24/04/2026
إنا لله وإنا إليه راجعون إن العين لتدمع وإن القلب ليحزن وإنا على فراقك يا صديقي الأستاذ محمد سعيد لمحزونون
اللهم اغفر له وارحمه واجعل قبره روضة من رياض الجنة ولا تجعله حفرة من حفر النيران وارزق أهله الصبر والسلوان إنك
على كل شيء قدير وعبادك لطيف خبير
🤲
الفاتحة
06/04/2026
مهما وصفنا بالجمال نبينا
يبقى الجمال بوصفه يتجمل
21/02/2026
ከሰደቃ ሁሉ የተሻለው የረመዳን ሰደቃ ነው::
ለዚያውም ሐቅን ከባጢል መለያ ዲን ማስተማሪያ ማእከል::
ነገ ምሸት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 3:30 ጀምሮ ለውዱ መርከዛችን ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል ሁላችንም እንዘጋጅ::
03/12/2025
"እኛ የአሏህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"
إنا لله وإنا إليه راجعون.
የ ሸይኽ ዑመር አባ ቦፋ. ሸይክህ በሺር ሸይኽ ዑመር አባ ቦፋተሻገረዋል...........................................................
إن العلماء ورثة الأنبياء وإن الأنبياء لم يورثوا دينارا ولا درهما إنما ورثوا العلم
ዑለማዎች የነብያቶች ወራሾች ናቸው ነብያቶችም ዕውቀትን እንጂ ለዑመቶቻቸው ገንዘብን አላወረሱም። የሁሉም ነብያቶች እምነት የሆነዉን ኢስላምን በማስፋፋትና በማስተማር አይነተኛና የማይተካ ሚና ያላቸው ዑለማዎች ናቸው። ወደ አኼራ ያለፉትን የአሏህ እዝነት አይለያቸው ያሉትንም አሏህ ያቆይል አሚን። الفاتحة
19/10/2025
"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን" አል-ቁርአን
አባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ማዕከል ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማምሻውን አልፈዋል። አባታችን ሐያታቸውን ሁሉ ዕውቀትን በመፈለግና ተምሮ በማስተማር ላይ ያሳለፉ ከበርካታ ዑለማዎችን ዕውቀትን ሰንደው ለትውልድ ያስተላለፉ የሙስሊሙ ዑማ ብቻ ሳይሆን የሀገርም ባለውለታ የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸው።
አስ-ሱና ቲቪ በአባታችን ማለፈ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለመላው ሙስሊም ፤ ለቤተሰቦቻቸው ፤ ለደረሶቻቸው ፤ ለዕውቀት ጓዶቻቸው ብሎም ለመላው የሀገራችን ህዝብ መጽናናትን ይመኛል። አባታችን ቢያልፉም ስራዎቻቸውና የዕውቀት ፍሬዎቻቸው ሁሌም ሕያው ናቸው አሏህ በሰፊው ራሕመቱና እዘነቱ ያካባቸው መኖሪያቸውንም ጀነት ያድርገው አሚን።
....................................................................
إن العلماء ورثة الأنبياء وإن الأنبياء لم يورثوا دينارا ولا درهما إنما ورثوا العلم
ዑለማዎች የነብያቶች ወራሾች ናቸው ነብያቶችም ዕውቀትን እንጂ ለዑመቶቻቸው ገንዘብን አላወረሱም። የሁሉም ነብያቶች እምነት የሆነዉን ኢስላምን በማስፋፋትና በማስተማር አይነተኛና የማይተካ ሚና ያላቸው ዑለማዎች ናቸው። ወደ አኼራ ያለፉትን የአሏህ እዝነት አይለያቸው ያሉትንም አሏህ ያቆይል አሚን።
አስ-ሱና ቲቪ / As-Sunnah TV
04/09/2025
እንኳን ለታላቁ ነብይ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መውሊድ አደረሳችሁ። በነብዩ መወለድ መደሰት መታደል ነው። መውሊዱ በረከት የምናገኝበት መሐባ የምንጨምርበት እንዲያደርግልን አላህን እንለምናለን። ፍልስጤማዊያን ወንድሞቻችንን አላህ ነስሩን እንዲሰጣቸው ከልባችን ዱዓእ እናድርግ።
31/07/2025
