04/05/2025
ይህ ሰው ከኦቶማን ኢምፓየር የመጨረሻው ወታደር እንደሆነ ይነገራል፣ ታዲያ በእድሜ ማምሻው ላይ የተከበረውን መስጀደል አቅሷ (ፍልስጤም) ይጠብቅ ነበር።
ከስፍራው እንዲያፈገፍግ ትእዛዝ ቢተላለፍበትም ትእዛዙን ተቀብሎ ወደ እናት ሀገሩ ተርኪዬ መመለሱን አልተቀበለውም ነበር።
ለምን ቦታውን ለቀህ ወደ ሀገርህ አትመለስም ብለው አጥብቀው ሲጠይቁትም እንዲህ ብሎ ነበር የመለሰላቸው:-
የነቢዩ ቂብላና 3ኛ ሐረም የሆነውን የተከበረ መስጂድ ለቅቄ ብሔድ ነቢዩ ያዝኑብኛል ብየ ፈርቸ ነው አላቸው!
እንደነኝህ አይነት ተራራ የሆኑ የዲን ዘቦችን እተካለሁ ብሎ የተነሳውን ወጠጤ ቡድን እና የነኝህን ታላላቅ ሰዎች ገድል ስንመለከት ልባችን እጅጉ ይደማል።
ፋቲሕ ሚዲያ / Fatih Media
03/05/2025
01/05/2025
28/04/2025