09/02/2026
ጀግናው ወ ጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምያ በምሥ/ ወለጋ በነቀምቴ ቤኬጀማ ክ /ከተማ ቀበሌ 06 ከ23 (ከሃያ ሦስት ዓመት በፊት ተወልዶ የቅድመ አያት አባቶቹን የደም ውስጥ የጀግንነት ወኔ ይዞ
የኢትዮጵያ አየር ሀይል 90 ዓመቱን በተመሣሣይ እለት በአሜሪካ አየር ሀይል ውስጥ ተመርጦ ሥልጠናውን ጨርሶ በዕለቱ ከስምንት መቶ አሥራ ዘጠኝ ተመራቂዎች ጋር ኢትዮጵያዊዉ በማዕረግ የተመረቀው ወጣት ሶለን አድጎልኝ መኮንን በኔ በወላጅ አባቱ በኩል የትውልድ ግንድ
በንጉሡ በኋይለሥላሤ ዘመነ መንግሥት በ 1928- 1933 ዓ/ም ፋሽስት ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ ከአርባ ዓመት በኋላ ቂም ይዞ ሀገሪቱን ሲወር ንጉሡ ኢትዮጵያን ለጠላት ትተው ወደ ውጪ (ለንደን )በሸሹበት ጊዜ
በወለጋ ጠቅላይ ግዛት የሌቃ ዱለቻ (የገተማ )ባላባትና ገዢ የነበሩ በላንበራስ ሞጋ እንግዳ
ከሌሎች ከአራቱ ማዕዘናት ከተሠማሩ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው የአሁንዋን ኢትዮጵያ ያስረከቡን ! በእናቱ በኩል ከጀግናው ኢትዮጵያዊ ፊታውራሪ መኮንን ጀንበሬ በንጉሡ ጊዜ በወለጋ ጠቅላይ ግዛት የነቀምቴ ከተማ ገዢ የነበሩ ! ፋሽስት ጣሊያን በምዕራብ አቅጣጫ ሀገሪቱን ሲወር በከፊታውራሪ ሞሣ ጂጆ ከአጎታቸው ከቀኝ አዝማች አብዲሣ ሞሣ በጠለት ወረራ ጊዜ ከነበሩ አርበኞች ጋር በመቀናጀት በዱር በገደሉ ጠላትን በማሳደድ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ በህይወት የተረፈውም ወደ መጣበት መልሰውታል ! በወቅቱ ከነቀምቴ ከተማ ወደ ምስራቅ አ/አ ወደ ሚወስደው መንገድ ላይ በከ ቦንያ የምትባል የጠላት ካምፕ ላይ ፊታውራሪ መኮንንና ጀግኖቹ የጠላትን ቦንብ ጣይ ባለ ሁለት ሞተር የውጊያ አውሮፕለን በማጋየት ! በአካባቢ ተወላጆች ብዙ የተዘመረላቸው ጀግና ናቸው ! ከሙገሣውም በጥቂቱ ሀገሬው ደስ ብሎት በኦሮምኛ እንዲህ አለ መኮንን ጀንበሬ ደፊኖ ጀልቀቤ ፈጫሳ ኢረ ኦሌ ሮቢ ሬፈ ቱሌ ! ብዙ የተባለላቸው ነበሩ በወቅቱ ሆለታ ገነት ማሠልጠኛ ት/ቤት የነበሩ ጀግናው አብዲሣ አጋ እና አርበኞቹ የጥቁር አንበሳ ጦር ከጦርነቱ የተነሳ ወደ ምዕ ኢትዮጵያ በመምጣት የነፊታውራሪ መኮንን ጦር በመቀላቀል ጠላትን አስወግደዋል ! የተቃጠለው የጦር አውሮፕላን ሁለት ሞተሮች በወለጋ ሙዚየም ይገኛል እናም በዘመናት ትውልድ የኢትዮጵያ የአባቶቹ የጀግንነት ውጤት ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ እንዲህ ሲገለጥ የጀግናው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ደስታው የለቀ ነው እንኳን ደስ አለን እያልኩ ፈጣሪ አምላክ ከህልሞቼ ውስጥ አንዱ በልጅነቴ አየር ሀይል ለመሆን አመኝ ነበር በልጄ ፈጣሪ መልስ ሆኖኛል ።
አንግዲህ ወገኔ ወላጆች ህልማችሁ በእናንተ ባይፈጸም በልጅህ ይፈፀማል እመን ወገኔ መልካም ዕድል እያልኩ እንዲህ ሲሆን ትልቁ የእግዚአብሔር እርዳታ ሲሆን የሰውም ድርሻ አለበት ለዚህ ብቃት ለማመስገን ፍቀዱልኝ ?
1ኛ ፈጣሪ አምላክ እግዘብሔርን
2ኛ ወልዳ ደክማ ያሳደገችውን እናቱን ውድ ባለቤቴና ወንድም እህቶቹ ወዳጅ ዘመዶቹ እና ጎረቤት የቤኬጀማ መካነኢየሱስ ማ/ምዕመናን
3ኛ የቤቴል መዋዕለ ሕፃናት ባለ ራዕይና የት/ቤቱ ሀላፊ ወንድም ተስፋዬ ወዳጆና በወቅቱ የነበሩ ትጉ መምህራን
4ኛ ለነቀምቴ ካቶሊክ ት/ቤት አስተዳደርና ለወንድም ትንሳኤ እና መ/ምህራን
5ኛ ለ4ኪሎ ዮኒቨርሲቲ እና አ/አ ለሚገገኘው ሴሚኔሪ ! ባጠቃላይ የሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ውጤት ወጣቱም በተግባር ስለተረጎመው ለሱም ክብር አለኝ እንኳን ደስ አለን ወጣቶች በተለያየ የሥራ መሥክ ሀገራቸውን እንደሚያስጠሩ አልፎም እንደሚያገለግሉ አባቶች እናቶች ተስፋ አለን በ