Getinet Worku - ጌትነት ወርቁ

Getinet Worku - ጌትነት ወርቁ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Getinet Worku - ጌትነት ወርቁ, Addis Ababa.

ትናንት በእግሩ፣ ዛሬ በብሩ የሀገርን ገጽታ ግንባታ በትከሻው የተሸከመው ኃይለኛው ኃይሌብዙ ጊዜ ሺአለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ እንደርእስ አድርጎ መጻፍ እፈልግና ግን ያቅተኛል። እንጃ ቃላትን ይዘላ...
24/04/2026

ትናንት በእግሩ፣ ዛሬ በብሩ የሀገርን ገጽታ ግንባታ በትከሻው የተሸከመው ኃይለኛው ኃይሌ

ብዙ ጊዜ ሺአለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ እንደርእስ አድርጎ መጻፍ እፈልግና ግን ያቅተኛል። እንጃ ቃላትን ይዘላል።
ለእኔ "ኢትዮጵያውያን ዓለምን ረስተው፣ ዓለምም እነሱን ረስቶ ለሺህ ዓመታት ኖሩ(ተኙ)" ያለውን የታዋቂው እንግሊዛዊ የታሪክ ተመራማሪ ኤድዋርድ ጊበን(Edward Gibbon) አባባል/መርገም ከቀየሩ አንዱና ዋናው አድርጌ ነው የምቆጥረው።

የሩጫው ድል አንድ ነገር ነው፤ በየተረሱ አካባቢዎች እየሄደ በብሩ የሚሠራቸው ሪዞርቶች ለእኔ ውድ የኦሎምፒክ ሜዳሊያዎች ናቸው።

ከዚያ ደግሞ የሆቴል አገለግሎት ልሕቀትን የት እንዳደረሰው ኹለት ቀን በአንዱ ሆቴሉ ቆይቶ መውጣት በቂ ነው። የአያት ቤት እንጂ የሆቴል አገልግሎት ለማለት ይከብዳል።
ደ/ብርሃንን ከአጼ ዘርዓያእቆብ ቀጥለህ #አበራህላት!

(ታችኛውንና መካከለኛ ገቢ ደግሞ እንዲያማክል ቢደረግ)
*****
Disclaimer
የጊበን አባባል ላይ በተቃውሞ ጎራ የሚተቹና አውሮፓዊ ማግለል ነው የሚሉ አሉ።
ዘመነ መሣፍንት የተባለውን በድፕሎማሲ መነጠልና በውስጥ ቁርቁስ በተለይ ከአውሮፓውያን አንጻር የተነገረ መሆኑን ልብ ይሏል። በኢትዮጵያ ታሪክ አጻጻፍም የጨለማ ዘመን/Dark age" የሚባለው ከ7ኛው -16ኛው መ.ክ.ዘ ያለውን ጊዜ ነው። በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በዚኽ የማይስማሙ አሉ። ኢትዮጵያ በባህል፣ በሥነጽሑፍና በኪነጥበብና በሃይማኖታዊ(ክርስትናውም እስልምናውም) በኩል ያበበችበት ጊዜ ነውና። እነ ቅዱስ ላሊበላ በኪነሕንጻ፣ እነአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሥነጽሑፍና ሌሎችም ባህል ወግ ሃይማኖታዊ እሴችና ባህሎች ያበቡበት ጊዜ ነው። ብቻውን ብዙ ጥራዝ ያለው መጽሐፍ ስለሚወጣው ወደመጽሐፍት ግቡ። ለጊዜው አምሮት ማስታገሻ ቅንጭብ ንባብ እነኾ።
https://www.ethiopianreview.com/index/329

ስሙኝ የአስተሳሰብና ትርክት ልዩነት እንጂ ተራ ቂምና የተለመደው ዓይነት አፈና አይደለም!ብልጽግና "የወል ትርክት" በሚሉት አጥፊ መዶሻ ኢትዮጵያዊ እሴትን ሲንድ፣ ትዝታን ሲያጠፋና ወርዶ ወር...
16/04/2026

ስሙኝ የአስተሳሰብና ትርክት ልዩነት እንጂ ተራ ቂምና የተለመደው ዓይነት አፈና አይደለም!

