ይግባኝ ለክርስቶስ

ይግባኝ ለክርስቶስ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ይግባኝ ለክርስቶስ, አዲስ አበባ, Addis Ababa.

21/05/2024

ክቡራን እና ክቡራት ተከታታዮቻችን ለጊዜው በዚህ ፔጅ ኢየተገናኝን ሀሳብ እንለዋወጣለን

25/01/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ መጠሪያ ።

፦፦፦ ብፁዕ ወቅዱስ ====== ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚለይበት

፦፦፦፦ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ==== ግብፆች የኢትዮጵያው ፓትርያርክ በተመሳሳይ መጠራት ስለሌለባቸው እንደአርመኑ ፓትርያርክ " ካቶሊኮስ" የሚል ይጨመር ብለው ሲጠይቅ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ግን በቋንቋችን በግእዙ እንሰጣችኋለን እሱን አጽድቁልን በማለታቸው " ፓትርያርክ " ከሚለው ቀጥሎ " ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ " ተብሎ ይጠራል ።

፦፦፦፦ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ===== ግሪኮች ወደአፍሪካ ጳጳስ ሾመው ሲልኩ " አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ( ፍሬ ምናጦስ ) የኛ ተዘላጅ ነው " በሚል ፈሊጥ የሚላከው ጳጳስ " ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም " ስለሚል አባ ሰላማ የኢትዮጵያ እንጂ የግሪክ አለመሆናቸውን ለመግለጽ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመን በፓትርያርኩ ስም ውስጥ እንዲካተት ተደረገ ።

፦፦፦፦ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ==== ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት ከመሾሟ በፊት ከግብፅ የሚመጡት ጳጳሳት ከመንፈሳዊው አገልግሎት በቀር አስተዳደራዊ ስራዎች የሚሰሩት በእጨጌዎች ነበር የመጨረሻው እጨጌ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ሲሆኑ ከፕትርክናቸው በፊት " ብፁዕ እጨጌ " ተብለው ይጠሩ ነበር ፤ ይህንንም ስም ለታሪክ እንዲቀመጥ እና እንዳይጠፋ እንዲሁም ጥንታውያን አባቶቻችን የግብፅ ጳጳሳትን ጫና ተቋቁመው ሃይማኖታችንን እንዳቆዩልን ለመግለጽ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ ስም ላይ ተደርቦ እንዲጠራ ተደርጓል ።

የኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክ መጠሪያ በአጭሩ ይህ ነው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ።

23/01/2024

ይህ ዜና ከዛሬ 9 ዓመት በፊት ኢሳት የዘገበው ነው ፤ በ9 ዓመቱም የጎንደር ሲኖዶስ ጸሐፊ እና የጎጃም ጠ/ስራ አስኪያጅ ሲሾሙ ይኸው ቤተ ክህነቱ ከድጡ ወደማጡ መጓዙን አፈጠነው ፤ " ለምን " ብሎ የሚጠይቅ ጠፋ ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ እጅግ አምርረው በሚጠሏት ሁለት መነኮሳት እጅ ወደቀች ፣አብዛኛው መንጋ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን የሁለቱ መነኮሳት ንግግርን ብቻ ኢየሰማ ነጎደ በምስራቅ ጎጃም ብቻ 8 ወረዳዎች በቅባት ተሿሚዎች ተይዘው አንድም ሰው ትንፍሽ እንዳይል ተደረገ ፣ ይባስ ብለውም ከምስራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም በ2015 ዓ/ም ምንም ዓይነት ፈሰስ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዳይስጥ ተደረገ ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን መንጋው በአባ አብርሃም ቂቤ ምላስ በመታለል መንጎዱን አላቋረጠም ።