ነብያችንን መውደድ ﷺ || የተጓዦች ስንቅ 🍂
بِسْمِ اللَّـهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
ቲርሚዚይ በሸማኢል ፤ ቃዲ ዒያድ በሺፋእ ፣ ቀስጦላኒይ በመዋሂብ ፤ ቡሲሪይ በሚሚየህ ፤ ሸይኽ አህመድ ሲራጅ በሙከረሙ ያብሰለሰሉት ዉዱን ነብያችንን ሙሐመድን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መሆኑ አይደበቅም።
የሐገራችን ማዲሆች “የማዶው” “የጦይባው” እንዲሁም “የረዉዳው” እያሉ ሲቀኙ አጥንትን ይሰረስራሉ ። ከልባቸው የሸሸጉትን ፤ ከሆዳቸው ያረገዙትን ፍቅር በስንኞቻቸው ሲተነፍሱት ልብን ይሰርቃሉ ። አይደለም ዉዱን ነብይ የሚያዉቃቸውን የማያዉቃቸውን ሰው በትዝታ ያሸፍታሉ ። የለበጣ ሳይሆን ፈንቅሎ እንዲያለቅስ ያስገድዳሉ ። ከአማርኛ ቅኔ አለፍ ብለው የዐረብኛ በላጋን ተንተርሰው የተሰደሩ የመድህ ስንኞች ሩህን ከስጋ መነጠል ልምዳቸው መሆኑ ከወንዘኛ ዘንድ ይታወቃል ።
የማዶዉ ሹም ከተወለዱ ፣ የኪስራ ጉልላት ከተደረመሰ ፤ ለሺህ አመታት የነደደው የፋርስ እሳት ከከሰመ እነሆ 1500 አመታት ተቆጠሩ ። ጨለማ ተገፎ ብርሃን ከተተካ 15 ክፍለዘመናት ነጎዱ ። “ሰው ነው አሉት እንጂ መቼ ነው እንደ ሰው” የተባለላቸው ዉዱ ነብያችን(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከእናታችን አሚናህ ለሰው ልጆች ከተበረከቱ 18 ሺህ ወራት ተከታተሉ ። የረቢዕ ወር ቆንጆዉ ነቢይ ለሰው ልጆች ከተበረከቱበት ከ531 ሺህ ቀናቶችን በላይ ተፈራርቀዋል ። እነሆ ይህ የተከበረው የረቢዕ ወር ሚሊኒየምን ተሻግሮ አምስት መቶ አመታትን ሊደፍን እያስገመገመ ይገኛል። ከሰው ልጆች አድርጎ ከፈጠረን በኋላ ቁርዐን ለተወረደላቸው ነብይ ዑመት ያደረገን አሏህ ዘመናትን ያዳረሰ ምስጋና ይገባው።
ከአፈጣጠር እስከ ስነምግባር አምሳያ ያልተገኘላቸውን ነብይ አለመውደድ እድለ ቢስነት ነው። ለምን ተወሱ ብሎ ምዕመናን ላይ ማንጓጠጥ ትልቅ ሙሲባ ነው። የሶፈር ወር ለረቢዕ ሰርገኞች ጉድ ጉድ ማለቻ ወር ነው። ረቢዕ ደግሞ አፍቃሪዎች ተኩለው የሚታዩበት ወር ሲሆን ለማፍቀር ያልታደሉት ደግሞ ተከፍተው የሚታዩበት የፀደይ ወር ነው ። ረቢዕ ለሙሂቦች ነፋሻማ ሲሆን ተቃርነው ለምን ብለው ለሚጠይቁ ሰዎች ደግሞ ቁረንን የሚዘረግፍ ዉርጫማ ወር ነው።
የነብያችንን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዉልደት ቀን(መዉሊድ) ማክበር በሸሪዐው ፍቁድ የሆነ ተግባር ነው። የሸሪዐዊ ትምህርትን በአግባቡ ለሰነቁ ፤ ፈኖችን ላዳረሱ ፤ የዑሱልን ትምህርት በአግባቡ ለተለሙ ሰዎች ፍቁድነቱ አይጋረድም ። በርግጥ ነብዩን የመውደድ ስጦታ ፈር በለቀቀ የቢድዐ አረዳዳቸው ለተነፈጉ ሰዎች የመዉሊድ ቃና ትርጉም አይሰጣቸውም ።
ለመሆኑ ነብያችንﷺ መውደድ ማለት ምን ማለት ይሆን ?
الحب هو صحابي جاء إلى النبي ﷺ فقال: متى الساعة يا رسول الله؟ قال: «وَمَا أَعْدَدْتَ لَهَا؟»، قال: ما أعددت لها من كثير صلاة ولا صوم ولا صدقة، ولكني أحب الله ورسوله، قال: «أَنْتَ مَعَ مَنْ أَحْبَبْتَ». قال أنس: فما فرحنا - أي أصحاب محمد ال - بشيء فرحنا بقول النبي: «أَنْتَ مَعَ مَنْ أَحْبَبْتَ»، قال أنس: أنا أحب النبي ﷺ وأبا بكر وعمر، وأرجو أن أكون معهم بحبيهم وإن لم أعمل بمثل أعمالهم.
ሶሐብዩ ወደ ነብዩ ﷺ መጣና "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የትንሳዔው ቀን መቼ ነው?" ሲል ጠየቃቸው። እርሳቸውም "ለእሷ ምን አዘጋጀተሃል?" አሉት። ሶሐብዩም "ብዙ ሰላት፣ ብዙ ጾም ወይም ብዙ ምጽዋት አላዘጋጀሁም፤ ነገር
25/06/2025
እንኳን አደረሳቹህ የተባረከ የነስር የክብረት የደስታ ካሰብነው ሁሉ ከፍ የምንልበት የሁለት ሀገር ክብረትን የምንወፈቅበት ያድርግልን።