06/01/2021
ሊቃውንትን አነጋግሯል፤ የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን ትኩረት ስቧል፤
ወንጌላዊው ማቴዎስ አመጣጣቸውንና ስጦታቸውን ተናገረ እንጂ ሀገራቸውንና
ስማቸውን አልጻፈም፨
ለማንኛውም ነቢያት ስለነዚኽ ነገሥታት ሀገር በትንቢት ምን ተናገሩ?
የሚለው ለሁሉም መልስ ይሆናል።
ከነቢያት ዳዊትና ኢሳይያስ የሰብአ ሰገል አመጣጥ ተገልጾላቸው ትንቢት
ሲናገሩ፤ ይልቁኑ ኢሳይያስ ሀገራቸው የሳባ ምድር ኢትዮጵያ እንደኾነና ኹሉም
ከዚኽ እንደሚኼዱ፦
"የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ
ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና
ያወራሉ" (ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 6) አለ፨
ዳዊትም በመዝሙሩ ላይ ለአምላክ ልደት ስጦታ እንደሚመጣ ጠላት
ሰይጣን ጠላት ሄሮድስ እንደሚያፍሩ ኢትዮጵያውያን በፊቱ እንደሚሰግዱ፦
"በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስና
የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን
ያቀርባሉ ነገሥታትም ሁሉ ይሰግዱለታል" (መዝ 71 (72):9-10) ይላል። ይህም
የትንቢት ቃል ሲፈጸም፦
“ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም
ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም
አቀረቡለት።” (ማቴዎስ 2፥11) ይለናል።
በተጨማሪም ዳዊት "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ነገሥተ
ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር" ( ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር
ትዘረጋለች (ታደርሳለች)፤ የምድር ነገሥታት እግዘአብሔርን አመስግኑት"
በማለት ትንቢት ተናግሮላታል፨
ታላላቅ ሊቃውንት እንደገለጹት የግእዝ ቋንቋችን እንደሚያስረዳን "በጽሐ"
የሚለው የግእዝ ቃል ቀጥታ የዐማርኛ ትርጉሙ (ደረሰ) ማለት ሲኾን ታበጽሕ
ማለት ደግሞ (ታደርሳለች) ማለት ነው፨ "ሰፍሐ" ማለት ግን (ዘረጋ) ማለት
ነውና ትሰፍሕ ቢል ትዘረጋለች ባልን ነበር፤ መዘርጋት ማንም ሊዘረጋ ይችላል፤
ዘርግቶም ሊቀበልም ላይቀበልም ይችላል፤ ይኽቺ ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያ ግን "ታበጽሕ" (ታደርሳለች) ተብላ ተነግሮላታልና አምላኳ ሲወለድ
ሥጦታን በማቅረብ በእውነት አድርሳለች ነገሥታቱም አመስግነዋልና ይኽም
ከአምላኳ ለርሷ ብቻ የተሰጠና የተነገረላት ነው (መዝ 67:11)፨
ሥጦታም መስጠት ጥንቱኑ በብሉይ ኪዳን በነ ንግሥት ሳባ የጀመረችው
እንጂ ለሀገሪቱ እንግዳ አይደለም "ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም
ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ
ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር" እንዲል (መጽሐፈ
ነገሥት ቀዳማዊ 10: 10)፨
ከምንኖርባት ፕላኔት መሬት ላይ ካሉ የዓለም ሀገራት በብቸኝነት ጌታችን
የተወለደበትን ወር ለክርስቶስ አምላኳ የሰጠች ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤
ይኸውም ጌታ የተወለደበትን ወር "ታኅሣሥ" ብላለች በቋንቋዋ በግእዝ፤
ይኸውም በግእዝ ቋንቋ "ኀሠሠ" ማለት ፈለገ ማለት ሲኾን ታኅሣሥ ማለት
"ወርኀ ተኀሥሦ" (የማሰስ ወር፣ የፍለጋ ወር) ማለት ሲኾን፤ ሊቃውንት ይኽነን
ያሉበት ምክንያት ሦስቱ ነገሥታት "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?
ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና" እያሉ አስሰው ፈልገውት
ስላገኙት ይኽ ሥያሜን ቀደምት አባቶቻችን ሰጥተዋል (ማቴ 2: 1-2)፨
ከዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች ውስጥ ዊልያም ሊዮ ሀንስበሪና
ኢሀርፐር ጆንሰን Africa's Golden Historical facts እና በሌሎች በጥልቅ
ጥናታዊ ሥራቸው ላይ የሰብአ ሰገል መነሻ ሀገር ኢትዮጵያ እንደነበረች
"Casapar king of Ethiopia, Melchior King of Ethiopia, and
Balthazar king of Saba ... he brought the gift of frankincense ...
which was for a thousands years the capital city of African
Christian Kingdom" የሚልና ሌላም ገራሚ ጥናትን እናነባለን፨
https://books.google.com.et/books?id=NuEDAAA
AMBAJ&pg=PA86&lpg=PA86&dq=
በአውሮፓ የዜና መዋዕል ጥናትና ምርምር የያዘው የሰብዐ ሰገል
ትውልድ የነበረውን ካህኑ ዮሐንስ (Prester John) የሚሉት ታሪካዊ መሪን
ለማግኘት በዓለም ዙሪያ ባደረጉት ሰፊ ዐሰሳ ሥርወ መንግሥቱ ሕንድ ሳይኾን
ኢትዮጵያ እንደነበር ገልጠው ጽፈዋል (Thornton, Joe (2012). A Cultural
History of the Atlantic World, 1250-1820. Cambridge University
Press. pp. 16–17). https://www.blackpast.org/global-african-h
istory/prester-john/
ሰብአ ሰገል የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ሲሆኑ ታላቁ ተመራማሪ ጆን ጃክሰን
"ethiopian and the origin of civilization" በሚለው ድንቅ መጽሐፉ ገጽ
28 ላይ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የሥነ ጠፈር ጥናት የተጀመረባት ጋላክሲን
ከነፕቶሎሚ አስቀድማ መሰየም የቻለች ሀገርና ለሌሎች ሀገር ጥናቱን
እንዳስተላለፈች በስፋት ገልጾታል፤ እነዚኽም ነገሥታት የሥነ ጠፈር (የኅዋ)
መርማሪዎች ከነበሩ ምንጩ እዚኽ መኾኑ ያስረዳል፨
ሌሎች ተመራማሪዎች በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣው ቤዴን ጨምሮ
ሜልኩ (ሜልኪዮር) የሚባለው የፐርሺያ ንጉሥ እንደነበር ወርቅን በጌታ ፊት
እንዳቀረበና ከሰብአ ሰገል አረጋዊው ርሱ እንደኾነ ጠቅሷል፨
ማንቱሲማር (ጋስፖር) ደግሞ ንጉሠ ሕንድ ሲኾን በጌታችን ፊት ዕጣንን
ያቀረበው ርሱ መኾኑን ይጠቅሳሉ፨
በዲዳስፋ (ባልዛር) ደግሞ ጥቁሩው ንጉሠ ኢትዮጵያ እንደኾነ ሲገልጹ
መልኩም ጥቁር እንደነበር በመመስከር ከርቤን በአምላኩ በክርስቶስ ፊት
እንዳቀረበ ጽፈዋል፨ ዛሬ ድረስ ምዕራባውያን በሚሠሩት የልደት የፊልም
ተውኔትና ሠዓሊዎቻቸው በሚሥሏቸው የሰብአ ሰገል ሥዕሎች ላይ
ኢትዮጵያዊውን አንዱን ጥቁር ያደርጉታል። https://www.washingtonpo
st.com/archive/lifestyle/style/1989/12/10/the-legend-of-the-
three-kings/c58d1b2c-4615-47a9-be76-7ca057b7ed37/
መተርጉማን ደግሞ ወርቅ ያመጣውን ከነገደ ሴም፣ ዕጣን ያመጣውን
ከነገደ ካም፣ ከርቤ ያመጣውን ከነገደ ያፌት ያደርጉታል። በኹሉም ብንመረምር
የኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ በሀገሪቱ የሚጀምረው በ34 ዓ.ም. ሳይኾን ልክ
ጌታችን ሲወለድ በ 1 ዓመተ ምሕረት መሆኑ ነው፨
ዛሬ ድረስ በምድራችን የሚኖሩ ሀገራት ኹሉ በዲዮናስዮስ ኤክስጊዩስ
በተፈጠረው ስሕተት ክርስቶስ የተወለደበትን ዘመን በመሳሳት 7 ዓመት
ጨምረው ተሳስስተዋል፤ ይኽነን ስሕተታቸውን የሮማ ካቶሊክ መሪ የነበሩት ፓፕ
ቤኔዲክት በጻፉት መጽሐፍ ያመኑ ሲኾን፤ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ
ሳትጨምር ሳትቀንስ ልደተ ክርስቶስን በትክክል የምታከብር ብቸኛ የዓለማችን
ሀገር ናት (http://www.telegraph.co.uk/news/worldnews/the-
pope/9693576/Jesus-was-born-years-earlier-than-thought-clai
ms-Pope.html )፨
[ደስ በሚያሰኘው በጌታችን ልደት በዓል ዋዜማ ስለ ሰብአ ሰገል
በጥቂቱ በኢትዮጵያዊው ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ]