16/05/2026
“ሶማሊ ክልል በታሪኩ ምርጡን የሰላምና እድገት አመታት እያሳለፈ ነው..”
👉 ከኢትዮ ኦብሰርቨር የተገኘ
በሶማሊ ክልል በዴሞክራሲ ሰላምና መልካም አስተዳደር ላይ የሚሰራው የካራማራ ግሩፕ ተወካይ የሆኑት አሊ አብዲ “A Region under Redemption: The 2026 Somali Region Election” በሚል ርእስ ዛሬ ለህመት በበቃው ዘሪፖርተር ላይ ባጋሩት ፁሁፍ በአንድ ወቅት የድህነት እና ግጭት ምሳሌ የነበረው ሶማሊ ክልል በሚያስደንቅ ለውጥ ላይ ነው ፤ በኢትዮጵያም የሰላም፣ ልማት እና ብልፅግና ምልክት እየሆነ መጥቷል…” ሲሉ አትተዋል፡፡
አሊ በተለይም የአዲሱን ዘመን እድገት፣ አካታችነት እና ተቋማዊ ግንባታ ከተመለከትን ያለፉት ስምንት አመታት ሶማሊ ክልል በታሪኩ ሰላማዊ የተባለውን ጊዜ እያሳለፈ የሚገኝበት ነው ሲሉ ይገልፁታል፡፡
አስተማማኝ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ዘላቂ መረጋጋት እና የፖለቲካ አካታችነትን በተግባር ያረጋገጠው የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ እና አመራሩ እነዚህ ማሳያዎች ለአዲስ የስልጣን ዘመን እንደገና ተመራጭ ለመሆን መሰረት ናቸው ብሎ ያምናል፡፡
በዚህ ክልል ተወልደው ላደጉ ሁሉ ያለፉት አስር አመታት ወሳኝ የታሪክ መታጠፊያ የሆነ ያክል ይሰማናል ያሉት ፀሀፊው - በአንድ ወቅት በግጭት እና ተገማች አለመሆን፣ ሲመሽ የሚዘጉ ከተሞችና ገበያዎች፣ ለጉዞ አደገኛ የሆኑ መንገዶች እና ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ቤተሰቦች ያመነቱ የነበሩበት ጊዜያት አሁን የሩቅ ትዝታ ይመስላሉ ሲሉም ነው ያስታወሱት።
ሆኖም ይላሉ ፀሀፊው ፣ ሆኖም ይህ ለውጥ በአንድ ጀምበር አልመጣም፡፡ ይህ ለውጥ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በመሩት እና የቀድሞውን ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ከስልጣን መስወገድን የጠየቀ የፖለቲካ ለውጥም ጭምር የተመዘገበበት ያ ደግሞ በሶማሊ ክልል ለአዲስ የአመራር ሀይል በር የከፈተበት ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ያ የለውጥ ጅማሮ የቀድሞውን የክልሉ ፕሬዘዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር (አብዲ ኢሌ) ከስልጣን ያስወገደ በምትኩም አቶ ሙስጠፋ መሀመድን ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት በኋላም ፕሬዘዳንት እንደሆኑ መንገድ የጠረገ አጋጣሚ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱት👇🏽
A region once mired in prolonged conflict and underdevelopment has undergone significant transformation, emerging as a symbol of peace, development, and