26/07/2024
ተዋሕዶ ሐይማኖቴ
አስተማማኝ
26/07/2024
02/03/2024
መልካም በአል
02/03/2024
27/09/2022
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ
መልካም በአለል
12/09/2022
እንኳን ለዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም እና በፍቅር አደረሳች
ስለበአሉ ሙሉ ማብራሪያ በቴሌግራም ቻናል ያገኛሉ 👇👇👇
https://t.me/ethomereja/3104
ፈጥነው ይቀላቀሉ
መልካምበአል
11/09/2022
ዓመታትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ
( መዝ 65:11 )
የተሰጠንን በጎ ዓመት በበጎነት እንኖር ዘንድ በዘመን መለዋወጥ ውስጥ እኛ እየተለወጥን ያለፈውን ዘመን በመተው በአዲሱ ዘመን በአዲስ አስተሳሰብ ፡ በሰላምና በፍቅር በአብሮነት ሀገራችንን የምናገለግልበት ለቤተክርስቲያናችን ሕልውና አጥብቀን የምንሠራበት የበረከትና የንስሐ ዘመን እንዲሆንልን የዘመናት ባለቤት ቸሩ አምላካችን ፈቃዱ ይሁን ፡፡
በሃገር ውስጥ በውጭ ዓለማት የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አዲሱ ዓመት መንፈሳዊ ትርፍ የምናተርፍበት የበጎነት ዘመን ይሁልን ፡፡
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ
አዳማ /ናዝሬት
07/09/2022
#የ2014 ዓ/ም
ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላሳ መብለጥና ማነስ
የለበትም፤ ሁልጊዜ ሠላሳ ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2015 ዓ.ም = 9+21= 30
መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤
መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤
መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ
በየካቲት ይውላል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 21 ስለሆነ ከ14 ይበልጣል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በመስከረም ይዉላል፤
•••
ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ መስከረም 21 ሲሆን መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት (ዕለተ መጥቅዕ) ቅዳሜ ይሆናል፡፡
•••
መባጃ ሐመር= የዘመኑ መጥቅዕ + መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ በመጠቀም የሚገኘው ቁጥር ከ 30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን መባጃ ሐመር እንላለን፡፡
ልብ ይበሉ የዕለታት
ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
የቅዳሜ---8
የእሑድ---7
የሰኞ------6
የማክሰኞ--5
የረቡዕ------4
የሐሙስ----3
የዓርብ ------2 ነው
የዕለታት ተውሳክ የአመጣጥ ስሌቱም የሚከተለውን ይመስላል።
ከዕለተ መጥቅዕ ጀምረን እስከ ነነዌ ጾም መግቢያ ስንቆጥር 128 ቀን ይሆናል፡፡
በ30 ብንገድፈዉ 4 ደርሶ ቀሪ 8 ይሆናል፡፡ ይህም የቅዳሜ ተውሳክ ነው። በዚህ ዓይነት ስሌት ስንሄድ መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት
• ቅዳሜ ከሆነ ፡- 128፥30= 4 ቀሪ 8
• እሁድ ከሆነ፡127፥30= 4 ቀሪ 7
• ሰኞ ከሆነ፡ 126፥30=4 ቀሪ 6
• ማግሰኞ ከሆነ፡ 125 ፥30= 3 ቀሪ 5
• ረቡዕ ከሆነ ፡124 ፥30= 2 ቀሪ 4
• ሐሙስ ከሆነ ፡ 123፥ 30= 2 ቀሪ 3
• ዓርብ ከሆነ ፡122፥ 30= 2 ቀሪ 2
ስለዚህ የዕለታት ተውሳክ ቀሪዎቹን በመያዝ ይታወቃል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳክ በመደመር ነው።
መባጃ ሐመር= 21+8=29
መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 29 ይያዝና መጥቅዕ መስከረም ላይ ስለወደቀና መጥቅዕ የወደቀበት ዕለት ቅዳሜ ስለሆነ የዘመኑ መጥቅዕ 21 የቅዳሜ ተውሳክ 8 ድምር 29 ስለሆነ ጾመ ነነዌ ጥር 29 ቀን በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው።
• ጾመ ነነዌ፦ መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር በ30 ገድፈን እናገኛለን፡፡ይህ ጾም ተውሳክ የለውም የሚወጣውም በደረቅ መባጃ ሐመር ነው፡፡ ሌሎችን አጽዋማትና በዓላት
ተውሳካቸውን ጾመ ነነዌ የዋለበትን የቀን ቁጥር (መባጃ ሐመር)ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን ከ30 በታች ከሆነ ደግም ራሱን በመጠቀም እናገኛለን።
•••
፩፦ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀናት አሉ።
ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ይሆናል፡፡
፪፦ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡
41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11 የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፫፦ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡
62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና ተውሳክ ይሆናል፡፡
፬፦ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡
67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7 የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፭(5) ትንሳኤ በክፍል 3(፫) የመጨረሻው ክፍል ነገ ይቀጥላል
በቴሌግራም መቀላቀል ኦርቶዶክሳዊ መረጃያግኙ ሙሉ ባህረ ሀሳብ ያንብቡ ይረዱ ሠናፍቃን ለሚጠይቁት ጦያቄዎች መልስ ይስጡ በሊንኩ ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/ethomereja/3741
ፈጥነው በመግባት ይቀላቀሉ
03/09/2022
ብዙ ሼር ያስፈልጋል ይደረግ
ጥብቅ ማሳሰቢያ
****
ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበበ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""
ሰምኑን የቤተክርስቲያናችን ባልሆኑ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የቤተክርስቲያናችንን አርማ በመጠቀምና የቤተክርስቲያናችን ማህበራዊ መገናኛዎች በማስመሰል ልዩ ልዩ ዜናዎችን በመስራት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚሞክሩ ድረ ገጾች እየተሰራጩ መሆኑን ደርሰንበታል።
እነዚሁ ድረ ገጾች ላይም በተለይ የቤተክርስቲያናችን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት መግለጫ በማስመሰል የሚያስተላልፏቸው ዘገባዎች ሐሰተኞች ከመሆናቸውም በላይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስም የተከፈቱ የቲዩተርም ሆነ የፌስ ቡክ አካውንት የሌለ መሆኑን እየገለጽን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ በቤተክርስቲያናችን መገናኛ ብዙሃንና በሕዝብ ግንኙነት ድረ ገጾች ብቻ የሚያስተላለፉ መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ከነዚህ ህጋዊ የቤተክርስቲያናችን መገናኛ ዘዴዎች ውጪ የሚተላለፉ መልእክቶች ሁሉ የሐሰት መረጃዎች መሆናቸውን በመረዳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር ከተከፈቱ ሐሰተኛ የማኅበራዊ ድረ ገጾችራሱን በመጠበቅና ለክፉ ዓላማ ማሳኪያ ተብለው የተከፈቱ መገናኛ አውታሮችን እንዲጋለጡ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።
መረጃው ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር በማድረግ እንዲተባበሩን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።
የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
በቴሌግራም 👇👇👇
https://t.me/ethomereja
ፈጥነው ይቀላቀሉ
22/07/2022
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕከምና ከሀገር ውጪ እንደሚሄዱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡
ምእመናን በጸሎት እንዲያስቧቸው ጠይቀዋል፡፡
በመ/ር አቤል አሰፋ
(ኢኦተቤ ቴቪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም )
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሕክምና ከሀገር ውጪ መጓዝ ማሰባቸውን በማስመልከት ዛሬ ከብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለኢኦተቤ ቴቪ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው በአስቸጋሪ የጤና ሁኔታ መቆየታቸውን ጠቅሰው ከሀገር ውጪ ለመታከም ማሰባቸውን ገልጸዋል፡፡ በተቻለ መጠን የተለየ ችግር ካልገጠማቸው ከ አንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ በመንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ሀገርና ስለወገን እየጸለዩ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንዲቆዩ ጠይቀዋል፡፡
የዐይን ሕክምና ጨምሮ ሙሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው አስኪመለሱ አባቶችና ምእመናን በጸሎት ያስቡኝ ያሉት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ክብር አስጠብቀው ሥራቸውን በኃላፊነት እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል፡፡
ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕክምና ሊሄዱ እንደነበር የተናገሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታቻዎች ባለመመቻቸታቸው እንደቆዩ ገልጸው አሁን ግን ነገሮች ስለተስተካከሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው እስኪመለሱ ምእመናንና ካህናት ተረጋግተው የሚጠበቅባቸውን ተግባር እያከናወኑ እንዲቆዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለበለጠ መረጃ👇👇👇👇በቴሌግራም
https://t.me/ethomereja
ይቀላቀሉ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Telephone
Website
Address
Addis Ababa