07/10/2025
① ባልሽን በቁልምጫ ጥሪው።
② በቤተሰቡ ውስጥ መሪ እንዲሆን ፍቀጂለት።
③ እሱ ከተበሳጨ ወይም ከተናደደ አትከራከሪ።
④ እሱ ሲቆጣ ዝም በይና በኋላ ይቅርታ ለመጠየቅ ተነጋገሪ።
⑤ አንቺ እሱን ካስከፋሽው ወዲያውኑ "ይቅር በለኝ ፍቅሬ" በይው፤ ይቅር ሲልሽ ደግሞ አመስግኚው።
⑥ በሌሎች ሰዎች ፊት ስለ እሱ ጥሩ ነገሮችን ተናገሪ።
⑦ እናቱን አክብሪ።
⑧ ለወላጆቹ ስጦታ እንዲገዛ አበረታቺው፤ ይህን ማድረጉ ላንቺም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ ያነሳሳዋል።
⑨ በተለይ ገንዘብ ሲያጥረው የሚወደውን ምግብ ሰርተሽ አስደንቂው/ሰርፕራይዝ አድርጊው።
⑩ አንቺ እቤት እያለሽ ለባልሽ ምግብ በሰራተኛ እንዳታቀርቢ፤ ራስሽ አቅርቢለት።
⑪ ከውጭ ሲመጣ በእቅፍ ተቀበዪው፤ ቦርሳዎቹንና ልብሶቹን እንዲያወልቅ እርጂው።
⑫ አብራችሁ ውጪ ስትሆኑ ፈገግ በይለትና ፍቅርን ስጪው።
⑬ በልጆቻችሁ ፊት አመስግኚው።
⑭ ሻወር ሲወስድ ጀርባውን እጠቢለት።
⑮ በምሳ ዕቃው ወይም በቦርሳው ውስጥ የፍቅር መልዕክት አስቀምጪለት።
⑩ እንደናፈቅሽው ለመንገር ብቻ ደውዪለት።
⑰ ስልክ ሲያነሳ "እወድሃለሁ" በይው።
⑱ ጠዋት ላይ ለአንድ አስፈላጊ ነገር ቀስ ብለሽ ቀስቅሺው፤ ፍቅር እንዲሰማው አድርጊ።
⑲ እሱን ባል በማድረግሽ እድለኛ እንደሆንሽ ንገሪው።
⑳ ያለምንም ምክንያት እቀፊው።
㉑ በሕይወትሽ እሱን ስለሰጠሽ ፈጣሪን አመስግኚ።
㉒ ሁልጊዜ ጸልይለት።
㉓ በተለይ ከመተኛታችሁ በፊት አብራችሁ ጸልዩ።