ነፃነት ተገኜ /ነፂ ነኝ/

ነፃነት ተገኜ /ነፂ ነኝ/

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ነፃነት ተገኜ /ነፂ ነኝ/, Addis Ababa.

Photos from North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/'s post 14/02/2023
08/02/2023

ከ 14 ሺህ ሄ/ር በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑ ተገለፀ !!

የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እንደ ሀገር የሚያመጣውን በጎ ለውጥና በኢኮኖሚው ዘርፍ ተገዳዳሪ አቅም ለመገንባት ለግብርናው ዘርፍ ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት በመስጠት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ተገኘ አባተ ገልፀዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያን በምግብ ራሳችንን ለመቻልና ከተረጂነት ለመውጣት ዓላማ ያደረገ ሲሆን አርሶ አደሩ የሥራ ባህል ከመቀየር ባለፈና፤ ሰብልን በበጋ መስኖ ማምረት እንደሚቻል እየተሄደበት ያለው ለሃገር እድገት ወሳኝ ነው።

በ2015 በጀት ዓመት በዞኑ 20,000 ሄክታር መሬት በመለየት በበጋ መስኖ ስንዴ ዘር ለመሸፈንና 720,000 ኩንታል ምርት ለማገኘት አቅዶ ወደ ስራ በመግባት 14,017 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ዘር የተሸፈነ ሲሆን 5281.6 ኩ/ል ምርጥ ዘርና 12,455 ኩ/ል ማዳበሪያ በመጠቀም 64,506 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

የቴሌግራም አድራሻ :-
https://t.me/northwollopp

የፌስቡክ አድራሻ :-
https://www.facebook.com/officalNorthwolloprosperityparty

የቲውተር አድራሻ :- https://twitter.com/NW_prosperity?t=8P1fPW-5HNcs7tKaY3vxvw&s=09

የዩቲዮብ አድራሻ :-
https://youtube.com/

05/02/2023

የሩጫና የሙዚቃ ኮንሰርት መርሐ-ግብሩ ተራዝሟል። (ወልድያ ከተማ)

በወልድያ ከተማ ነገ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም "ለወልድያ እሮጣለሁ ክለቤን እደግፋለሁ" በሚል መሪ ቃል ሊካሄድ የነበረውና ሰዓታት የቀሩት የሩጫ ውድድር እና የሙዚቃ ኮንሰርት መርሐ-ግብር ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር በጦርነት ምክንያት የተጎዳውን ከተማ መልሶ ለግንባት እና ሕዝቡን ከቁዘማ ለማውጣት ከአንድ ወር በፊት የተያዘው እና ሀገር አቀፍ አትሌቶች እና አንጋፋ የሙዚቃ ተዋንያኖችን ጭምር ሊሳተፉበት የነበረው የጎዳና ላይ ሩጫ እና የሙዚቃ ኮንሰረት መርሐ ግብር ሰዓታት ቢቀሩትም በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት ለሌላ ጊዜ መራዘሙንና መርሐ-ግብሩ የሚካሄድበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም

28/01/2023

"የአማራን ሕዝብ ማኅበራዊ ረፍት በመንሳት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት መቼም ሊሳካ አይችልም" የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ግርማ የሽጥላ

ከሰሞኑ በምሥራቅ አማራ ሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች የፀጥታ ችግር አጋጥሞ ቆይቷል። ይህን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ግርማ የሽጥላ በደረሰው የፀጥታ መደፍረስ ችግር የፀጥታ ኀይሎችና ንፁሃን ዜጎች መስዋእትነት ከፍለዋል ብለዋል።

አሁን ላይ የክልሉ መንግሥት በየደረጃው ካለው የፀጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት በመሥራት አካባቢውን ወደ ቀደመ ሰላሙ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ድረስ ተቋርጦ የነበረው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ ኀይሎች በዋናነት ደግሞ ሸኔ የተሰኘው የሽብር ቡድን ቀጣናውን ለማተራመስ ወቅት እየጠበቀ የሚያደርሰውን ጥፋት እልባት መስጠት የሚያስችል ኦፕሬሽን በተቀናጀ መንገድ ከሕዝቡ ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል።

