ዳዕዋ በንፅፅር። Calling towards Islam comparatively.

ዳዕዋ በንፅፅር። Calling towards Islam comparatively. ምስጋና ለዓለማቱ ተንከባካቢ ለአላህ ነው::

20/03/2026
✍✍በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታጠቀ ቅዱስ ተጋድሎ (ግልፅ ማስረጃ)በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ጦርነት በብዙ ቦታዎች ከእግዚአብሔር ትእዛዝ የተነሳ እንደሚፈፀም ተጠቅሷል።▶ምሳሌ 1፡ የተደነገገ ጦርነት...
08/02/2026

✍✍በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታጠቀ ቅዱስ ተጋድሎ (ግልፅ ማስረጃ)
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ጦርነት በብዙ ቦታዎች ከእግዚአብሔር ትእዛዝ የተነሳ እንደሚፈፀም ተጠቅሷል።
▶ምሳሌ 1፡ የተደነገገ ጦርነት
ዘዳግም 20፡13
“አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣት ጊዜ በርሷ ያሉትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ስለት ትገድላቸዋለህ።”
ይህ ንግግር ምሳሌ ብቻ አይደለም፤ ግልፅ የጦር መመሪያ ነው።

▶ምሳሌ 2፡ እግዚአብሔር እንደ ተዋጊ
ዘፀአት 15፡3
“እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው”
ይህ አንቀጽ ብቻ እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ጦርነት እንዳለ ያሳያል።
▶3ኛ. ኢየሱስና ሰይፍ
ብዙዎች “ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ ነበር” ይላሉ፤
ግን መጽሐፍ ቅዱስ ያቀረበው ምስል ውስብስብ ነው።
▶4ኛ ማቴዎስ 10፣ 34
በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።”
▶5ኛ ሉቃስ 22፡36
“እርሱም፦አሁን ግን ኰረጆ ያለው ከእርሱ ጋራ ይውሰድ ከረጢትም ያለው እንዲሁ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ።”

ትክክለኛው እምነት በአላህ ማመንና በርሱ ላይ ምንንም አለማጋራት ነው። ነቢያችን ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመን መንገዳቸውንም መከተል ያጠቃልላል።
30/01/2026

ትክክለኛው እምነት በአላህ ማመንና በርሱ ላይ ምንንም አለማጋራት ነው። ነቢያችን ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመን መንገዳቸውንም መከተል ያጠቃልላል።

02/01/2026

ስለ ኃይማኖቶች ማወቅና መገንዘብ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው።

30/12/2025

የኢስላማዊ አጣብቂኝ ክሶች
(Islamic Dilema)

ተግዳሮት ፭ (5)፦ "ቁርኣን በወንጌል ፍረዱ ካለ ወንጌል አልተበረዘም ማለት ነው"

ክርስቲያን ወገኖች የቁርኣን 5:47ን በመጥቀስ "ቁርኣን በወንጌል ፍረዱ ካለ ወንጌል አልተበረዘም ማለት ነው" የሚል መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ። ለዚህ ስሁት አረዳድ ምላሾችን ከዚህ በታች እንደሚከተለው እናያለን፦

➺ የአውዱ ትንታኔ

የአንቀጹ ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል፦

"የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ፡፡ አላህም ባወረደው የማይፈርድ ሰው እነዚያ አመጸኞች እነርሱ ናቸው፡፡" (አል-ማኢዳህ 5፥47)

ይህ አንቀጽ የሚገኝበት አውድ (ከአንቀጽ 41-48) የሚያወራው ስለ ፍርድ ነው። በወቅቱ በመዲና የነበሩ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እየመጡ "በመካከላችን ፍረዱ" ይሉ ነበር። ቁርኣን ግን የራሳቸውን መጽሐፍ ትተው ወደ እርሳቸው የሚመጡት ለመከተል ሳይሆን የቀለለ ፍርድ ፍለጋ መሆኑን ይገልጻል።

ስለዚህ በፍርዱ እውነተኝነት የምታምኑ ከሆነ "በመጽሐፋችሁ ያለውን የነቢዩ ሙሐመድን መምጣትና ሌሎች ድንጋጌዎች ተቀበሉ" የሚል እንድምታ አለው።

➺ "ሰበበ ኑዙል" (አንቀጹ የወረደበት ምክንያት)

ታላቁ ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሲር እና ሌሎችም እንደገለጹት፣ ይህ አንቀጽ የወረደው የነጅራን ክርስቲያኖችና የመዲና አይሁዶች የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ነቢይነት በመጽሐፋቸው እያወቁ ለመደበቅ በሚሞክሩበት ወቅት ነው።

አንቀጹ "ፍረዱ" የሚለው ክርስቲያኖች በወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መምጣት ትንቢት አምነው እንዲቀበሉና እውነታውን ሳይደብቁ ለህዝባቸው በመናዘዝ እንዲፈርዱ ለማሳሰብ ነው። በወንጌል መፍረድ ማለት ወንጌል ያዘዘውን "የመጨረሻውን ነቢይ ተከተሉ" የሚለውን ትዕዛዝ መተግበር ማለት ነው።

