን ተከትሎ በቀጣይ በሁሉም የመዲናዋ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲሁም በተለያዩ አገራዊ መድረኮች ላይ ለተመልካች እንደሚቀርብ ከዝግጅት ክፍሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኪነ-ጥበብ ስራ ዓላማ ማህበረሰባዊ እውነታዎችን የምናይበት መስተዋትና ለውጥን የምናበስርበት መሣሪያ ሲሆን ከማዝናናት ባሻገር ውስብስብ ማህበረሰባዊና ተቋማዊ ሂደቶችን በቀለለና በሰረፀ አቀራረብ ለተመልካች ማድረስ ነው።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

Photos from General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ's post 13/03/2026

ለአጫጭር ጊዜ ስልጠና
ፈላጊዎች በሙሉ

አሁንም ስልጠናው እንደቀጠል፤ እንደተቀጣጠለ ነው፡፡ ብዙዎች እኛ በሙያ አብቅተን ልናስመርቃቸው ስንተጋ እነርሱ ደግሞ በአገልግሎት አሰጣጣችን እርካታ አግኝተው ደጋግመው እየመረቁን ነው፡፡

እርስዎም ይምጡ፤ ይመዝገቡ፤ መርጠው ይሰልጥኑ፡፡

በገበያ ፍላጎት የተመራ፣ በትብብር የሚሰራ በአዲስ መንገድ የተቀረጸ ስልጠና እንሆ

🌟 ለበለጠ መረጃ የስልክና ቴሌግራም አድራሻችን፦

✅ ስልክ ቁጥር
👉 0933884400
👉 0911972393

✅ ቴሌግራም
👉 https://t.me/WWETC1
👉 https://t.me/WWETC1

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa, Wingate Street
Addis Ababa
100