19/04/2026
ሃከሮች update ባልተደረጉ የዊንዶውስ የደህንነት ክፍተቶችን በመጠቀም ተቋማት ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው።
አንድ የሳይበር ደህንነት ተቋም እንዳስታወቀው፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ አንድ በደህንነት ምርምር ባለሙያ አማካኝነት በይነመረብ ላይ ይፋ የተደረጉ የዊንዶውስ የደህንነት ጉድለቶችን በመጠቀም፣ ጠላፊዎች ቢያንስ በአንድ ተቋም ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።
Huntress የተሰኘው የሳይበር ደህንነት ኩባንያ እንደገለጸው ጠላፊዎች BlueHammer፣ UnDefend እና RedSun የተባሉ ሦስት የዊንዶውስ የደህንነት ክፍተቶችን እየተጠቀሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል። የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ተቋም ማን እንደሆነና ጠላፊዎቹ እነማን እንደሆኑ እስካሁን አልታወቀም።
ሦስቱም የደህንነት ክፍተቶች በዊንዶውስ ውስጥ በሚገኘው Windows Defender anti-virus ላይ የሚከሰቱ ናቸው። እነዚህ ክፍተቶች ጠላፊዎች በአንድ ኮምፒውተር ላይ administrator ፈቃድ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ማይክሮሶፍት እስካሁን መፍትሔ (patch) ያወጣው ለBlueHammer ክፍተት ብቻ ሲሆን የቀሩት ሁለቱ (UnDefend እና RedSun) ገና ይፋ አልተደረገላቸውም።