በየቀኑ 1 ሐዲስ

በየቀኑ 1 ሐዲስ ኑ የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ እንተዋወስ!!

22/12/2025

መወዳደር የምትፈልጉ እድሉ ለእናንተም ነው። ካሸነፋችሁ በቃላቸው መሰረት ትሸለማላችሁ።

ሽልማቱ እንደሚከተለው ይሆናል።
1ኛ ለወጣ 4000 ብር
2ኛ ለወጣ 2000 ብር
3ኛ ለወጣ 1000 ብር
4ኛ ለወጣ 600 ብር
5ኛ ለወጣ 400 ብር

የውድድሩን ዝርዝር መረጃና ሂደት የቴሌግራም ቻናላቸውን ተቀላቅላችሁ መከታተል ትችላላችሁ።

የቴሌግራም ቻናል👉 t.me/Yagelegele_Eqa/1627

📍ከጠላት ጋር መገናኝትን አትመኝ ከመጣ ግን… ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تَتَمَنَّوْا لِقاءَ العَدُوِّ، وسَلُوا اللَّهَ العافِيَةَ، فَإِذا لَ...
21/12/2025

📍ከጠላት ጋር መገናኝትን አትመኝ ከመጣ ግን…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَتَمَنَّوْا لِقاءَ العَدُوِّ، وسَلُوا اللَّهَ العافِيَةَ، فَإِذا لَقِيتُمُوهُمْ فاصْبِرُوا، واعْلَمُوا أنَّ الجَنَّةَ تَحْتَ ظِلالِ السُّيُوفِ﴾

“ከጠላት ጋር ተገናኝቶ መፋለምን አትመኙ። ይልቁንስ አላህ ሰላምን እንዲሰጣችሁ ለምኑት። ነገር ግን አይቀሬ ሆኖ ከጠላት ጋር ከተገናኛችሁ ወደኋላ አትበሉ ታገሱ፤ ጀነት ከሰይፍ ጥላ ስር መሆኑን ደግሞ እወቁ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2965

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

👉በዉዱዑ ላይ መሆንን አዝውትረ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اسْتقيموا ولن تُحصوا، واعلموا أنَّ خيرَ أعمالِكم الصلاةُ، ولا يحا...
20/12/2025

👉በዉዱዑ ላይ መሆንን አዝውትረ

ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

﴿اسْتقيموا ولن تُحصوا، واعلموا أنَّ خيرَ أعمالِكم الصلاةُ، ولا يحافظُ على الوضوءِ إلا مؤمنٌ﴾

“በሐቅ ላይ ፅኑ፤ ሁሉንም ስራ ልታሟሉ አትችሉም። ከስራዎቻቹህ ሁሉ በላጩ ሶላት መሆኑን እወቁ። ዉዱዕን (ትጥበትን) አይጠባበቅም (ሙዕሚን) አማኝ ቢሆነ እንጂ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 952

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

👉ላኢላሃ ኢለላህ! ሙሀመዱ ﷺረሱሉላህ✅ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما من نفسٍ تموتُ وهي تشهدُ أن لا إلهَ إلا اللهُ، وأني رسولُ ا...
19/12/2025

👉ላኢላሃ ኢለላህ! ሙሀመዱ ﷺረሱሉላህ✅

ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما من نفسٍ تموتُ وهي تشهدُ أن لا إلهَ إلا اللهُ، وأني رسولُ اللهِ، يرجعُ ذلك إلى قلبٍ موقنٍ، إلا غفر اللهُ لها﴾

“እርግጠኛ በሆነ ልቦና ከአላህ በስተቀር የሐቅ አምላክ እንደሌለና እኔም የአላህ መልዕክተኛ እንደሆንኩ የምትመሰክር ነፍስ አትሞትም፤ አላህ ለሷ የማረላት ቢሆን እንጂ።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 2278

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

🚫በደልን አስቁም.....‼️✅ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِنَّ النَّاس إِذا رَأَوُا الظَّالِمَ فَلَم يَأْخُذُوا عَلَى يَدَيه أَوشَكَ أَنْ ي...
17/12/2025

🚫በደልን አስቁም.....‼️✅

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ النَّاس إِذا رَأَوُا الظَّالِمَ فَلَم يَأْخُذُوا عَلَى يَدَيه أَوشَكَ أَنْ يَعُمَّهُمُ اللهُ بِعِقَابٍ مِنْهُ﴾

“ሰዎች በዳይን እያዩ እጁን የማይዙት (ከበደሉ የማይከለክሉት) ከሆነ፤ አላህ ከሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል፡ 4338

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

⚠️⚠️ቀብር የመጀመሪያው?🔺⛔ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦  ﴿إنَّ القَبرَ أوَّلُ مَنازِلِ الآخِرةِ، فإِنْ نَجا مِنهُ، فما بَعد...
16/12/2025

⚠️⚠️ቀብር የመጀመሪያው?🔺⛔

ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ القَبرَ أوَّلُ مَنازِلِ الآخِرةِ، فإِنْ نَجا مِنهُ، فما بَعدَه أيسرُ مِنهُ، وإنْ لَم يَنْجُ مِنهُ، فما بَعدَهُ أشَدُّ مِنهُ﴾

