26/12/2025
ቀድሞ ለነበረው የስፖርት ዜና የፎቶ ጥራት ይቅርታ እየጠየቅን ተጨማሪ ፎቶ እንሆ
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Meskereme primary school, School, Arat kilo, Addis Ababa.
26/12/2025
ቀድሞ ለነበረው የስፖርት ዜና የፎቶ ጥራት ይቅርታ እየጠየቅን ተጨማሪ ፎቶ እንሆ
26/12/2025
ቀድሞ ለነበረው የስፖርት ዜና የፎቶ ጥራት ይቅርታ እየጠየቅን ተጨማሪ ፎቶ እንሆ 17/4/2018ዓ.መ መስከረም
26/12/2025
ዜና መስከረም
የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች እግር ኳስ ቡድን የቅዱስ ገብርኤል ትምርት ቤት አቻውን አሸነፈ
በ17/04/2018ዓ.ም በወረዳ ደረጃ በተዘጋጀው የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወንድ ተማሪዎች እግርኳስ ውድድር የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች እግር ኳስ ቡድን የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብረኤል ት/ቤት አቻውን በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ሠባት ለአንድ አሸነፈ ፡፡
የስፖርት ዲፓርትመንት ተወካዮች እና አሰልጣኙ ቡድናችን በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ እና በሰፊ የጎል ልዩንት ማሸነፉ ለቀጣይ ጨዋታዎች ሰፊ መነቃቃት እና የማሸነፍ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻ ጨዋታው በት/ቤታችን በመደረጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ጨዋነት ቡድናቸውን የደገፉ እና ተጋጣሚ ቡድኑንብ በሰላም ተቀብለው መሸኘታቸው ተቋሙ ያለውን ስፖርታዊ ጨዋነት የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ የእስታፍ አባላት ገልጸዋል፡፡
ታህሳስ 17 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ
27/11/2025
ዜና መስከረም
የመስከረም ቅ/አ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አይሲቲ ክፍሉን በተሻለ መንገድ አደራጀ :-
የት/ቤታችን አስተዳደር ከአይቲ ክፍል አባላት ጋር በመሆን የት/ቤቱን አይ ሲቲ ክፍልን ከበፊቱ በተሻለ በማደራጀት ለመማር ማስተማሩ ምቹ በማድረግ ስራ አስጀምሯል።
መምህራን በኮንፒውተር የሚሰሩ ስራዎቻቸውን አይሲቲ ክፍል በመም ጣት መስራት የሚችሉ መሆኑን የክፍሉ ተጠሪ መምህርት ሔለን ወልዱ አስታውቀዋል።
ህዳር 2018
አዲስ አበባ
26/11/2025
ዜና መስከረም
የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ ቅድመ መደበኛ መምህራን ስልጠና ሰጠ፡፡
የት/ቤታችን አስተዳደር ከቅድመ መመደበኛ አስተባባሪ ጋር በመሆን ለቅድመ መደበኛ መምህራንና ለሚመለከታቸው አካላት በሁለቱም ቋንቋ በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ እና በሕጻናት አያያዝ ዙሪያ ስልጠና የሰጠ ሲሆን ስልጠናው በአቶ አብይ ተፋራ እና በሱበር ቫይዘር አበራ ደሬሳ በኩል የተሰጠ እና መምህራኑ ከሕጻናቱ ጋር ካላቸው የዕለት ከለት ግንኙነት አንጻር ለልጆቹ ዕውቀት ከማስጨበጥ በተጨማሪ የበኃሪ ቀረጻ ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለባቸው ይህን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ ስልጠናው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የተሰጠ መሆኑን የቅድመ መደበኛ አስተባባሪ መምህርት ኮኮቤ ደገፉ ገልጸዋል ፡፡
ህዳር 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ
25/11/2025
ዜና መስከረም
መስከረም ቅድመ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለመምህራኑ ስልጠና ሰጠ
የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በትምህርት መሻሳል ም/ርዕሰ መምህር ዕቅድ መሰረት ለት/ቤቱ የቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤትለሚያስተምሩ የሁለቱም ቋንቋ መምህራን በጥናትና ምርምር/ በሪሰርች/ አሰራር ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው የት/ቤታችን ክላስተር ሱፐርቫይዘር በሆኑት በአቶ አበራ ኤሬሳ የተሰጠ ሲሆን መምህራን በስራቸው የሚገጥማቸውን እና ተቋሙላይ ሚታዩ ችግሮች ካሉ ችግር ፈቺ ምርምር እንዲያደርጉ የሚረዳ ስለሆነ ሁሉም መምህር በንቃት ተሳትፏል፡፡
ህዳር 16 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ
06/09/2024
በመጨረሻ ተሳክቷል
የክፍለ ከተማችን ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ለት/ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች ዕውቅናና ሸልማት መስጠት ከጀመረበት ዓመታት ጀምሮ በለፉት ሦስት ዓመታት ት/ቤታችን ሦስተኛና እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘን ስራችንን እያሻሻልን ቆይተን ዛሬ ላይ በ2016ዓ.ም 98.38% በማምጣት 1ኛ ደረጃን በመያዝ ልዩ ተሸላሚ ሆነናል ለዚህ ውጤት በአንድም በሌላ አስጸዋጽዎ ለነበራችሁ ለትቤታችን ማኅበረሰቦች ውጤቱ የጋራ ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡ በቀጣይም ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የደንበኞችን እርካታ በማስቀጠል ውጤታችንን ለማስጠበቅ በምናደርገው ጥረት አጋርነታችሁ እንደማይለየን በማመን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ነሐሴ 30 ቀን 2016ዓ.ም
መስከረም ቅ/አ/አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
አዲስ አበባ
01/09/2023
ማስታወቂያ
03/08/2023
ለመስከረም አ/ሕ/የመ/ደ/ት/ቤት ለመምህራንና ሰራተኞች በሙሉ ዳማት የሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ በከተማዋ ባሉት ሶስት ካፓሶች በማስታወቂያው ላይ በተገለፁት የትምህርት ዓይነቶች በ20እና 25 ፐርሰንት ቅናሽ ለማስተማር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጾልናል በዚህ መሰረት መማር የምትፈልጉ ሁሉ በተጨማሪ ማጣራት የምትፈልጉትን በማስታወቂያው ላይ ባለው ስልክ ደውላችሁ በማረጋገጥ በት/ቤቱ ሰው ሐብት ቢሮ ድረስ በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
27/11/2015ዓ.ም
26/06/2023
ለመስከረም አጸ/ሕጻናት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ መልካም የእረፍት ጊዜ ይሁንላችሁ ለ2015ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች መልካም የጥናት እና የፈተና ጊዜ ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን። ሰኔ 2015ዓ
መልካም እረፍት ተማሪዎች