Zemedkun Bekele (ዘመዴ):
~ ሀገር አቀፍ ጥሪ
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ
አርክቴክቶች በሙሉ በያላችሁበት።
*~★★★~*
• ይነበብ ፥ በደንብ ይነበብ፥ ተመካከሩበት፣ ተነጋገሩበት፣ ተወያዩበት። ነጭነጯን ነግሬአችኋለሁ። ተንፒሱ !!
| ~ ጥሪው ለሌሎቹም ይቀጥላል።
•••
የሁለቱን ቅዱሳን ነገሥታት የአብርሃ ወአጽብሃን፣ የቅዱስ ላሊበላንና የጎንደር የአፄ ፋሲልን፣ አብያተ መንግሥታት ያነፁትን፣ እነ አዳዲ ማርያምን የፈለፈሉትን የአባቶቻችንን ልጆች በባትሪ ፈልጉልኝ። በዘመናችን ያሉ የኢትዮጵያ የሥነ ህንፃ ሊቃውንትን ባለማዕተቦቹን የተዋሕዶ ልጆች ከያሉበት ፈልጋችሁ ጥሩልኝ። ቤተ ጊዮርጊስን የፈለፈሉ እጆች አሁን ይፈለጋሉ።
•••
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ባለ ማዕተቦቹ አርክቴክቶች ሆይ ከወዴት ናችሁ። አለሁ በሉኝ። እስቲ ተጠራሩ፣ ተሰባሰቡ፣ ተሰባሰቡ። ተመካከሩ። ለሥራ ተዘጋጁ። ታሪክ ለመሥራት ተዘጋጁ። ወዳጆቼ መጪው ጊዜ ጨለማ አይደለም። ወገግ ያለ ደማቅ ብርሃን ነው። ፏ ያለ፣ ሽር ብትን የምንልበት ብርሃን። እርግጥ ነው። ጭቃ አለ። ጥቂት ጭቃ አለ። በጭቃው ላይ ግን የሚያበራ የፀሐይ ብርሃንም አለ። እግረ ፀሐይን እኮ የመሬት ቆሻሻ፣ የምድር ጭቃ አያቆሽሸውም። እኛ ፀሐይ ነን። ከእንቅብ በታች የማንቀመጥ ሻማዎች፣ ብርሃን ነን። እናም ተዘጋጁ። ከጸሎት ጋር፣ ደግሞም ከንስሃ፣ ራስንም ከመግዛት ጋር በየቤታችሁ ሆናች ተዘጋጁ። ንድፉን ንደፉ። ፕላኑን አውጡ። ተመካከሩ።
•••
አይሆንም ብለህ እንዳትንቀኝ። ይሆናል። ይፈጸማል። አውሮጳዊ ያልሆነ፣ አማሪካዊ ያልሆነ፣ የፓሪስ የሮምን የሥነ ህንጻ ጥበብ ያልተከተለ፣ ያልኮረጀ፣ በያንዳንዱ ተቋም ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ማንነት ገላጭ ነገር፣ የሚያንፀባርቅ እውነቷን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የህንጻ ንድፍ እስቲ ንደፉ።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ሆስፒታል ዲዛይን።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ትምህርት ቤት ዲዛይን።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የግዕዝ ዩኒቨርሲቲ።
• ግዙፍ የሆነ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መርጃ ማዕከል
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ባንክ
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ኢንሹራንስ
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ዜማና የሥነ ጽሑፍ የጥናትና የምርምር ማዕከል
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የመድኃኒት ቅመማና የዕጸዋት ምርምር ማእከል።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ህንጻ ጥበብ ትምህርት ቤት
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ሥዕል ትምህርት ቤት ዲዛይኖች ይዘጋጁ። በምን ገንዘብ፣ መቼ ሊሠሩ ወዘተረፈ ብቻ እንዳትሉኝ። ይዘጋጁ። ይዘጋጁ። ይዘጋጁ። ተናግሬአለሁ። አሻራህን ለማስቀመጥ ተዘጋጅ።
•••
አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሰዋ ወደ ሞርያም ተራራ ይዞት እየሄደ ነው። የይስሐቅን መሰዋት የይስሐቅ ወላጅ እናት አሮጊቷ ሣራ እንኳን አታውቅም። የሚሰዋው ይስሐቅም አያውቅም። አሽከሮች፣ የመንደሩ ነዋሪዎችም አያውቁም። ራሱ የሚሰዋው ይስሐቅም ጭምር አያውቅም። አብርሃምና እግዚአብሔር ብቻ ነበሩ የሚያውቁት።
•••
ይስሃቅ ጠየቀ። አባቴ ሆይ ቢለዋው ተዘጋጅቷል። እንጨቱ ተዘጋጅቷል። የመስዋዕቱ በግስ ከወዴት አለ? የመስዋዕቱን በግ ሳንይዝ እኮ ነው ወደ ሞሪየም ተራራ እየወጣን ያለነው። ምን አልባት አረጋዊው አባቱ በሽምግልና ምክንያት ከረሳው ብሎ ማስታወሱ እኮ ነው። አብርሃም ግን መለሰ። “ የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል” አለው። እውነትም በስተመጨረሻ በዕፀ ሳቤቅ ሐረግ የተያዘ
የመናፍቃን ድብቅ ምስጥር የOTC
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የመናፍቃን ድብቅ ምስጥር የOTC, College & University, Humora, Addis Ababa.
04/06/2020
25/04/2020
የ666ምልክቶች ከኢትዮጵያ ብር ተመልከቱ
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Humora
Addis Ababa
494549
Addis Ababa
494549