17/11/2020
የአማራ ጦር ወልቃይትን ሲቆጣጠር የፋሲል ደሞዝ አስገራሚ ንግግር ወልቃይት እና ሁመራ አስገራሚው የአማራ ጦር ጀብድ
Adresing technology based information
17/11/2020
የአማራ ጦር ወልቃይትን ሲቆጣጠር የፋሲል ደሞዝ አስገራሚ ንግግር ወልቃይት እና ሁመራ አስገራሚው የአማራ ጦር ጀብድ
09/11/2020
28/05/2020
የቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ሳይማሩ እንደማይመረቁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሳይማሩ እንደማይመረቁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።
ለሳይንስና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑና በስራ ላይ ያሉ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ከመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል።
የሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር በቴክክኖሎጂ ትምህርት ማስቀጠል ባለመቻሉ ተማሪዎች ሳይማሩ አይመረቁም ብለዋል።
“በቴክኖሎጂ የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ማስቀጠል ከሞላ ጎደል አልተቻለም፤ እያንዳንዱ ተማሪ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ የሚማረውን እያነበበ፤ ምዕራፍ በምዕራፍ፣ ሞጁል በሞጁል ተምሮ ምዘና እየተደረገለት አልቆየም።
በዚህ ረገድ ያልመጣን፣ የትምህርቱን ይዘት ያላጠናቀቀን ተማሪ ተምሯል ብሎ ወስዶ፤ ይህንን ኮርስ ጨርሰሃል፣ በዚህ መልኩ ተገምግመሃል እና ይህንን ውጤት አግኝተሃል ብሎ ውጤት ሰጥቶ ማስመረቅ በትምህርትም በአሰራርም ወንጀል ነው፤ መሰል አካሄድ አይፈቀድም፤ እንደዚህም አይሆንም!” ብለዋል።
የድህረ ምረቃ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር በቴክኖሎጂ ማድረስ በመቻሉ ይመረቃሉ ከሚል ድምዳሜ ተደርሷል።
ሆኖም የቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምረቃ በኮቪድ 19 የስርጭት መጠን የሚወሰን እንደሆነ ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፤ ይህም የምረቃ ዓመታቸውን ተገማች የማያደርገው ነው።
ሁሉም ሊባል በሚቻል ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸው መሰረተ-ልማት ለቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርትን በቴክኖሎጂ ማድረስ የማያስችል ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል።
በ2012 የትምህርት ዘመን የቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውም ለዚሁ ነው፤ ተማሪዎቹን እንደማያስመርቁ ከወዲሁ ያስታወቁ አሉ።
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፤ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ፈጽመው እንዳይርቁ በሚል በተለያዩ መንገዶች ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ሲሰራ መቆየቱ የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አያኖ በዳሶ፥ በሁሉም መርሃ ግብር ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶች የመማር ማስተማር እያቀረበ ቢቆይም፣ በዚህ ዓመት ሊመረቁ የነበሩ የቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን እንደማያስመርቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የ2012 ቅድመ-ምረቃ የመደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎችን እንደማያስመርቅ ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ከቅድመ-መደበኛ የ2012 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች የመደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች ብቻ የማይመረቁ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በሌላ በኩል በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከውሳኔ ላይ አልደረሱም።