ብልጽግና "የወል ትርክት" በሚሉት አጥፊ መዶሻ ኢትዮጵያዊ እሴትን ሲንድ፣ ትዝታን ሲያጠፋና ወርዶ ወርዶ የነጠላ ጥለት ሲቀድ በከረመበት ፍርስራሽ ላይኮ ነው ልጁ ብቅ ብሎ አዲስ የግንብ ጡብ የደረደረበትና የጥፋቱን ቋያ ውሐ የቸለሰበት። እና ቢከለክል ምን ይገርማል?! ዩቲዩብ ላይ ራሱ ድሮን አለመተኮሱ የማይቻል ቢኾንበት ነው'ጂ!

የረባም ዘፈን አድማጭ አይደለኹም። አንዱ ኹለቱ ግን እንደብሔራዊ መዝሙርና የቅኝ ግዛት ነጻነት የትግል ዜማ ዓይነት ነገር ይቃጣቸዋል ልበል?!

በዚኹ አጋጣሚ እንደ ባለዘይት ብቅ እያልክ ትውልዱን ከቁዘማና "አልቆልናል" መንፈስ ቁስል እየቀባህ ስለምትፈውስ ምሥጋናዬ ይድረስህ!

ምሶሶው ዘመም ጣራውም ያፈሳል
ሃገር የሞተበት የት ሄዶ ያለቅሳል
ባሳደገኝ ቀዬ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደሌለው ሃገር
ያቆምኳትን ሰንደቅ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ ባንዲራዬን ላንሳት...

ሆ ሆ..

 #የሺዋስ እንኳን ወደ ትብብራችን መጣህ! ከምንበተን ሰብሰብ ብለን እየተፍጨረጨሩ ነገን በተስፋ ማየት ያባት ነው። በትብብር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከገቡበት የሕልውና አደጋ እንታደግ!አዲስ...
14/04/2026

#የሺዋስ እንኳን ወደ ትብብራችን መጣህ!
ከምንበተን ሰብሰብ ብለን እየተፍጨረጨሩ ነገን በተስፋ ማየት ያባት ነው።

በትብብር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከገቡበት የሕልውና አደጋ እንታደግ!
አዲስ አበቤ ካርድህን ያዝ!

ዛሬ በትንሣኤው ከመብላት መጠጣቱና ቤተሰባዊ ደስታው በላይ ከፖለቲካ እሥረኞች ጋር እናሳልፍ ብለን 7 የምንደርስ የትብብሩ አመራሮች ቂሊንጦ(እነአቶክርስቲያን፣ አቶ ዮሐንስ፣ ዶ/ር ወንደሰንና ...
12/04/2026

ዛሬ በትንሣኤው ከመብላት መጠጣቱና ቤተሰባዊ ደስታው በላይ ከፖለቲካ እሥረኞች ጋር እናሳልፍ ብለን 7 የምንደርስ የትብብሩ አመራሮች ቂሊንጦ(እነአቶክርስቲያን፣ አቶ ዮሐንስ፣ ዶ/ር ወንደሰንና ሌሎችም) እና ቃሊቲ ካሉ እሥረኞች ጋር ውለናል።

የኾነ ዓይነት የሕሊና እረፍት ይሰማል። በዚያው ልክ የእነመሥከረምን ሕጻናት ልጆች እናታችን ሳትመጣ ትምህርት ቤት አንሄድም፤ እሷ ጋር እየሄድን እንዋል ወይም አምጡልን የሚለውን ልብ ሰቅዞ የሚይዝ ጥያቄ መፍታት ባለመቻሌ ከፍተኛ አቅመቢስነት እየተሰማኝ ተመልሻለኹ።

እንግዲኽ ፈጣሪ ያሳያችኹ። እነዚኽ ያውም ከፋም ለማም በታወቀ መንግሥት ተይዘው በተንዛዛ ፍትሕ ድፍን ሦስት ዓመት የኾናቸው ናቸው። ደብዛቸው የማይታወቅ እነ ገነት አራጌን ስታስቡ ደግሞ ከንፈር ያደርቃል፤ ደም ግፊት ይጨምራል።

ኢትዮጵያ ሆይ ትንሣኤውን ሳታሰልሺ በየዓመቱ እያከበርሽ የትንሣኤው ጌታ ትንሽማ ጭላንጭል የዴሞክራሲ ብርሃን ይፈንጥቅልሽ።

ዝርዝር ትብብሩ ጽፏል
***
https://www.facebook.com/61581001423218/posts/122135347959033380/

12/04/2026

በውስጥም በውጭም ለምትኖሩ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችኹ አደረሰን!
ባልተመቸ ኹኔታ የምታሳልፉትንም አስበናችኋል!

 ፤ ወዲኽም ጨለማን ከመርገም ቁራጭ ሻማ ማብራት!±±±±±ለትንሳኤ ሙክት ልትገዙ አስባቸኋል? ቅርጫም ገብታችኋል?! ግንኮ በርካታ የምሥራቅ አርሲ ምሥኪናን በዚህ ጊዜ የበግ/የፍየል ሙክታቸውን...
06/04/2026

፤ ወዲኽም ጨለማን ከመርገም ቁራጭ ሻማ ማብራት!
±±±±±
ለትንሳኤ ሙክት ልትገዙ አስባቸኋል? ቅርጫም ገብታችኋል?! ግንኮ በርካታ የምሥራቅ አርሲ ምሥኪናን በዚህ ጊዜ የበግ/የፍየል ሙክታቸውን እያወጡ የሰባውን ይሸጡ ነበር፣ ነበር! ግን ምን ዋጋ አለው ተዘርፈዋል፤ አባታቸውም በግፍ ተገድሏል፡፡ እናታቸውም የድረሱልኝ ድምጽ ስታሰማ አልማሯትም፡፡ ያ 8 እና 10 ቤተሰብ የነበረው፣ እህል በጎተራ የሚያስቀምጥ፣ ጋሸ ተብሎ ሙክቱን እየነዳ የሚሸጠው፣ የበርካታ ጥማዶች ባለቤት ሙሉ ቤት ፈርሶ ሕጻናት ልጆቹ ሜዳ ላይ ወድቀዋል፡፡ እኛ ግን አኹንም እየቆዘምን ነው፤ ለመፍትሔውም ሩቅ ነን፡፡

እና ምን እናድርግ መሰለህ? ለፋሲካ እርድ ያሰብነውን የድሎት ሙክት ለዚኽ ዓመት እንተወው፤ ከኢድ የተረፈችንን ጥቂት ጥሪት ለዘካ እናድርጋት በረከት እናግኝባትና ለእነዚያ ባዶ ሜዳ ላይ ያለአሳዳጊ ለቀሩ ሕጻናት ተስፋ እንኹናቸው፡፡ በረት ባይሞሉም በግ ተከትለው ሲጠብቁ ይዋሉ፣ ትራባልኛለች፣ ትበዛለች፣ ከችግርም እወጣለሁ እያሉ ተስፋ ያድርጉ እስቲ፡፡ ከዚህ በላይ እንባ ማበስ አለ?!

ከታች ከእነለጇ የምታይዋት በግ ለፋሲካ እርድ የታሰረች ሳይሆን በቅርቡ ለማየትም ለመስማትም በሚዘገንን መልኩ የተገደሉት አረጋዊ ካህን ልጆች(8 ቤተሰብ ነው) ማጽናኛ የተገዛች ናት፤ ዋጋቸውም 14,500.00፡፡ እንዲኹ እናት አባታቸው ተገድለው ሜደ ላይ ለወደቁ ለሌሎችም አንድ የርቢ በግ እያስገዛን እያጽናናን ነው፣ ዋጋው ከ 12ሺህ - 15ሺህ ነው፡፡ ይኽን ልብ የሚያሞቅ፣ የሐዘንተኞቹን እንባና ቁስል በጥቂቱም የሚያክም በጎ ተግባር በአቅም እናግዝ እስቲ፡፡

በእርግጥ አንድ ቀን ፍትሕ ሲሰፍን መንግሥት ካሳውን ይከፍላል፡፡ ግን እየቆዘምንና ጣት እየጠቆምን ከምንቆይ እየሠራን፣ ድምጻችንን ጎላ አድርገን እናሰማ!
የመሪባን ውሐ እንደማጣፈጥ፤ ወዲኽም ጨለማን ከመርገም ቁራጭ ሻማ እንደማብራት ውሰዱት!

ከልጆቻችሁ ጉሮሮ ነጥቃችሁ፤ እኛንም አምናችሁ በበጎ ተግባር የተሳተፋችሁ በውስጥም በውጭም ያላችሁ ደጋጎች መሪር ሐዘንን ያርቅላችሁ!
ሰላም ለሀገራችን

Address

Addis Ababa
251

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getinet Worku - ጌትነት ወርቁ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Getinet Worku - ጌትነት ወርቁ:

Shortcuts

Share