01/10/2025
ነብስ ይማር ወገኖቻችን
በምንጃር ሸንኮራ የአረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ግንባታ ርብራብ በመደርመሱ ከባድ አደጋ ደረሰ!
የሞትና የአካል ጉዳት አጋጠመ
ምንጃር ሸንኮራ፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን በደረሰ ከባድ አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉንና የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አረጋግጧል።
የአደጋው መንስኤ፣ ለቤተክርስቲያኗ ፊኒሺንግ ሥራ ተብሎ ተረብርቦ የነበረ የእንጨት ግንባታ (ርብራብ) መደርመስ ነው።
የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑርላህ ከድር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በሰጡት መረጃ፣ አደጋው የተከሰተው ቤተክርስቲያኗ ዓመታዊ የማርያም ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የንግስ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደና ሰዎች የግንባታውን ሂደት እየጎበኙ በነበሩበት ወቅት ነው።
* ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ወዲያውኑ አልፏል።
* ርብራቡ የተጫናቸው ሌሎች ተጎጂዎችን ከፍርስራሽ ስር የማውጣቱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጸመው መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።
©️ኢትዮ ኤፍ ኤም
💔💔💔
18/04/2025
የፋሲካ በዓል ዋዜማ ምን ተብሎ ይጠራል?
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: https://t.me/Amhara_Banksc
ማሳሰቢያ
👉🏽 የተሳታፊዎች መልስ ተቀባይነት የሚኖረው በቴሌግራምና የፌስቡክ ገጾቻችን አስተያየት መስጫ ሳጥን ብቻ ነው።
👉🏽 ተሳታፊዎች መጀመሪያ የቴሌግራምና የፌስቡክ ገጻችንን መቀላቀል አለባቸው፡፡
👉🏽 ትክክለኛውን መልስ ቀድመው የመለሱ የመጀመሪያዎቹ 5 ተሳታፊዎች ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
👉🏽 የተስተካከለ ምላሽ (Edited) ተቀባይነት የለውም ፡፡
👉🏽 አሸፊዎች ሽልማታቸውን ለመውሰድ የአማራ ባንክ አካውንት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
👉🏽 አንድ ተወዳዳሪ ከአንድ ጊዜ በላይ ተሸላሚ መሆን አይችልም፡፡
👉🏽 ደንብ እና ግዴታዎች ተፈጻሚነት አላቸው ፡፡
—————————————————————
ጥያቄ እና መልሱ ቀጣይነት ስለሚኖረው በንቃት በመሳተፍ ይሸለሙ!
#አማራባንክ
09/03/2025
እቺን የቴዲ አፍሮ ግጥም በጣም ነው ምወዳት ❤
ሹመቴን መልሱ /ቴዲ አፍሮ/
ጎራው ያለ እደሆን ባላምባራስ ደስታ
ዘራፍ ያለ እንደሆን ባላምባራስ ደስታ
ጠላት ይጠፋዋል መደበቂያ ቦታ።
ፊት አውራሪ ፍላቴ
ግራ አዝማች በሃፍቴ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች በአካሉ
ዣንጥራር ቧያለው
ደጃዝማች እንዳለው
እንዲህ ነው ካልቀረ አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘመት።
የጣልያን ጄኔራል ኮኮቡን ደርድሮ
በሊጋባ ሞዜር ስንት አሳሩን ቆጥሮ
ድል አድርጎት የኛ ሰው ፎክረን በኩራት እንደተመለስን
ስልጣኔ መስሎን የሱን ስም ወረስን።
ሟቹ ጄኔራል ነው ገዳይ ፊት አውራሪ
ስም እንዴት ይዋሳል ደፋር ሰው ከፈሪ
በጠላት ሬሳ ላይ ቆመን እያቅራራን
በድላችን ማግስት የኛን ሹመት ንቀን ከሆንን ሌተናል
ባናውቀው ነው እንጂ የዛን ቀን ሞተናል።
ኮነሬል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ጄኔራል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ፈረንጅ አደለንም ሀበሻ ነን እኛ።
የሞች ስም አይደለም የገዳይ ሰው ምሱ
በደም ተበላሽተዋል ባለ ኮከብ ልብሱ
ገድዬው ሳበቃ ባስታጠቁኝ ወኔ
በሱ ስም አይጥሩኝ ቆሞ እንዲሄድ በኔ
ጄኔራል ድል ሆኖ ስላለፈች ነፍሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።
ፊት አውራሪ ካታካምቦ
ሊጋባ ዴሊቦ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች አካሉ
ዣንጥራር አበጋዝ
እንዲህ ነው አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘመት
ፍቃድዎ ከሆነ ግርማዊ ተፈሪ
እንዳገሬ ሹመት በሉኝ ፊት አውራሪ
በሟች ከመጠራት ስለሚሻል እሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።
03/09/2024
ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
እንኳን ለቅዱሱ አባታችን ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሰን !!!
