የሙስሊም ተማሪዎች ኢስላማዊ መድረክ

16/12/2025

ቁርአን #ሙስሊም #ቁርአን

ታላቁ ሰው አልፈዋል። አላህ ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃቸው። ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን እመኛለሁ።إنا لله وإنا إليه راجعون
20/10/2025

ታላቁ ሰው አልፈዋል። አላህ ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃቸው። ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን እመኛለሁ።

إنا لله وإنا إليه راجعون

19/09/2025

ሁሉም ሙስሊም የተባለ ሊያውቀው የሚገባ ዱአ ።

አሚን አላሁ አሚን ። #ሙስሊም ゚viralシfypシ゚viralシalシ

19/09/2025

እውነተኛ ማሪ ከአላህ በስተቀር ማን አለ ።

19/09/2025

ከአቃጆች ሁላ ምርጡ አቃጅ አንድ አላህ ብቻ ነው #ረሱልና #አቡበክርም #አልይን #ዑስማንን #ዑመርን #ነብዩም #በዱኒያ #አላህም

16/09/2025

♦️ #ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው #በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች
አየተጨዋወቱ እያሉ #ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አባ በከር አንተ #በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው
ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።
#አቡበክርም ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣
2.አንቱን ማየት፣
3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
#ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
#ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
#አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣
#ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣
በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣
ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
#ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ
"አንቱ #የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ
#ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ #ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ
ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-
" #አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-
#በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።
#አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!
°
ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ።
ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል!
ኢንሻ አሏህ!!
#አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!
اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد ﷺ💚❤️

ለፕሮፋይል የሚሆን ውብ የአላህ ቤት  fans    #ሙስሊም
06/08/2025

ለፕሮፋይል የሚሆን ውብ የአላህ ቤት fans #ሙስሊም

ውብና እጅግ  የተዋባ መስጂድ ዱባይ ላይ ልዩ ስሙ ሻርጃ ላይ  ማሻአላህ በሉልኝ ?
06/08/2025

ውብና እጅግ የተዋባ መስጂድ ዱባይ ላይ ልዩ ስሙ ሻርጃ ላይ ማሻአላህ በሉልኝ ?

06/07/2025

ቁርአን ውስጥ እጅግ የሚማርከኝ አንቀፅ

21/06/2025

ፈርድ ሶላት ነው ። እየሰገድከው ዉዱእ ብታጠፋ ተመልሰህ መስገድ ማትችለው ፣
ሱና ቢሆን ግን ተመልሰህ ምትሰግደው ሶላት ምንድን ነው ?🤔🧐 ተሳተፉ

ፔፕ ጋርዲዮላ ይባላል አለም ላይ እጅግ ታዋቂ ስኬታማና ተፅእኖ ፈጣሪ  የእግር ኳስ ክለብ  አሰልጣኝ  ነው ። ሰሞኑን  የክብር ዲግሪ ተሰጥቶት ነበር ከሱም በላይ ያስደሰተኝና ያስደነቀኝ ንግ...
14/06/2025

ፔፕ ጋርዲዮላ ይባላል አለም ላይ እጅግ ታዋቂ ስኬታማና ተፅእኖ ፈጣሪ የእግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ነው ። ሰሞኑን የክብር ዲግሪ ተሰጥቶት ነበር ከሱም በላይ ያስደሰተኝና ያስደነቀኝ ንግግር መናገሩ ነው !

ከፔፕ ጋርዲዮላ የክብር ዶክትሬት ሸልማት ንግግር የተወሰደ:-

"በፍልስጤም እና በጋዛ እየሆነ ያለውን የሚገልፅ አንድ ተረት አለ..
በአንድ ጫካ ውስጥ ከባድ እሳት ተነስቶ እየነደደ ነበር። በውስጡ ያሉት እንስሳት በሙሉ እርዳታ የሚሰጣቸው አጥተው በፍርሃት ተዋጡ።
የደኑ አካል የሆኑ ትናንሽ ወፎች ግን በሰማይ እየበረሩ፤ኢምንት ውሃ በጫካው ላይ በመርጨት እሳቱን ለማጥፋት ይሞክሩ ነበር።
ይህን የተመለከተው እባብም ሳቀና ፦"አንቺ ወፍ! ምን እያደረግሽ ነው?እሳቱን በፍጹም ማጥፋት አትችዪም አላት።"
ትንሿ ወፍ መለሰችለት:- "አዎ! አውቃለሁ።"
እባቡም፦ "ታዲያ ምን እያደረግሽ ነው?" ሲል ጠየቃት።
ወፊቱም፦"ድርሻዬን እየተወጣሁ ነው።" አለችው።

ይህ የኛው የዓለም ታሪክ ነው… ሰዎቹ ተጽዕኗችን እጅግ ትንሽ እንደሆነ ይነግሩናል።ነገር ግን እውነታው የዚህ ዓለም ኃይል ከብቃት በላይ በምርጫ ላይ መሆኑ ነው።ኃይላችን ስለ መርህ መቆም እና በሚያስፈልግ ጊዜ ዝም ላለማለት መወሰን ነው።"

ይህ ድንቅ እውነት ነው።ይህ የጋዛ ጦርነት እንደወፊቷ የአቅማቸውን ያህል ድርሻቸውን ከሚወጡ፤እነዚህ ላይ እስከሚያሾፉት የእባቡ አምሳያዎችን አሳይቶናል።

ፔፕበጋዛ እየደረሰ ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፍ ለዓመት ያክል መላ አካሉን እንዳሳመመው ገልጿል።ስለጋዛዊያን ህፃነት ሰቆቃ ድምፁን አሰምቷል።ሰዎች የሚለኩት በመሰል የችግር ጊዜ አቋማቸው ነውና ፔፕ ሰብዓዊነት የሚሰማው ሰው እንደሆነ በትልቁ የሽልማት መድረኩ ላይ አሳይቷል።
በሽልማቱ ላይ አለም ስለዘነጋቸው የፍልስጤም ህፃናት ድምፅ ሆኖዋቸዋል

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸው ወቅት ስለ ጋዛ “ በጋዛ እያየን ያለነው ነገር በጣም ያማል ሙሉ አካሌን ይሰማኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም " በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት እናቶች እና አባቶች እየተሰቃዩ ነው “ ሲሉ ከጋዛ በተጨማሪም በዩክሬን እና ሱዳን ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
#ሱብሀናላህ አላህ ሂዳያን ይስጠው ማሻአላህ ዱአ አርጉለት እስልምናን አላህ ይወፍቅህ አቦ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሙስሊም ተማሪዎች ኢስላማዊ መድረክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to የሙስሊም ተማሪዎች ኢስላማዊ መድረክ:

Shortcuts

Share