የገጽ ለገጽ ትምህርት ሲቋረጥ የሁኔታዎች ትንተና ሰርተናል ያሉት፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ፥ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ ተመልሰው በአጭር ጊዜ መርሃ-ግብር የመጨረስ ዕቅድ ቢኖረንም የኮቪድ 19 ስርጭት ነባራዊ ሁኔታ ይወስነዋል ብለዋል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምረቃ ላይ ወጥ አቋም እያንጸባረቁ አይደለም። ሆኖም፤ የኮቪድ 19 ስርጭት የተገታ እንደሆነ ግን ተማሪዎችን በአፋጣኝ ወደ መደበኛ መማር ማስተማር ሂደታቸው የመመለስ ዕቅድ እንዳላቸውም ገልፀዋል።
ተማሪዎች በሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በየሚማሩባቸው ተቋማት የተዘጋጀላቸውን የትምህርት ቁሳቁስ በማንበብ እየተዘጋጁ መጠበቅ አለባቸው የተባለውም ለዚሁ ነው።
በርስቴ ፀጋዬ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
28/05/2020
እግዚአብሔር ዐረገ
አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። መዝ ፵፮ ፡ ፭።
ዐረገ ማለት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ ማለት ነው።
በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ ማለትም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ዕሪና (መብለጥ ማነስ የሌለበት መተካከል) ያመለክታል። ይህም የሥልጣን እኩልነት የመንበርን አንድነት ይገልጥልናል። የአብ የመንፈስ ቅዱስ መንበር እርሱ የወልድም መንበር ነውና። ከፍና ዝቅ ያለ ዙፋን የለም። ኹለትና ሦስትም አይደለም። አንድ ብቻ ነው እንጅ።
ዐረገ ስንል ጌታችን ስለተዋሐደው ሥጋ ክብር እየተናገርን እንደኾነ እንወቅ። ቅድመ ዓለም በቃልነቱ የወልድ ስፍራው ይኸው ነው። ስፍራው ያልነው ልዕልናውን መኾኑ ይታወቅ። ድኅረ ዓለምም ከልዕልናው ለቅጽበት ዝቅ አላለም። ስፍራውን አልለቀቀም።
በዚያ መንበር ተቀምጦ የማያውቀው ሥጋ ነበረ። በተዋሕዶ ከበረ ስንል ትስብዕት (ሥጋ) ወደዚህ የልዕልና ደረጃ ከፍ አለ ማለታችን ነው። ይህም በማኅፀነ ድንግል ቃል ሥጋ ሲኾን የተደረገ እንጅ ፴፫ ዓመት ከ፫ ወር ጠብቆ የደረሰበት አይደለም። ተዋሐደ ማለት ከኹለት አንድ ኾነ ብቻ ሳይኾን ከበረ ማለትም ነውና። ሰው አምላክ ኾነ ከማለት የሚተካከል ሌላ ምን ክብር አለ?
በጌታ ልደት የዘመሩት ቅዱሳን መላእክት በሰማይም በምድርም ምስጋና ይኹን ያሉት ለምን ይመስላችኋል? ሉቃ ፪ ፡ ፲፬። እዚህ በምድር በእመቤታችን እቅፍ የሚያዩትን ሥግው ቃል ወደ ሰማይ ሲያቀኑ በዘባነ ኪሩብ በማየታቸው ነው። በምድር በትሕትና ስላዩት ያመሰገኑትን በሰማይ በልዕልና ስላዩት ተገረሙ። በምድር አመስግነው እንዳይፈጽሙ በሰማይ ይታያቸዋል። በሰማይ ብለው እንዳይቀሩ በምድር ይታያቸዋል። ስለዚህ በአንድ ጊዜ በምድርም በሰማይም ላለው ምስጋና አቀረቡለት።
ሥግው ቃል - ሰው የኾነው አምላክ (God The Incarnate) በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሥኖ በዚህ ዓለም ሲመላለስ ከየማነ አብ ከዘባነ ኪሩብ ሳይለይ ነው። የደቀ መዛሙርቱን እግር በጉልበቱ ተንበርክኮ ሲያጥብ ሥግው ቃል ከየማነ አብ ከዘባነ ኪሩብ ሳይለይ ነው።
ለዚህም ነው ራሱ ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው" ያለው። ዮሐ ፫ ፡ ፲፫። ይህን ቃል ሲናገር በምድር እንደነበረ ግልጽ ነው። ግን በዚያችው ቅጽበት የሰው ልጅ በሰማይ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እየተሠለሰ እየተቀደሰ ነበረ። ስለዚህ በዚህ በምድር አብሮን እያለ በሰማይ መኖሩን ነገረን።
