21/09/2023
Mathematics Department, AAU
Addis Ababa University
College of Natural and Computational Sciences
Department of Mathematics
21/09/2023
21/08/2023
A Brief History of Higher education in Ethiopia
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን አቅጣጫ ተሰጠ::
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
ነሃሴ 09/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር ) በ2016 የትምህርት ዘመን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ነሃሴ 09/2015ዓ. ም በተጻፈ ደብዳቤ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
እስካሁን በመሰጠት ላይ ያሉ የቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በ2016 ዓ.ም በዝርዝር ተፈትሸውና ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ልየታ ጋር መጣጣማቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በጻፉት ደብዳቤ የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶች ባሉበት እንዲቆዩ፣ መጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ እንዲሁም በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።
አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ባሉበት እንዲቆዩ የተወሰነው የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን የመክፈት ስራ መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ደብዳቤውን👇 ያገኙታል
28/07/2023
https://www.facebook.com/100064682287722/posts/681758053990265/?mibextid=CDWPTG
የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test/ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሃገር በሁሉም ፕሮግራሞች ሊሰጥ ነዉ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡//፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሀምሌ 20/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test/ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሃገር በሁሉም ፕሮግራሞች ሊሰጥ ነዉ።
ይህንንም በወጥነት ለማስፈጸም እንዲቻል ለሁሉም የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተጻፈ ደብዳቤ ዩኒቨርስቲዎቹ የ2016 ትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ማስታወቂያ በማዉጣትና በመመዝገብ እጩ ተማሪዎችን እስከመስከረም 10/2016 ዓ.ም እንዲያሳዉቁ ተገልጿል፡፡
የደብዳቤውን ሙሉ ይዘቱን በተጠቀሰው ሊንክ ያገኛሉ http://ln.run/p0Bc2
በተጨማሪም :-👇
ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ያስጀመረውን ትምህርት ለትውልድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ንቅናቄ ለመደገፍ እንዲሁም በቀጥታ የተማሩበትን ትምህርት ቤት ለመደገፍ
https://sip.moe.gov.et እንዲሁም
ትምህርት ሚኒስትር ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቅርብ ያስጀመረውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ፖርታል ለማግኘት
https://learn-english.moe.gov.et ዌብ ፖርታሎቻችንን ይጎብኙ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa