24/05/2025
ለብዙ ሺህ አመታት አለምን በሀያልነት ሲያሸብሩ ኑረዋል። የአለምን ግዛት ለሁለት ከፍለው የፈለጉትን የአለማችንን ክፍል ህዝቦች ረግጠው ለበርካታ ዘመናት ገዝተዋል።
እነኚህ ሁለቱ ሀያላን ሀገራት በጦር አቅማቸው ተፎካክረው የአለምን የመሪነት ስልጣን ለመቀዳጀት ለ700 አመታት ከባባድ ጦርነቶችን በሁለቱ መካከል አካሂደዋል።
ሮም እና ፐርሺያ
የጦር አቅማቸው እጅግ የሰለጠነ እና ብዛታቸውም እልፍ አእላፍ ስለነበር ማናቸውም ሳይሸናነፉ 700 አመታትን ተፋልመዋል።
ለ7 መቶ አመታት የዘለቀው 1,000 የጦርነት ግጥሚያ ማብቅያ ጠፍቶለት ሀገራቱን በስጋት እና ፉክክር አከባብሮ አቆማቸው።
የነብይህ ሰሀባዎች ድንገት ባዶ እግራቸውን ከመካ በኢማን ወኔ ተሞልተው ወደነዚህ ሀያላን ግዛት ተጓዙ።
ለ700 አመታት የቆየውን የጦርነት ፉክክር ወድያ ትተው በ4 አመታት ሁለቱንም ሀያላን ሀገራት አንበረከኳቸው።
ምን ሆነ መሰለህ!
ያለሜዳቸው እና ያለ አቅማቸው ለጦር የተጓዙት ስንቅ አልባ ሰሀባዎች በ15 ግጥምያዎች ብቻ ፐርሺያን ሲያንበረክኩ ፤ ሮምን ደግሞ በ9 ግጥምያዎች በቁጥጥር አውለዋቸዋል።
ከሁሉም እሚገርመው በ 200,000 ዘመናዊ ሰራዊት የፀናን ስረወ መንግስት የረሱሉ ሰዐወ ደረሳዎች በ 15,000 ወታደር በ4 አመታት ብቻ መበታተናቸው ነው።
ክብር አይገባቸውም'ን?