አብዛኞቹን የትግራይ ፣ የወሎ እና የሸዋ ጳጳሳት ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ ስንጠይቃቸው የሚመልሱት መልስ " ሁለቱም የፖለቲካ አጀንዳ እንደሚያራምዱ እና ቤተ ክርስቲያኗን ኢየጎዱ እንዳለ እናውቃለን ነገር ግን አንዴ ስለተሾሙ 3 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ከመጠበቅ ውጪ አማራጭ የለንም " የሚል ምላሽ ነው የሚሰጡት ይህ ማለት " እኛ ያወጣነው ህግ ከሚሻር ቤተ ክርስቲያን ትፍረስ " እንደማለት ይቆጠራል ፤ ይኸው ዓይናችን ኢያየ በ2ቱ ድንፋታ እና ቂም በቀል ትፈራርስ ጀመረ ።

በመጨረሻም ኢሳትም ዜናውን ሳያስተባብል 9 ዓመት ሞላው ቤተ ክህነቱም ኢየተበጣጠሰ እዚህ ደረሰ ።

23/01/2024

፦ይህ ቆብ ወደኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ሀገሪቱም ቤተክህነቱም እንደታወኩ አሉ

፦ ይህ ቆብ ሊቃውንትን ያሳደደ ፣ እውነተኞቹን አገልጋዮች ያስገደለ ፣ ምንፍ*ናን ያስፋፋ ነው

፦ ይህ ቆብ በዓይናችን እናዳየነው በጆሯችን እንደሰማነው ጥቂቶቹን ባለሀብት ያደረገ ፣ አመንዝራነትን ያስፋፋ ፣ ሙስናን ህጋዊ ያደረገ ነው

፦ ይህ ቆብ ረድኤተ እግዚአብሔርን ያራቀ ፣ መንፈሳዊ አገልግሎትን ሥራ ያደረገ ፣ ሃይማኖትን ያጠፋ ነው

፦ ይህ ቆብ በኢትዮጵያ ጥፋትን እንጂ ምሕረትን ይዞ አልመጣም ፣ ኃጢአትን እንጂ ጽድቅን አላስተማረንም እናም ወደመጣበት ግብፅ ይመለስና እንደቀድሞው ሊቃውንቱ ቤተ ክርስቲያኗን ይምሯት ፣ ጵጵስናው ለገዳም አባቶች ብቻ ተሰጥቶ የሰሌን ቆባቸውን እንዳጠለቁ በየገዳሙ ሆነው ይጸልዩ አስተዳደሩን ባለሙያዎቹ ያስተዳድሩት ያለበለዚያ አሁን 3 የደረሰው መንበር የሚቀጥለው አመት 4 ላለመድረሱ ምንም ማረጋገጫ የለም ፤ ጳጳስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የሚለውን ተረት በኅብረት ሆነን እናስወግደው ።

23/01/2024

እመቤቴ ምስክሬ ናት ?

እኚህ ሰውዬ ከፍተኛ የሰው እንባ እንዳለባቸው ዛሬ ተረዳሁኝ ባህር ዳር ደርሰው ሲመጡ አዲስ አጀንዳ ይነሳል ከዚያም ህዝበ ክርስያኑን በመግለጫ ያደነቁሩታል ።

በነገራችን ላይ

የቀድሞው አቡነ በርናባስ በ1994 ዓ/ም ፣ የቀድሞው አቡነ ጴጥሮስ በ2004 ዓ/ም ተመሳሳይ እርግማን ረግመዋቸዋል እርግማኑም " የተቀመጥክበት ወንበር አይርጋልህ ጠዋት የተናገርከው ለማታ ማታ የተናገርከው ለጠዋት አይሁንህ ፣ የጠዋት ወዳጅ ማታ ይክዳህ ፣ የነካኸው አይባረክ ፣ " የሚል ነበር እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ? ይህንን የሰማሁት ባህርዳር ነው መቼም ሰውየው ውሸታም ናቸው እንጂ "ሁለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አረገሙኝም" ብለው መስቀል ይዘው ይማሉ እስኪ ።

ለዛሬ ይቆየን !!!

