16/04/2022
Motivational words for life
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Motivational words for life, School, Addis Ababa.
16/04/2022
የእድሜያችን ጉዳይ!
(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ ታሪክ)
የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን በጀመርኩባት በመጀመሪያዋ ቀን ፕሮፌሰራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ካስተዋወቀ በኋላ፣ እኛም በተራችን ሁላችንም እርስ በርሳችን እንድንተዋወቅ አበረታታን፡፡ ከወንበሬ ተነስቼ የምተዋወቀውን ሰው ለመፈለግ ወዲህና ወዲያ በማለት ቃኘት ሳደርግ ከጀርባዬ አንድ እጅ በስሱ ዳበስ አደረገኝ፡፡ ማን እንደነካኝ ለማየት ዘወር ስል ከፈገግታዋ የተነሳ ሁለንተናዋ የሚያበራ አንዲት ፊቷ እጅጉን የተጨማደደ በእድሜ የገፋች ሴት ነች፡፡
“መልከ መልካም ሆይ፣ እንዴት ነህ? ስሜ ሮዝ ይባላል፡፡ የሰማንያ ሰባት አመት ሴት ነኝ፡፡ እቅፍ አድርጌ ሰላም ልልህ እችላለሁ?” በማለት ያልጠበኩትን ሰላምታ አቀረበችልኝ፡፡
ፈገግ ካልኩኝ በኋላ በታላቅ ጉጉት፣ “በሚገባ” አልኳት፡፡ እቅፍ አድርጋ ሰላም ካለችኝ በኋላ ጊዜ ሳላባክን አንድ ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡
“ለምንድን ነው በዚህ ለጋና የዋህ እድሜሽ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የመጣሽው?” በማለት ቀለድኳት፡፡
እርሷም በቀልድ፣ “እዚህ የመጣሁት ሃብታም ባል ባገኝ ላገባውና ሁለት ልጆች ለመውለድ ነው” አለችኝ፡፡
“እየቀለድኩኝ እኮ አይደለም” አልኳት፣ በዚህ እድሜዋ ለትምህርት ያነሳሳት ምን እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎት ስላደረብኝ፡፡
“ሁል ጊዜ የኮሌጅ ዲግሪ እንዲኖረኝ ሕልሙ ነበረኝ፣ አሁን ጊዜው ደርሶ ይኸው ዲግሪዬን ልይዝ ነው” አለችኝ፡፡
ክፍለ ጊዜው ካለቀ በኋላ ወደ ተማሪዎች መዝናኛው ሕንጻው አቅጣጫ በቀስታ እየተራመድን የሚጠጣ ነገር ተገባበዝን፡፡ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከትምህርት ሰዓት በኋላ አብረን በማሳለፍ እንነጋገር ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ያካፈለችኝ በእድሜ ያገኘችው ጥበብና ልምምዷ እጅግ አስገራሚ ነበር፡፡
በቀጣዮቹ አመታት ሮዝ የትምህርት ቤቱ ታዋቂ ሴት ወደ መሆን መጣች፡፡ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በቀላሉ ወዳጆችን ታፈራ ነበር፡፡ ዝንጥ ብላ መልበስን ታዘወትር ነበር፡፡ ሴሚስተሩ መጨረሻ ላይ በነበረን የኳስ ጨዋታ ግብዣ ላይ ንግግር እንድታደርግ ጋበዝናት፡፡ ወደ መድረኩ ተጋብዛ ንግግር ስታደርግ ያስተማረችንን በፍጹም አልዘነጋውም፡፡
“መጫወት የምናቆመው በእድሜ ስላረጀን አይደለም፣ መጫወት ስላቆምን ነው የምናረጀው፡፡ ደስተኞችና ስኬታማዎች መሆን ከፈለጋችሁ፣ ምስጢራቱ ግልጽ ናቸው፡፡ በየቀኑ የሚያስቅ ነገር ፈልጋችሁ ማግኘት አለባችሁ፡፡ የምትከታተሉት ሕልም ሊኖራችሁ ይገባል፣ ምክንያቱም ሕልማችሁን ስታጡ ትሞታላችሁ፡፡ በዙሪያችን በርካታ ሰዎች ሞተው እንኳን እንደሞቱ አልገባቸውም፡፡ በማርጀትና በማደግ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ የአስራ ዘጠኝ አመት ወጣት ሆነህ አመቱን ሙሉ ምንም ሳትሰራ በአልጋ ላይ ካሳለፍክ ሃያ አመት ወደ መሆን መምጣትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ ሰማንያ ሰባት ዓመቴ ሆኖ አመቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ባሳልፍ፣ ሰማንያ ስምንት ወደመሆን መምጣቴ አይቀርም፡፡
በአድሜ መግፋት ለሁሉም የተሰጠ እውነታ ነው፡፡ እድሜን መቁጠር ምንም አይነት ልዩ ስጦታና ችሎታ አይጠይቅም፡፡ ለማለት የፈለኩት በሚከናወኑት የሕይወት ለውጦች ውስጥ ሁሉ ያለንን እድል በመጠቀም ማደግ ይኖርብናል ነው፡፡ እኛ በእድሜ የገፋን ሰዎች ያለፈውን ሕይወታችንን አስመልክቶ በአብዛኛው የሚኖርብን ጸጸት ስላደረግናቸው ነገሮች ሳይሆን ስላላደረግናቸው ነገሮች ነው፡፡ ማርጀትንና መሞትን የሚፈሩ ሰዎች ብዙ ጸጸት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡
በዲግሪ በተመረቀች በአንድ ሳምንት ውስጥ ሮዝ በሰላም ከዚህ አለም ተሰናበተች
like&share
Click here to claim your Sponsored Listing.