14/02/2025
ሰሞኑን አንድ ፊልም እያየሁ ነበር ቲክታክ ላይ
።
የሆነ ጉድጒድ ነገር አለ ነጮቹ እንጨት አምጥተው ጉድጒዱን ይሻገሩታል ………
ቻይና እንደ ነጮቹ መሻገሪያ አስቀምጦ ይሻገራል።
አፍሪካ/ኢትዮጲያዊ ግን ጉድጒዱን ለመሻገር ይፀልያል ፀሎት ጨርሶ ሲጨርስ ለመሻገር ሲሞክር ጉድጒድ ውስጥ ይገባል መሻገር አልቻለም።
የሚገርመው ይሄንን ጉዳይ ብዙ ሺ ሰዎች ለዛውም የኛው ሰው እረ የማከብረው ንቁ በሳል የተማረ ጒደኛየም ላይክ ብሎታል በጣም ነው የሚያሳፍረው
ምን እያለ እንደሆነ እንኳን እንዴት መረዳት ተሳነን እየተሰደብክም አሜን ማለት ። ሃይማኖትህንም በቴክኒካል ሁኔታ ሲያዋርድ ላይክ ብለህ እንዴት ይቻላል።
ቪዱዮውን በብዛት አበሻ እና ጥቁሮች ናቸው ላይክ ያሉት።
ካልሰራህ ካልጣርክ እግዚአብሄር አያግዝህም። ፀሎትን ያለ ስራ አሳይቶ ፀሎት ትርጉም እንደሌለው መረን እንሰሳ እንድትሆን ሲያሰለጥኑህ ቢያንስ መቃወም ስነ ልቦና ከሌለህ እንዴት ላይክ ትላለህ አሳፋሪ ሁላ።
ፀሎት ሳታደርግ ዝም ብለህ ኑር ፈጣሪ የለም ወደሚል ፍልስፍና እየወሰደህ እንዴት ነው ግን…………
።።
እረ ምን ይሄ ብቻ የታክሲ ሰልፍ ላይ ነኝ ሰውየው ትራምፕ እኮ የአፍሪካ መሪዎችን ሰደበ "ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለህ አለ " ያቅራራል የሚገርመው አጠገቡ ያሉት አዎ ልክ ነው ጅቦች ምናምን አላለም ። እስቲ እናፍታታው እውን የአፍሪካ መሪዎች ብቻ ናቸው ችግር ፈጣሪ በግለሰብ እያንዳንዳችን ችግር የለብንም። ጥቂት ሃሳብ ቢነሳ ነገሩን ከዘውጋችን ጋር የማናላትም ነን ወይ። ትራምብ የሚመራት ሃገር አይደለ እንዴ ኮንጎ ላይ የመሳሪያ ስፖንሰር ሱማሊያ ሌት ተቀን በአሸባሪ ስም የጥይት መሞከሪያ አይደለች እንዴ አሜሪካ አይደለች እንዴ ሊቢያን ያፈራረሰችው፣ አሜሪካ አይደለች እንዴ ግብጥ ላይ በህዝብ የተመረጠን አሸባሪ ሙስሊም ነው ብላ በወታደር ያስቀየረችው። አዎ አፍሪካውያን ክፋ ህዝቡ መሃይም ነው ይሄ ሁሉ የሆነው ግን ብቻቸውን ግን አይደሉም።
በርግጥ አፍሪካ አይተባበርም አንዱ አንዱን ያጠፋል ይወጋል ጎንጎ M23 የሚያደርሰው ጥፋት የሚዘርፈው ሃብት የታጠቀው መሳሪያ በአፍሪካውያን ጎረቤቶቹ ነው በነ ካጋሜ። ኢትዮጲያ በወያኔ ስትለበለብ ሱዳን ጉዳዩን ሲያወሳስብ ኤርትራ ንፁሃን ተጋሩን ሲገል ነበር አፍሪካ አዎ ክፋ ነው ይሄ ሁሉ የሆነው ግን በአሜሪካና አጋሮቹዋ ጭምር ነው። ስለዚህ ኑ ላሞኛችሁ ነው ትራምብ እያለን ያለው ህዝቤ ደሞ የእውቀት ጥግ ጭራ ነው እና አዎ ይላል አብሮ።
ኖ ሞር አፍሪካ