Photos from ይግባኝ ለክርስቶስ's post 23/01/2024

ሰበር ዜና

የፈራነው ይህንን ነበር ገና በአባ አብርሃም ዘመን ብዙ እናያለን

ዛሬ ጥር 14 2016 ዓ.ም የኦሮምያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖድዮስ መንበረ ጴጥሮስ ተመሰረተ

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ) _ ምስረታውን አስመልክቶም ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት ብጽህ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት መከልከላችን ይታወሳል ብለዋል።

በመሆኑም እንደሚታወቀው የቤተ ክርስትያኗን ዶግማና ቀኖና በተከተለ መንገድ ጥር 14 2015 አመተ ምህረት ሲመተ ጳጳስ መመስረቱንና ዬህም የብሄር ቤሄረሠቦች ብሄረሰቦችን ያካተተውን ሲመተ ጵጵስና በመቃወም መንግስትን በሀይል በሀይማኖት ሽፋን መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሲሞክሩ ተስተውሏል ተብሏል በመግለጫው።

መንግስትም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነት ስለነበረበት ነገሩ በህርቅ እንዲያልቅ ለማድረግ ወስኖ እኛም ተቀብለናል፤ ይሁንና መንግስትን በመሸንገል ሀምሌ 2015 ጥያቄያችን ተዳፍኖ አልፋፏል ብሏል መግለጫው።

ከዛሬ ዛሬ ይሻሻላል ብለን ብንጠብቅም ከቤተ ክርስትያኗ በሀይል አግልለውናል፥ በነጻነት የማምለክ መብታችንንም ነፍገውናል፥ የሚናፍቀንን ህዝብ ማገልገል አልቻልንም ያለው መግለጫው እንደሚታወቀው ሁሉም የራሱ ሲኖድስ አለው ሲል አክሏል።

ለትግራይ ተፈቅዷል የአማራም ህዝብም ሲኖድዮስ አለው ስለምን ኦሮሞ ህዝብ በራሱ ቋንቋ ማምለክ ይከለከላል ሲል መግለጫው አክሎ፣ ይሄ የሚያሳየው ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳየ እና ኦሮሞም በራሱ ሲኖዲዮስ የመገልገል መብት ያለው መሆኑን ሲኖዶሱ በመግለጫው ገልጿል።

ከዛም ባለፈ መንግስ ላይ ሞት የሚያውጅ ዘርን ከፋፎሎ የሚረግም በሀገሪቱ ላይ ጦርነትን ለሚያውጅ የ 5 ኪሎ ሲኖድዮስ መላም የኦሮሞ ህዝብ እንዳይገዛ ጥሪ እናስተላልፋለን ብሏል መግለጫው።

የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ምንም አይነት ቀለም ያለው ባንዲራም ሆነ ምልክት ስለሌላት በኦሮምያ ምድር ላይ የማንንም የፖለቲካ ፖርቲ ባንዲራ በቤተክርስትያን ሽፋን እንዳይውለበለብ፣ እንዳይሰቀል፣ እንዳይቀባ እናሳስባለን ያለው መግለጫው፣ አያይዞም የኦሮቶዶክስ ቀለሟና ባንዲራዋ የክርስቶስ መስቀል ብቻ መሆኑንም ጠቅሷል።

በመጨረሻም፣ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ፣ የኦሮምያ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ጥያቄው የህዝብ መሆኑን አውቆ ከሲኖዶሱ ጎን ይቆም ዘንድ መጠየቁን በመግለጫው ተጠቅሷል።

ሂሪያ ዱፌራ

23/01/2024

ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሳሕ ወንትሀሰይ ባቲ ።
ጥር 14 ፤ 2015 ዓ/ም የቤተ ክህነቱ የዘረኝነት እና የሙስና ጭንብል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋለጠበት ስለሆነ ሀቀኞቹ ኦርቶዶክሳውያን ዕለት ኅሪት ብለው ያከብሯታል ።

ፊውዳልዝም እና አሃዳዊነት ከቤተ ክህነቱ ጓዙን ጠቅልሎ እስኪወጣ ድረስ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን እናት እስክትሆን ድረስ ማናችንም ትግላችንን ልናቆም አንችልም ።