ስለዚህ ዐረገ ሲባል በተዋሐደው ሥጋ ይዳሰስልን የነበረው ከእንግዲህ የማይዳሰስ ኾነ፤ ከእንግዲህ እናየዋለን እንጅ አንዳስሰውም ማለትን ያጠይቃል። ዐረገ ማለት ቦታ ለቀቀ አይምሰለን። እግዚአብሔር ሔደ፣ መጣ ቢባል ተሰወረ ተገለጠ ማለት እንጅ ምሉዕ በኩለሄ ነውና ወደየት ይሔዳል ወደየትስ ይመጣል? ሲሔድም ሲመጣም ቦታውን አይለቅቅም። ስለዚህ ሲመጣ ተገለጠ ሲሔድ ተሰወረ እንላለን።
ሥግው ቃል ዐረገ ሲባልም ከእንግዲህ፡-
- [ ] የሚከፍለው ካሣ የለም
- [ ] የትሕትና ሥራውን ፈጽሟል
- [ ] በኃይልና በሥልጣኑ ይገለጣል
- [ ] በመለኮታዊ ባሕርይው በቀደመ አኗኗሩ ይገኛል
- [ ] ብናየው እንጅ አንዳስሰውም ማለት ነው።
ሲመጣ የሰማነውን ሲሔድ ዐየነው። ርደት ያለበት ዕርገት የእርሱ ብቻ ነው። ቅዱሳን ቢያርጉ ወደ ማያውቁት አዲስ ቦታ ነው። ጌታ ግን ወደ ነበረበት ብቻ ሳይኾን ወደ አለበት ነው ያረገው። ለጌታ ዕርገት አዲሱ ነገር የእኛ ማየት ብቻ ነው።
ጌታችን ሲያርግ ቅዱሳን ሐዋርያትን ባርኳቸዋል። "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ" እንዲል። ሉቃ ፳፬ ፡ ፶-፶፩። የቡራኬ ቀን ነውና እኛንም ይባርከን። ስንባረክ ቡሩክ ሥራ እንሠራለንና። እነርሱ ሲባረኩ ሰግደውለታል። ሳይንበረከኩ መባረክ የለምና። በክርስትና ከፍ ለማለት ዝቅ ማለት ይቀድማል። ዝቅ ማለት በትሕትና። ቅዱሳን ጌታ ሲያርግ በሰቂለ ሕሊና በተመስጦ ልቡና ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር። ሥራ ፩ ፡ ፲። መባረክ ወደ ሰማይ ያሳያል። ስንባረክ ልባችንም መሻታችንም ከክርስቶስ ጋር ያርጋል። እኛ በእግረ ልቡና እርሱ በአካል።
ከፍ እንበል። የሚወርዱ መኖራቸው እኛን ከፍ አያደርገንም። ካለንበት በጥቂቱም ቢኾን ከፍ እንበል። ልዕልና ወዳለው መንፈሳዊ ሥራ ልቡናችንን እናሳርገው።
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ!
28/05/2020
‼️
!
ወንድሜ ዲ.ዳንኤል ክብረት በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም የተቋቋመ ገዳም ወይም ደብር የምታውቁትን ከቦታው መጠሪያ ጋር እድንጠቁመው ጠይቆናል።
በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም የተቋቋመ ገዳም አራት ቦታ ልጠቁም።
1.ምስራቅ ጐጃም ገንቦታ ወለቴ ገዳም፣
2.አዊ ዞን ዳንግላ ወንደፋይ ቀበሌ
3.ጎንደር-ደራ ወረዳ ቆራጣ ወለቴ
4.ሳጋ ወለተ-ጴጥሮስ ገዳም።
ቆራጣ ወለቴ ደራ ወረዳ በቆራጣ ቀበሌ በውስጥ ይገኛል።ቆራጣ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ከሀሙሲት ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 24 ኪ.ሜ.ርቀት ትገኛለች።ወይንም ከባሀርዳር ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በጣና ሐይቅ 3፡00 ሠዓት የባህር ላይ ጉዞ በኋላ በምራፈ ማርያም ቀበሌ ይገኛል።
ይኼ የሬማ መድሐኒዓለም ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም የተተከለው በዐፄ ይሥሐቅ (1406-1421 ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው።የገዳሙ መሥራች አቡነ ኖቭ ይባላሉ።
በቆራጣ ቀበሌ የሚገኘው ይህ ገዳም ባጋጠሙት የተለያዩ ችግሮች ፈራርሷል።በ17ኛው መክዘ እንደተሳሉ በሚነገርላቸው ሐይማኖታዊ ሥዕላት ደብዝዝዋል።
ገዳሟ በርካታ ቅርሶች አሏት። ወለተ ጴጥሮስ መቋሚያ፣ቆብና እጅግ ጥንተዊ የሆኑ የብራና መጽሀፍትን፣የአፄ ሠርፀድንግል አጽምና አልጋ፣የተለያዩ አባቶች እና ነገስታት አፅሞች ይጠቃሳሉ፡፡
ሁለተኛው በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም የተቋቋመ ገዳም አዊ ዞን ከዳንግላ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ 17 ኪ.ሜ ጉዞ በኋላ ወንደፋይ ቀበሌ የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ገዳም ትገኛለች።የጻቋ አጽም ያረፈው ከዚህ ቦታ ነው።
ሦስተኛው ገዳም ደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ወረዳ
በበርቁት እና ገና መምቻ ቀበሌ ሳጋ ወለተ ጴጥሮስ ገዳም ነው።ይኼ ቦታ የተሰወረችበት ነው።
አራተኛው በአዊ ዞን በዳንግላ ወረዳ ገንቦታ ወለቴ ገዳም ናቸው።
የእናት ውለታዋ ምንድነው?