Ayesanaw abebe ስለ ተዋህዶ እንመሰክራለሁ

Ayesanaw abebe ስለ ተዋህዶ እንመሰክራለሁ [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]

ከጾመ ኢየሱስ ( ከዐቢይ ጾም ) - ትንሣኤ ፡፡ክፍል 33  ( ማቴ 26  ÷ 36 -  56 ) ፡፡ጌታችን በጌቴሴማኒ ሲጸልይ ፡፡በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ ...
06/04/2026

ከጾመ ኢየሱስ ( ከዐቢይ ጾም ) - ትንሣኤ ፡፡
ክፍል 33 ( ማቴ 26 ÷ 36 - 56 ) ፡፡
ጌታችን በጌቴሴማኒ ሲጸልይ ፡፡
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ ደቀ መዛሙርቱንም፡- ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመር።
ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው። ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፡- አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።
ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን። እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።
ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፡- አባቴ፥ ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን አለ። ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው። ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፥ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።
ማብራሪያ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፡- ቢቻልህ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ብሎ ወደ አባቱ ሲጸልይ ፡- ጽዋ ያለው ሞቱን ነው፡- ያንተ ፈቃድ ይሁን ማለቱ እኛም ከጸለይን በኋላ የለመንነው ሁሉ ይሁንልን ከማለት የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው ብቻ እንዲሆንልን ማስተዋል እንዳለብን ያስተምረናል ፡፡
በጸሎት መትጋት ወደ ፈተና እንዳንገባ ይረዳናል ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ በአይሁድ እጅ ስለ መያዙ ፡፡
ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፡- እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። ተነሡ፥ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል አላቸው።
ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ። አሳልፎ የሚሰጠውም የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።
ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና፡- መምህር ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው።
ኢየሱስም፡- ወዳጄ ሆይ፥ ለምን ነገር መጣህ? አለው። በዚያን ጊዜ ቀረቡ እጃቸውንም በኢየሱስ ላይ ጭነው ያዙት።
እነሆም፥ ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው። ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ። ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን?
እንዲህ ከሆነስ እንደዚህ ሊሆን ይገባል የሚሉ መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ? በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ፡- ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።
ማብራሪያ
ለሐዋርያነት የተመረጠው ይሁዳ ጌታችን ኢየሱስን ወዳጅ መስሎ ሳመው ፡፡ ለሠላሳ ብር ብሎ ክርስቶስን አስያዘው ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያዝ ያላስቻለው ጴጥሮስ ሰይፉን መዝዞ ሊይዙት ከመጡት አንዱን ጆሮውን ቆረጠው ፡፡ በዚህ ወንጌል ጴጥሮስ መሆኑ ባይገለጥም በሌላ ወንጌል ወንጌል ጴጥሮስ መሆኑ ተልጦአል ( ዮሐ 18 ÷ 10 ፡ 11 ) ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ግን ሰይፍ ማንሳት ተገቢ አለ

06/04/2026
እወሰነት ነው
30/09/2021

እወሰነት ነው

Amen Amen Amen
10/06/2021

Amen Amen Amen

29/05/2021

Address

Addis Ababa

Telephone

+251931336388

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ayesanaw abebe ስለ ተዋህዶ እንመሰክራለሁ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Ayesanaw abebe ስለ ተዋህዶ እንመሰክራለሁ:

Shortcuts

Share