ምክንያት ከተባለ በጣጣጣጣጣጣም በአጭሩ

ጥንታውያን የአብነት ትምህርት ቤቶች ከሰሜን ኢትዮጵያ ውጪ እንዳይኖሩ ተዘግተዋል ።

ብቸኛ ሆኖ የቀረውን የደብረ ሊባኖስ ጉባኤ ቤት በጀት (የጥቂት ተማሪዎች ቀለብ) በ2015 ዓ/ም አባ አብርሃም" አለቅም " ብለው ማንገራገራቸውን እዚሁ ቤተ ክህነት ቁጭ ብለን ታዝበናል

መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ የፈረሰውን የታእካ ነገሥት በአታ ለማርያም ት/ቤትን በፌስቡክ በማጋራታቸው ከጠቅላይ ስራ አስኪያጁ ማስጠንቀቂያ አዘል ዛቻ በጆሯችን ሰምተናል ።

በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ በኦሮሚያ እና በደቡብ አህጉረ ስብከት ኮታ የአካባቢው ተወላጆችን ልኮ ከማስተማር ይልቅ የተማሪነት ኮታው በገንዘብ ኢየተሸጠ ከደብረ ማርቆስ እና ከምስራቅ ወለጋ ታላቅ እና ታናሽ ወንድማማቾች ሲላኩ ኢያየን ዝም ማለት ኃጢአት መሆኑን ስንጮህ ሰሚ ብናጣም ጥር 14 ፤ 2015 ዓ/ም የዚህንም ጭንብል ገፎታል ።

እናም ጥር 14፤ 2015 የቤተ ክርስቲያን አስተርእዮ ( የመገለጥ ቀን ) ስለሆነ ፣ ስንዴው ከእንክርዳዱ የተለየበት ቀን ስለሆነ ፣ የቤተ ክሀነቱ የዘር ፖለቲከኞች የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እነሱ ተደብቀው ምስኪኑን ምእመን ያታለሉበት ቀን ስለሆነ ነገን ለምናስብ እንደ ቤተ ክህነቱ ከበርቴዎች ቋንቋ ያቺ ዕለት ህገወጥ ሹመት የተፈጸመባት ሳትሆን በህጋዊ ስም የተሰገሰጉት አሀዳውያን የተጋለጠባት ዕለት ስለሆነች " ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሳሕ ወንትሀሰይ ባቲ " ብለን እናከብራታለን ።

Photos from ይግባኝ ለክርስቶስ's post 22/01/2024

በምስጢራዊዋ እና ጥንታዊቷ ከተማ ወንጪ የጥምቀት አከባበር ።

Photos from ይግባኝ ለክርስቶስ's post 21/01/2024

የቃና ዘገሊላ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በሰላም ተከብሮ ዋለ ።

በትናንቱ የጥምቀት በዓል ከባህር ዳር ሀገረ ስብከት በቀር በመላው ኢትዮጵያ የወንጌሉ ቃል ብቻ የተሰበከ ሲሆን በባህር ዳር ግን የተለመደው ዲስኩር በአባ አብርሃም ተነግሯል ።

Photos from ይግባኝ ለክርስቶስ's post 20/01/2024

የጥምቀት በዓል በመላው ኢትዮጵያ በሰላም ተከብሮ ውሏል ።

Photos from ይግባኝ ለክርስቶስ's post 19/01/2024

ከተራ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሁሉም የባህረ ጥምቀት ስፍራዎች በሰላም ተከበረ ።
በተለይም በጃንሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በዓሉ ሰላም ሊሆን የቻለው ሁከት ፈጣሪው ሰው ርቆ ስለሔደ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸውልናል ።

18/01/2024

በአባ አብርሃም ጥረት የጎጃም ካህናትን ብቻ ከሌላ አካባቢ ተወላጆች ለይቶ በአዲስ አበባ ለማበልጸግ ከቤተ ክህነቱ የተጣበቀው ዓባይ ባንክ አ.ማ ።
በቅርብ ቀን

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

አዲስ አበባ
Addis Ababa