ክርስቲያን ወገኖች ያመጡት ክስ የሚከተሉትን አመክንዮአዊ ክፍተቶች ይዟል፦

1/ "ወንጌል" የሚለው ቃል ትርጓሜ፦ ቁርኣን "ኢንጂል" (ወንጌል) የሚለው ለአላህ መልእክተኛ ለዒሳ (ዐ.ሰ) የወረደውን መለኮታዊ ቃል እንጂ፣ ሰዎች የጻፏቸውን አራቱን ወንጌላት (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ) አይደለም። ሙስሊሞች አራቱ ወንጌላት ውስጥ የመለኮት ቅሪት የሆኑ ቃላት ቢኖሩም የሰው ቃልም ተቀላቅሎበታል ብለን እናምናለን።

2/ መበረዝ (ተሕሪፍ) እና መኖር፦ አንድ መጽሐፍ "ተበርዟል" ሲባል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም። እውነትና ሐሰት ተቀላቅሎበታል ማለት ነው። ቁርኣን በሌሎች አንቀጾች (ለምሳሌ 2:79) መጽሐፉን በእጃቸው እንደሚጽፉና "ከአላህ ዘንድ ነው" እንደሚሉ በግልጽ ይናገራል። ስለዚህ 5:47 በይዘቱ ውስጥ መለኮታዊ ቅሪት መኖሩን እንጂ "ያልተበረዘ/ኦርጅናል" መሆኑን አያመለክትም።

3/ ተቃርኖ፦ ክርስቲያኖች "ቁርኣን ወንጌል ትክክል ነው ይላል" ካሉ፣ በዛው ወንጌል ውስጥ "ከእኔ በኋላ የሚመጣውን ነቢይ (አሕመድን/ሙሐመድን) ተቀበሉ" (ቁርኣን 61፥6) የሚለውን ትዕዛዝ ለምን አይቀበሉም? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ቁርኣን የጠቀሰው ኢንጅል ላይ ያለን ህግ መቀበልና በሱ መፍረድ ይህንን የሚያካትት ስለሆነ።

➺ ቁርኣናዊ ማስረጃ (5:48)
ከአንቀጽ 47 ቀጥሎ ያለው አንቀጽ 48 ጉዳዩን ይቋጨዋል፦

"ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ (ሙሀይሚን) ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡."

"ሙሃይሚን" ማለት በቀደሙት መጽሐፍት ውስጥ የተለወጠውንና ትክክለኛውን የሚለይ 'ሚዛን' ማለት ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች በወንጌል እንዲፈርዱ የታዘዙት ከቁርኣን ጋር በማይጋጭ መልኩ እና በወንጌል ውስጥ ያለውን የነቢዩን መምጣት እንዲቀበሉ የሚያደርገውን ፍርድ ነው።

➺ ማጠቃለያ

ቁርኣን 5:47 ክርስቲያኖች በመጽሐፋቸው ውስጥ ያለውን እውነት (በተለይ ስለ ነቢዩ ሙሐመድ የተነገረውን) ተቀብለው እንዲፈርዱ እንጂ፣ አሁን በእጃቸው ያለው "መጽሐፍ ቅዱስ" ቃል በቃል ያልተበረዘ መለኮታዊ ቃል ነው የሚል ትምህርት የለውም። አንቀጹ ከሰበበ ኑዙሉ ጀምሮ እስከ አውዱ እንዲሁም እስከ ተፍሲሩ ድረስ የሚያስተምረውም ከላይ በተገለጸው መሠረት ነው።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻

29/12/2025

ግጠሙኝ እያሉ ደጋፊዎችን ሰብስቦ በር ዘግቶ እስልምናን እየተ ሳደቡ ማምሸት አፀ ያፊ ተግባር ነው። ይህን እያደረገ ያለው ማን ነው?

29/12/2025

መሳ ደብ መርሁን ያደረገው እ ፎ ይ ሲሳ ደብ እንዴት 3,000 ሰው ቁጭ ብሎ ያዳምጣል?

ይህን ላይቭ የምትከታተሉ የዚህ ፔጅ ተከታታዮች አላችሁ? ምን እውቀትስ ተማራችሁ?
27/12/2025

ይህን ላይቭ የምትከታተሉ የዚህ ፔጅ ተከታታዮች አላችሁ? ምን እውቀትስ ተማራችሁ?

የነቢያት ሁሉ ተልዕኮ አላህን በብቸኝነት አምልኩ፣ በእርሱም ምንንም አታጋሩ የሚል ነው።
17/09/2025

የነቢያት ሁሉ ተልዕኮ አላህን በብቸኝነት አምልኩ፣ በእርሱም ምንንም አታጋሩ የሚል ነው።

14/08/2025

ዓለምን የፈጠረ፣ የተንከባከበ አዛኙና ሩህሩሁ አምላክ አላህ በሰው ልጅ ክህደት ፈፅሞ አይገባውም👌 ከተራ ብሽሽቅና መነቋቆር ወጥተን በሚዛናዊ እይታ የእምነታችንን መሰረት ማጤን አለብን‼

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዳዕዋ በንፅፅር። Calling towards Islam comparatively. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category