Students News Channel

Students News Channel

Share

ተማሪ ነክ የሆኑ ትክክለኛ መረጃዎች ሁሉ ይቀርቡበታል በዚህ የfacebook ገጽ በዋናው የቴሌግራም ቻናላችን ማለትም በ t.me//nationalexamsresult ላይ ከሚዳሰሱት መረጃዎች በተጨማሪ ሌሎችም ትክክለኛ እና እውነተኛ መረጃዎች ይቀርቡበታል

25/05/2022

"ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንዲራ ውጪ በት/ቤታችን ውስጥ አይሰቀል " የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች

አዲስ አበባ ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተፈጠረው ምንድን ነው?

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን for more information join our telegram channel

( t.me//NATIONALEXAMSRESULT )

ባሳለፍነው ሳምንት የገላን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦሮምያ ክልል ባንዲራ እንዲሰቀል እና የክልሉ መዝሙርም እንዲዘመር ይታዘዛል። ይሁንና ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር እና ባንዲራ ውጪ አንዘምርም አንሰቅልምም በሚል ቅሬታቸውን ያሰማሉ።

ከትናንት ወዲያ ሰኞ ዕለት ደግሞ ጠዋት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ከተዘመረ እና ብሔራዊ ባንዲራ ከተሰቀለ በኋላ የኦሮምያ ክልል ባንዲራ ሊሰቀል እና የክልሉ መዝሙር ሊዘመር ሲል ተማሪዎች ወደክፍል መግባት ይጀምራሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና አንዳንድ መምህራን በግዴታ ካልዘመራችሁ ባንዲራውንም
ካልሰቀላችሁ ብለው ተማሪዎችን ማስገደድ ሲጀምሩ ተማሪዎች ይህንን ሳይቀበሉ ቀርተው ወደ ክፍላቸው ይገባሉ። ትናንትናም እንዲሁ ይቀጥላል።

ዛሬ ጠዋት ግን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቁጥራቸው ብዙ የሚሆኑ በከፊል የታጠቁ ፖሊሶችን በጊቢው ውስጥ እና አካባቢ በማሰማራት በግዴታ ሊያስዘምራቸው በመሞከሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማሰማት ይጀምራሉ። ኃይል በመጠቀም ለማስገደድ የሞከሩ መምህራንም ነበሩ።

የተማሪዎቹን ጩኸት የሰማው የአካባቢው ኅብረተሰብ እና ወላጆችም በመደናገጥ ወደ ትምህርት ቤቱ ያመራሉ። ተማሪዎችም በዚህ ሁኔታ መማር እንችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን ሁኔታው ሳይባባስ ወደቤት ተበትነዋል።

ተጨማሪ መረጃ አጣርተን እናደርሳለን

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
For more info. Join us on Telegram
t.me//NATIONALEXAMSRESULT

31/03/2021

#ጥያቄ
የማለፊያ ነጥብ እንዴት ይሰላል🤔

➖ መልስ

የብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ነጥብ የሚሰላው 3 ዋና ነጥቦችን መነሻ በማድረግ ነው።

📌 ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አጠቃላይ ብዛት

📌 የዩኒቨርሲቲዎች ብዛት

📌 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸው ተማሪ የመቀበል አቅም

በዚህ መሰረት እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ በሚሰጣቸው እያንዳንዱ ዲፓርትመንት ( የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ) የሚቀበለውን የተማሪ ብዛት ለ ያሳውቃል፡፡

ከዚህ በኋላ ከላይ ያሉት 3 ነጥቦች ታሳቢ ተደርገው ተፈታኝ ተማሪዎች ያመጡት ውጤት አቬሬጅ ይወሰድና ማለፊያ ነጥቡ ስንት መሆን እንዳለበት ይቆረጣል።

በዚህ ጊዜ የማለፊያ ነጥብ የሚቀነስላቸው ተማሪዎች ማለትም

📌 ሴት ተማሪዎች
📌 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች እና
📌 የአርሶ አደር አካባቢ ተማሪዎች እንዲሁም 📍 ከልዩ ድጋፍ ክልል የተፈተኑ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ ከዋናው የማለፊያ ነጥብ ላይ ተንተርሶ ዝቅ ተደርጎ ይቆረጣል፡፡


መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
t.me//NATIONALEXAMSRESULT

26/02/2021

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ፦

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ኢንጅነር አስቴር ይትባረክ ዛሬ እንዳስታወቁት በክልሉ 12 ሺህ ያህል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይገኛሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 29/2013 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጠው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች በትግራይ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተው ፈተና እንዲወስዱ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ አክሱም፣ በአድግራትና ራያ ዩኒቨርስቲዎች እስከ የካቲት 23/2013ዓ.ም. ድረስ በአካል ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት ወራት የመማር ማስተማር ሂደት ባይኖርም ተማሪዎች ቀደም ባሉት ዓመታት የትምህርት ዝግጅት እያደረጉ በመምጣታቸው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንዲቀመጡ ያስችላችዋል ብለዋል።

ተማሪዎቹ ቀደመው በዩኒቨርሲቲዎቹ በመገኘት ለአስር ቀናት ያህል ዝግጅት እንዲያደርጉ እድል መሰጠቱን ኢንጅነር አስቴር ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን በዚህ link ተቀላቀሉን
t.me//NATIONALEXAMSRESULT

26/02/2021

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ የሙያ መስክ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል።

የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ፎርም ሲሞሉ የሙያ መስክ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የሙያ መስክ ምርጫውን በተመለከተ ዛሬ ከሰአት በሌላ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ደውለን አያይዘን የጠየቅናቸው ሲሆን በሰጡን ምላሽም በቀጣዪ ዓመይ ማለትም በ2014 ዓ.ም ሊተገበር ለታሰበው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ግብዓት እንዲሆን እና ዩኒቨርሲቲዎችንም በሚሰጡት የትምህርት ዘርፍ በመከፋፈል ተማሪዎችን እንደየክህሎታቸው ለመመደብ እንዲያስችል ታስቦ ነው" ብለውናል።

ይሁንና አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ የተወሰኑ ት/ቤቶች ይህንን ፎርም እያስሞሉ አይደለም ስንል ላነሳነው ጥያቄ " በሌላ ጊዜ ማስሞላታቸው አይቀርም ሁሉም ተፈታኝ ፎርሙን ይሞላል ሲሉ ገልጸውልናል"


መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን በዚህ link ተቀላቀሉን
t.me//NATIONALEXAMSRESULT

Telegram: Contact @NATIONALEXAMSRESULT 21/09/2020

UPDATE| የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከጥቅምት ወር እንዲጀምር ታቅዷል
[ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ]

ሁለተኛ ሴሚስተር ያልጀመሩ ተማሪዎችን በሁለት ወር፣ የሴሚስተሩን 25 በመቶ የተማሩትን ደግሞ በ45 ቀናት ማካካሻ ለማስጨረስም ታሳቢ ተደርጓል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ነባር ተማሪዎችን በሶስት መርሃ ግብር፤ ተመራቂ ተማሪዎችን ደግሞ እስከ ሁለት ወር ለማሰጨረስ ነው የታሰበው።

ተመራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች ጉዳይ እየታየ የሚቀጥል ሲሆን ትምህርት ማስቀጠያው ከጥቅምት እንዲጀምርም ታስቧል።

በአንድ ክፍል ውስጥ ከ25 እስከ 30 ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዷል፤ ሌሎች መማሪያ ክፍሎች ደግሞ የመያዝ አቅማቸውን ግማሽ ብቻ እንዲይዙ ይደረጋል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን

Telegram: Contact @NATIONALEXAMSRESULT

26/08/2020

Be a member in our telegram channel and win a lot of gifts T.Me//NATIONALEXAMSRESULT

07/05/2020

ሪፖርቱን በፖለቲካ ማሳበብ አዕምሮ ቢስነት ነው❗️



አንዳንዶች ገና ካሁኑ የዛሬውን ሪፖርት የፖለቲካ ፍጆታ ነው እያሉ እየተሳለቁ ነው፡፡ በተለይም በነዚህ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከ #ምርጫ ጋር ተያይዞ እየተነሱ ካሉ ውዝግቦች ጋር በማያያዝ የሚለፈልፉ አልጠፉም🤦‍♂

ለማንኛውም በዚህ ሰአት ለመረጃ የሚያዋጣን የጤና ሚኒስቴር እንጂ የምርጫ ቦርድ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም😒

ከምን ጊዜውም በላይ ጥንቃቄ የሚያስፈልገን ጊዜ እየቀረበ ይመስላል❗️

መዘናጋት እጅግ ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል!

የዛሬው ሪፖርት እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገን ማሳያ ነው።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች

➡️ 19 ሰዎች የውጭ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ንክኪ የላቸውም

➡️ 3 ሰዎች የጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️ 3 ሰዎች በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️ 21 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

➡️ 2 የደ/ብ/ሕ/ ክልል ነዋሪዎች

➡️ 2 የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ናቸው።

በተለይም በአዲስ አበባ የተጠቁ ነዋሪዎች ቁጥር ከፍ ያለ ነው።

መዘናጋታችንን ካላቆምን ነገ ከነገ ወዲያ የከፉ ሪፖርቶችን መስማታችን አይቀርም እና አደራ ጥንቃቄ አይለየን❗️


ለበለጠ ፈጣን መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
T.ME/NATIONALEXAMSRESULT

STUDENTS NEWS CHANNEL 20/04/2020

ሰበር ዜና

#ሼር

STUDENTS NEWS CHANNEL ❗️ሰበር ዜና❗️ አፍሪካዊቷ ማዳጋስካር ለኮሮናቫይረስ ባህላዊ መድሀኒት አግኝቻለው ብላለች ቲቪ ኤም በተባለ የብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ዛሬ ቀርበው ንግግር ያደረጉት የማዳጋስካር ...

31/03/2020

🚨ተጠንቀቁ -አንብባችሁም ለራሳችሁ ብቻ አታስቀሩ እባካችሁ- ሼር አስርጉት‼️

እንደሚታወቀው በኮሮና በሽታ ምክንያት ሁላችንም ጭንቀት ውስጥ ነን።
ነገ ደግሞ የፈረንጆቹ አፕሪል 1 ወይም April fools day ነው። ስለዚህ ሀላፊነት የሌለው አንዳንድ ድንዙዝ አላዋቂ ቂል ሰው አይጠፋም እና ነገ ከበድ ያለ ነገር በማህበራዊ ሚዲያም ይሁን ሰዎችም ቢነግሯችሁ ሳታጣሩ ምንም እርምጃ አትውሰዱ።

ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነውና ጊዜውም አስፈሪ ነውና እባካችሁ ብዙዎች እንዳይሸወዱ በጭንቅ ላይ ጭንቅ እንዳይሆንባቸው ይህንን መረጃ ለወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ አጋሩ!!
🙏


ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
T.ME/NATIONALEXAMSRESULT

16/03/2020

አቶ አርኣያ be like
"ከባለፈው Entrance የተረፍሽ አሁን አለቀልሽ"

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

On Telegram T. Me//nationalexamsresult
Addis Ababa