Suleyman ሱለይ Amharic fun and life quotes

Suleyman ሱለይ  Amharic fun and life quotes

Share

life .............the good life is one inspired by love and guided by knowledge .....suley?

Photos from Civil  Engineering's post 27/12/2021
30/11/2021
Photos from Wait's post 01/11/2021
01/11/2021

ኑሮ በዘዴ ኑሮ በዘዴ የተማራችሁ ኑሮ እንዴት ይዟችኋል ??

01/11/2021

ወዳጀ,,,,
🌀 አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
🌀 ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡

🌀 በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መሞከር ይኖርብሀል ፡፡

🌀 አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ

🌀 በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
-ዋልተር ባግሆት

🌀 ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
-ጂም ዋትኪንስ

🌀 ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
-አርል ኒተንጋል

🌀 ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ

🌀 ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር

🌀 ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
-አልበርት አንስታይን

🌀 አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
-ካርል ጉስታቭ

🌀 ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

✴ እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡ -ኮንፊሺየስ

✴ ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

✴ ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
-ሱዚ ካስም

✴ እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
-ብሩስ ሊ

✴ የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

✴ ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

✴ ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
-ሮቢን ሻርማ

✴ አለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
-ፖል ኮኢልሆ

✴ መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

✴ ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
-የማዎሪ አባባል

✴ 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
-ስኮት ቤልስካይ

✴ ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
-ያልታወቀ ሰው

✴ ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡

ሼርርርር
ብሩህ ቀን

01/11/2021

♦ስትቀርበው ለራቀ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:- ውድ ነገር ያለቦታው ርካሽ ነውና፥

♦ሥታምነው ለከዳህ አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ታማኝ በመሆንህ አሸንፈሃልና፥

♦ሥትፈልገው ባጣኽው ነገር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-እሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህና፥

♦ሥትወደው ለጠላህ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ሥንት ምርጥ ሠዎች አንተን የሚወዱ አሉና፥

♦ሥላልሆነው ነገር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ገና ከዚህ በኋላ የሚሆኑ ነገሮች አሉና፥

♦አጣዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ብታጣ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-አገኘዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ታገኘዋለህና፥

♦ያሠብከው ሳይሆን ቢቀር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ፈጣሪ ያላሠብከውን ይሠጥሃልና፥

♥ፍቅር ሥትሰጠው ፍቅር ለማይሠጥክ አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ምንአልባት ፈጣሪ ምርጥና ደሥ የሚል የፍቅር ታሪክ እየፃፈልክ ይሆናልና፥

!!
✅አንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ላንተ አልተፈጠረም!

✅ፈጣሪ ላንተ የሚያሥፈልግክን ያውቃል ያሠብከውን አሥጥሎክ ያላሠብከውን ይሠጥካል!

🔶️ሥላለፈው ብዙም አታሠላሥል፣
🔶️ሥለ ወደፊቱም አብዝተህ አትጨነቅ፣
🔶️ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ፤

✳✳አትጨነቅ✳✳

ይችም ቀን ታልፍና #ድሮ ትባላለች!
ሠአቷ ታልቅና #ታሪክ ትባላለች!
ሥለዚህ አትጨነቅ #በደሥታ እለፋት!
ነገም ሌላ ቀን ነው፣ህይወትህ ተሥፋ አላት።✅

መልካም ጁምዓ

Photos from I Like Share This's post 20/10/2021
Photos from ‎محمدز‎'s post 12/10/2021
Photos from ታሪክን ወደኋላ's post 02/09/2021
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Addis Ababa