ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን፣አደረሳችሁ።
መልካም የገና በዓል!!!!
Voice of Ethiopian Lecturers VEL
Voice of Ethiopian Lecturers (VEL) is a platform for Ethiopian University lecturers and Professors.
የወደፊቱ የሀገር ተረካቢዎች የተማረው ማህበረሰብ በችግር ሲሰቃይ እያዩ ስለሆነ ከአሁኑ ትምህርት በቃን እያሉ እየተውት ነው። ተፋ ተፋ፣ስርቆት፣ዝርፊያ፣ግድያ፣እገታ፣ስድት የትውልዱ ምርጫ እየሆኑ ነው። ከአሁኑ መፍትሄ ካልተበጀለት የወደፊቱ ከአሁኑ እጅግ የከፋ ነው።
15/07/2025
ቀልዳቸው አይጠገብም!!!!
ሀገራችን በያዝነው አመት ታምር የሆነ እድገት አስመዝግባለች(ጠቅላይ ሚኒስተሩ)፣አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ከስራ ሲወጣ ቡሌ እየለመነ ይመገባል፣ስለዚህ እጅግ ከባድ ድህነት ውስጥ ስለሚገኝ ግብር ይቀነስለት(ካሳሁን ፎሎ)፣ ሀገራችን ለታማኝ እና ድሀ መንግስት ሰራተኛ ከዚህ በላይ ግብር መቀነስ የምትችልበት አቅምየላትም( ገንዘብ ሚኒስተር)፣ሀገራችን በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለች መገመት አይከብደንም። ቡሌ እየለመነ የሚበላ ሰራተኛ በስርዓት ያስተናግደኛል፣ያገለግለኛል ብለህ የምታስብ የሀገሬ ህዝብ በፍፁም እንዳታስበው።
ከቁሳዊ ልማት በፊት ሰብአዊ ልማት ይቅደም!!!!!
እየተራብኩ አልመግብም!!!!!
15/07/2025
ሰላም!!!!!
የመምህራን ጥያቄ የዳቦ ጥያቄ ነው። በልተን ሀገራችን እና ህዝባችን እናገልግል ነበር። መንግስት ተብየው ደግሞ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በጥያቄዎቻችን ላይ መቀለድ ስራው ከሆነ ሰነባብቷል። እየተራቡ ህዝብን ማገልገል ፈፅሞ የማይታሰብ ጉዳይ ነው። ስለዚህ እየተራበ ህዝብ የሚያገለግል ትውልድ አለ ብሎ ማሰብ በሀገር ላይ መቀለድ ነው። በተራበ ምሁር የሚማር ትውልድ መጨረሻው ውድቀት፣ድንቁርና፣ችግር እና ድህነት መሆኑን በደንብ ሊታወቅ ግድ ይላል። ስለዚህ ልጆቸ ተገቢውን እውቀት ያገኙልኛል ብሎ የሚያስብ ሁሉ የእኛን የዳቦ ጥያቄ ሊደግፋ ይገባል።
ሁላችንም ወይ በጋራ ታግለን መብታችን እናስከብር ካልሆነ የተሻሉ አማራጮችን ፈልገን ራሳችን ከችግር እናውጣ!!!!!
አሁን በቅርቡ ከሚፀድቀው በጀት አመት ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥያቄዎች ታሳቢ አልተደረጉ ከሆነ ከቀጣይ አመት ጀምሮ ለውጥ ሊያመጣ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች እንደሚደረጉ መንግስት ሊያውቅ ግድ ይለዋል። በዚህ ምክንያት ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሀላፊነቱም መንግስት እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያወቅና ሊረዳን እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን ሊቆም ይገባል። ሁሉንም እንቅስቃሴዎቻችን ለህዝብ ይፋ የምናደርገው በቀጣይ ለምናደጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎቻችን ላይ አሁን ላይ ለምን እንዲህ ማድረግ አስፈለግ የሚል የማህበረሰብ ጥያቄ እንዳይነሳ ለማስገንዘብ ስለተፈለገ እና ህዝብም ጥያቄአችን የዳቦ ጥያቄ ብቻ እንደሆነ ህዝባችን እንዲያውቅልን ስለምንፈልግ ብቻ ነው!!!
ለአንድ የመንግስት ባለስልጣን በወር እስከ 100 ሺህ ብር የምትከፍል ሀገር ለምሁራን ሲሆን አቅም የለንም የሚል ማዘናጊያ መስማት አንፈልግም። ስለዚህ ወደ ስራ ማቆም አድማ ከመግባታችን በፊት የዳቦ ጥያቄዎቻችን ምላሽ ሊያገኙ ይገባል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ነገር ሀላፊነቱን የዩኒቨርሲቲ መምህራን የማንወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን። ሁላችንም በአንድነት የዳቦ ጥያቄዎቻችን ማስመለስ አለብን
ሰላም!!!
ሀገራችን እጅግ ታምራዊ በሚባል ደረጃ እያደገች ነው ተብለናል። ስለዚህ እንደ ዜጋ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር አጥብቀን መጠየቅ አለብን። ይህን ለማድረግ ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል።ትክክለኛ ጊዜው መቼ ነው? ኑ እንነጋገር? ሁላችንም መብቶቻችን ለማስከበር መታገል አለብን።
Click here to claim your Sponsored Listing.