“ቀብር የመጀመሪያው የአኼራ ‘የቀጣዩ ዓለም’ መዳረሻ ነው። እሱን ነፃ የሆነ ከዛ በኋላ ያለው ገር ይሆንለታል። እሱን ነፃ መሆን ያልቻለ ከዛ በኋላ ያለው የ
ከበደ ይሆንበታል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 1684

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

⚖ከተውሒድ በኋላ ሶላትን አደራ ⛔ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أوَّلُ ما يُحاسَبُ بِهِ العبدُ الصلاةُ، وأوَّلُ ما يُقْضى بينَ ا...
14/12/2025

⚖ከተውሒድ በኋላ ሶላትን አደራ ⛔

ረሱል صلى
الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

﴿أوَّلُ ما يُحاسَبُ بِهِ العبدُ الصلاةُ، وأوَّلُ ما يُقْضى بينَ الناسِ في الدماءِ﴾

“በቂያማ እለት በባሪያው ላይ መጀመሪያ ሂሳብ የሚደረገው ሶላቱ ሲሆን፤ በሰዎች መካከል መጀመሪያ ፍርድ የሚሰጠው የደም መፋሰስ ጉዳይ ነው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ፡ 2572

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

‼️ ነቢያዊ ምክር! ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦يَا عَائِشَةُ لَا تَرُدِّي الْمِسْكِينَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ، يَا عَائِ...
12/12/2025

‼️ ነቢያዊ ምክር!
ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

يَا عَائِشَةُ لَا تَرُدِّي الْمِسْكِينَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ، يَا عَائِشَةُ أَحِبِّي الْمَسَاكِينَ وَقَرِّبِيهِمْ ؛ فَإِنَّ اللَّهَ يُقَرِّبُكِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

"አኢሻህ ሆይ! ምስኪንን በባዶ አትመልሺ። የተምር ክፋይም (ስጥተሽ ) ቢሆን እንጂ። ዓኢሻህ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ። አቅርቢያቸውም። አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።"

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 2352

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

‼️ኢማም ሆነህ ስላትን ስታሰግድ🔸🔸ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህብለዋል፦ ﴿إِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِلنَّاسِ فَلْيُخَفِّفْ ؛ فَإِنَّ مِنْ...
11/12/2025

‼️ኢማም ሆነህ ስላትን ስታሰግድ🔸🔸

ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ
ብለዋል፦

﴿إِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِلنَّاسِ فَلْيُخَفِّفْ ؛ فَإِنَّ مِنْهُمُ الضَّعِيفَ، وَالسَّقِيمَ، وَالْكَبِيرَ، وَإِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِنَفْسِهِ﴾

“አንዳችሁ ሰዎችን የሚያሰግድ ከሆነ ቀለል ያድርግ (አያስረዝም)። በእነሱ ውስጥ ደካማ፣ በሽተኛና ባለጉዳይ ይኖራልና። አንዳችሁ ለብቻው ከሰገደ ግን የፈለገውን ያህል ያስረዝም።”

📚 ቡኻሪ (703) ሙስሊም (467) ዘግበውታል

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

✅  መልካምን ንግግር ተናገር 🎁ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إن أحدكم ليتكلّم بالكلمةِ من رِضْوانِ الله ما يظنّ أن تبلغَ ما ...
10/12/2025

✅ መልካምን ንግግር ተናገር 🎁

ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إن أحدكم ليتكلّم بالكلمةِ من رِضْوانِ الله ما يظنّ أن تبلغَ ما بلغتْ فيكتب اللهُ لهُ بها رِضْوانُهُ إلى يومِ يلقاهُ﴾

“አንዳችሁ የአላህን ወዴታ የሚያስገኝን ንግግርን ይናገራል ፤ በዚህም ንግግር ያልጠበቀውን ደረጃ ትደርሳለች ከአላህ ውዴታ ይፀፈለታል እሱን እስከሚገናኝበት ቀን ድረስ

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 2319

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

📌 አትበሳጭ! ከአላህ ጋር ተሳሰብ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما من شيٍء يُصيبُ المؤمنَ فى جسدِه يُؤذِيهِ، الا كفَّرَ اللهُ عنه من سيئاتِه﴾...
09/12/2025

📌 አትበሳጭ! ከአላህ ጋር ተሳሰብ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما من شيٍء يُصيبُ المؤمنَ فى جسدِه يُؤذِيهِ، الا كفَّرَ اللهُ عنه من سيئاتِه﴾

“በአንድ አማኝ ላይ በሰውነቱ ላይ አስቸጋሪ (አሳማሚ) የሆነ ነገር አያገኘውም፤ በሱ ሰበብ አላህ ወንጀሉን ቢያብስለት እንጂ።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2274

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

🌆 ዱኒያ ላይ ስትኖር እጥር ምጥን ያለች ቶሎ የምትከወን ብቻ እቅድ ይኑርህ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿كُنْ في الدُّنْيا كَأنَّكَ غَرِيبٌ أوْ عابِرُ سَبِي...
08/12/2025

🌆 ዱኒያ ላይ ስትኖር እጥር ምጥን ያለች ቶሎ የምትከወን ብቻ እቅድ ይኑርህ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿كُنْ في الدُّنْيا كَأنَّكَ غَرِيبٌ أوْ عابِرُ سَبِيلٍ.﴾

“ዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም ልክ እንደ መንገደኛ ሑነህ ኑር።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6416

II
ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram👉 t.me/EveryDayHadith99

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በየቀኑ 1 ሐዲስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share