11/01/2022
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያየ💚💛❤🇪🇹
እንኮን በሰላም መጣችሁ�
11/01/2022
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያየ💚💛❤🇪🇹
11/01/2022
ለቅዱስ ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ የሕክምና ግብዓቶች ድጋፍ ተደረገ
********************
የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ለቅዱስ ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ፥ ድጋፉ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አሸባሪው ህወሓት ባደረሰው ዝርፊያና ውድመት የተጎዱ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የተበረከተ ነው ብለዋል።
በዚህም በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በአቅራቢያቸው የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።
የተጎዱ የጤና ማዕከላትን መልሶ ማቋቋም ከሁሉም ተቋማት እና ዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታልም መድሃኒቶች እና የንጽህና መጠበቂያዎችን ወደ ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታል ለማድረስ ጉዞ መጀመሩን መናገራቸውን ከጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
11/01/2022
03/01/2022