⛪️ ቅዱስ ዮሴፍ አጠራራቸው ከከበረ እስራኤላውያን መካከል የሆነ፣ የእመቤታችን ጠባቂ የነበረ ጻድቅ ሰው ነው
⛪️ ደጉ ሽማግሌ ምንም ቢያረጅም እመቤታችንን ለማገልገል አልደከመውም
➻ አብሯት ግብጽ ድረስ ተሰዷል
➻ ረሀብ፣ ጥማቷን፣ ጭንቅ፣ መከራዋን ተካፍሏል
➻ ኢየሱስ ክርስቶስን በማሳደግ ደክሟል
❤ የትውልድ ዘመን በ፴ /30/ ዓ.ዓ
❤ የትውልድ ቦታ ቤተልሔም፣ እስራኤል
❤ የአባት ስም ያዕቆብ
❤ የእናት ስም ዮሐዳ
❤ ሥራ ጻድቅ
❤ በዓለ ንግሥ ሐምሌ ፳፮ እና ግንቦት ፳፬
❤ የእረፍቱ ቀን ሐምሌ ፳፮
የቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ በረከትና ምልጃ አይለየን። በጸሎቱ ያስበን። አሜን።
#ተዋህዶ
#ኢትዮጵያ
03/08/2024
🕯🕯
መድሃኒአለም ሆይ ፦ አንተ ቸር ስትሆን ንፉግ የሆንኩት እኔ አንተን ጌታዬ ማለቴ እንዴት ደፋር ብሆን ነው? በሽተኛ የሆንኩ እኔ መድሃኒት አንተን የገፋሁ ምንኛ ብኩን ነኝ? እንግዲህስ አባቴም ብዬ እንዳልጠራህ የአባትነት ክብርን አልሰጠሁህም ፡ ጌታዬ ብዬም እንዳልጠራህ አንተን መፍራቴ አልፀናም ፡ ነገር ግን ልጅ ምንም በአመፃ ቢኖር ደግ አባት የልጁን መመለስ ይናፍቃልና አንተ እኔን እንደምትወደኝ አውቃለሁ ስለእኔ መልካም ግብር ያይደለ ስለአንተ የፍቅርህ ብዛት ልጄ ትለኛለህና አመሰግንሃለሁ።
ደሃን የሚያቀርብ ማነው? ክፉ ደሃንስ ማን ያቀርባል? ፀባዩ የከፋ ደሃንስ ማን ወደቤቱ ይጋብዛል? የሚሰርቅ ሌባ ችግረኛንስ ማን ባልንጀራ ያደርጋል? እኔ እንዲሁ ነኝና፦ ምንም የሌለኝ ደሃ ሃጢአትን የማደርግ ደሃ ፡ ፍቅር የሌለኝ ደሃ ፡ በሃጢአት አንተን የማሳዝን ችግረኛ እኔ ነኝና ፡ እንግዲህ እንዲህ ላለ ሰው ወዳጁ ማነው? ለተናቀ ፡ ለተጠላ ፡ ለደከመ ደጉ ሳምራዊ የሚሆነው ማነው? ከአንተ በቀር ፡ አንተ የሁሉን መመለስ ትወዳለህና ፡ አንተ የሁሉን መዳን ትወዳለህና ስለፍቅርህ ተስፋ ይቆይልኛል፡፡ ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡ አሜን፡፡"
"አቤቱ ፥ ስለስምህ ህያው አድርገኝ ፤ ስለፅድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት "። መዝ 142(143)÷11
27/07/2024
ጽናቱን ይስጥልን 😢
ልብ ሲያዝን ሲከፋው
የሚያድርገው ነገር ሲጠፋው
ከሰው ሰው ሲጎል በሀዘን በመከራ
ወደ እውነቱ መንገድ አምላክ እየመራ
ወንድምህ በስቃይ ህይወቱን ሲቀማ
ታለቅሳለህ ታዝናለህ ውስጥህ እየደማ
እህቴ አይዞሽ ሆድሽ አይባባ
አምላክ አለ አይንሽ አያንባ
ምህረቱን ያወርዳል በቸርነቱ
አምላክ ይቅር ባይ ነው በእውነቱ
🙏 🙏 🙏
በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቼ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶኛል!
ጽናቱን ይስጥልን 😢