"የአማራን ሕዝብ ማኅበራዊ ረፍት በመንሳት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት መቼም ሊሳካ አይችልም" ያሉት አቶ ግርማ በደረሰው የሰው ህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ሐዘን እንደተሰማው ገልጸዋል።

በጽንፈኝነት መሳሪያ ተጠቅመው የሕዝብ እልቂት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኀይሎችን ህልማቸውን ለማክሰም እየተሠራ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ብዝሐነት የሚገለፅበት ቀጣና የምሥራቅ አማራ ክፍልን እሳት በመለኮስ ችግር ለመፍጠር ሀገር አፍራሾች እየሠሩ መሆናቸውን እንረዳለን ነው ያሉት።

አካባቢውን ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስም ከሁለቱ ዞኖች ከተወጣጡ የሥራ ኀላፊዎች፣ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከአማራ ክልል የፀጥታ መዋቅር ጋር በአጣዬ ከተማ ውይይት ስለማድረጋቸውም ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ በቀጣይ መሠራት ስላለባቸውና በየጊዜው ሕዝቡን ረፍት በመንሳት ርካሽ የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱትን ጽንፈኛ ኀይሎች እልባት ለመስጠት በሚቻልበት ሁኔታ መክረናል ብለዋል።

"ከምንም በላይ ሕጋዊ ተጠያቂነት እንዲመጣ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ ሥራ እየሠራ ነው" ያሉት አቶ ግርማ የደረሰው ጥፋት ከፍተኛ ቢሆንም አጥፊዎችን በሕግ አግባብ ለመጠየቅ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኀይሎች ተመጋጋቢ ሥራዎችን በመስራት አካባቢውን የጦርነት ቀጣና ለማድረግ ሌት ከቀን እየሠሩ ስለመሆኑ እንገነዘባለን ያሉት አቶ ግርማ ይህንን በውሉ በመረዳት የክልሉ መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት እየሠራ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የቀጣናው የጸጥታ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ ለማድረግም ክልሉ ማድረግ ያለበትን ሁሉ ይሠራል ብለዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብ ተረጋግቶ በቀጣናው ለተሰማራው የፀጥታ ኀይል አጋዥ ተግባር እንዲፈፅምም ጥሪ አቅርበዋል።

•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~

28/01/2023

# ለኢትዮጵያና ለአፍሪካዊ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት በሚል መሪ ቃል ከ50 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ ተዘጋጀ !!

በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የሚገኙ የወጣቶች ሊግ አባላት እና ደጋፊዎች በብልፅግና የወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ አቅጣጫዎች በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ከጥር 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም 50 ሺህ ወጣቶች በላይ የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ መዘጋጀቱን አቶ ግርማ ጥጋቡ የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የወጣቶች ሊግ ሀላፊ ገልፀዋል።

በመድረኩም የወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ ውሳኔዎች በዝርዝር አባላቶችና ደጋፊዎች በንቁ ተሳትፎና ባለቤትነት በመምከር ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ አንድነትን ለመገንባት የላቀ ሚና ማበርከት፣ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት በወንድማማችነት የሚያጎለብት፣ የወጣቶችን አህጉራዊና አለም አቀፋ ተሳትፎ ሚናን ለማሳደግ ግንዛቤ በመፍጠር ለውሳኔዎቹ ተግባራዊነት የጋራ ሀላፊነታችን እንዲወጡ ኃላፊዉ ለወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።

•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

የቴሌግራም አድራሻ :-
https://t.me/northwollopp

የፌስቡክ አድራሻ :-
https://www.facebook.com/officalNorthwolloprosperityparty

የቲውተር አድራሻ :- https://twitter.com/NW_prosperity?t=8P1fPW-5HNcs7tKaY3vxvw&s=09

የዩቲዮብ አድራሻ :-
https://youtube.com/

Photos from Amhara Prosperity Party /APP/'s post 24/01/2023
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa