19/02/2023
5 አስገራሚ ዛሬዉኑ የሚተገብሯቸዉ ቀላል እና በፍጥነት ህይወቶን የሚቀይሩ የድርድር እዉቀቶች እና ጥበቦች
1 በህይወት ምን እንደምትፈልግ እወቀዉ
-በህይወታችን የምናገኘዉ የፈለግነዉን/የተመኘነዉን አይደለም፣ለመደራደር ፈቃደኛ የሆንበትን እና የተደራደርነዉን ነዉ የምናገኘዉ
-በድርድራችን ስኬታማ ሆነን የፈለግነዉን ለማግኘት ግልፅ ባለ ሁኔታ ምን እንደምንፈልግ እና የምንፍልገዉ ለማግኘት ምን ለመስጠት ዝግጁ ነን
-ብዙ ገንዘብ ማግኘት እፈልጋለሁ አንበል ምን ያህል ገንዘብ ግልፅ በሆነ መንገድ እንፃፈዉ
2 ሁሉንም ነገር እንደራደረዉ
-ትልቁ ህግ፣ ካልጠየቅን ምንም አናገኝም
-ከዛሬ ጀምሮ በሄድንበት ሁሉ ለምንገዛዉ ነገር ጥሩ ዋጋ እንጠይቅ/እንደራደር/ በመጠየቃችን ብቻ ከ5-10% ቅናሽ እናገኛለን
-ሁሉንም ነገር ስንገዛ መኪና፣ጌጣጌጥ፣የቢዝነስ ስምምነት ዉሳኔዉን ከሚወስነዉ ጋር ስንከራከር ትልቅ ቅናሽ እናገኛለን
3 የትኛዉም ቦታ ስንሄድ ለመደራደር ተዘጋጅተን እንዉኛጣ ተዘጋጅቶ የወጣ ያሸንፋል
-ከማን ጋር ነዉ የምደራደረዉ
-የምደራደረዉ ዉሳኔዉን ከሚወስነዉ ጋር ነዉ
-ውሳኔዉን የሚወስነዉ ምንድነዉ የሚፈልገዉ፣ለሱ ጠቃሚዉ ነገር ምንድነዉ፣ሁለታችንም ተጠቃሚ የምንሆንበት ድርድር እንዴት እንፍጠር
-በደንብ ካልተዘጋጀህ፣ለድርድሩ አልተዘጋጀዉም ብለህ ሌላ ቀጠሮ ያዝ
-በህይወት በጣም መጥፎዉ ነገር ምንም ሳትዘጋጅ ወደ ጦርነት ዘሎ መግባት ነዉ
4 ምንጊዜም አንተ ቁረጥ እኔ መርጬ አነሳለሁ የሚለዉን መርህ ተከተል
-ሁለት ልጆች ካሉህ እና ኬክ ለመካፈል ከተጣሉ እንዴት እንደምታካፍላቸዉ ከተቸገርክ አንደኛዉ ኬኩን ለሁለት እንዲቆርስ ሌላኛዉ ደግሞ መርጦ እንዲወስድ አድርጋቸዉ
5 ህይወት እና እዉነታ ድርድር ነች
-ትልቅ የመኖሪያ ቤት ትፈልጋለህ፣ አለም ልትሰጥህ ፈቃደኛ ነች ፣ለሱ የሚሆን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ ከሆንክ
-ተወዳጅ እና ደስየሚል ቤተሰብ መመስረት ትፈልጋለህ፣ለሱ የሚሆን ድርድር እና መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ሁን
-ሁሉንም የህይወትህን ክፍል መደራደር ትችላለህ
-ጥሩ ድርድር ጊዜ፣አቅም፣ጉልበት ይፈልጋል
-ምርጥ ስራ ትፈልጋለህ ፣ተደራድረህ አግኘዉ
-ከልጆችህ ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ትፈልጋለህ፣ ተደራድረህ አግኘዉ
-በህይወትህ ለምትፈልጋቸዉ ነገሮች በሙሉ ፣ መደራደር የምትችለዉ ሌላ ሰዉ አለ
-ህይወት ሁሌም ድርድር ነች