ኦንላይን ስራ

ኦንላይን ስራ

Share

በዚህ ፔጅ ስለ ኦንላይን ስራ መረጃዎችን ያገኛሉ። ስለ ዩቱብ?

24/03/2022

ከስኬትህ ይልቅ ውድቀትህ ያስተምርሃል። ህይወትህን የሚቀይር ትምህርት የምታገኘው ከስኬትህ ሳይሆን ከውድቀትህ ነው። ስለዚህ ፈጥነህ ውደቅና ሳይረፍድ የስኬትን ሚስጥር ተማር።

Your failures teach you more than your success. You will learn a lesson that will change your entire life from your failure, not from your success. So, hurry up to fail forward and acquire the secret of success before it's too late.

ለመውደቅ ከፈራህ ሽባ ሆነህ ነው የምትቀረው። ለመውደቅ አትፍራ። ህፃን ልጅ እየወደቀ እየተነሳ ነው ቆሞ መሄድ የሚለምደው። የዛኔ ባንወድቅ ኖሮ ዛሬም ቆመን መሄድ አንችልም ነበር። ከዚህ ቀደም ተለማምደን ቢሆን ኖሮ አሁን ምርጥ ስፖርተኞች እንሆን ነበር። ስለዚህ የውድቀት ተሞክሮ በጊዜ ይውጣልህ! experience it now. ውድቀትን ራሱን ተለማመደው። የምትሞክረውን ነገር አሁኑኑ ጨክነህ ሞክረው። ከፈለገ ይበላሽ፣ ይሳሳት፣ ይጨመላለቅ፣ ሰዎች አይውደዱት፣ ይስደቡህ፣ ይሳቁብህ፣ ይቀልዱብህ፣ ምን ችግር አለው። አትሸማቀቅ። ጥሩ አድርገህ ለመስራት ግን የቻልከውን ጥረት አድርግ። እየታወቀህ የሚያስወቅስ ስራ አትስራ። ለዚህ የሚሆን ደግሞ ብዙ እምቅ ሀይል እንዳለህ አምናለሁ።

ሆኖም ግን ማንኛውንም ስራ ቢሆን፣ ገና እንደጀመርከው ምርጥ አድርገህ አትሰራውም፣ ፍፁም አይሆንም። ፍፁም የሰው ስም ብቻ ነው። ፍፁም ይሆናል ብለህ አትጠብቅ። ታሳስተዋለህ፣ ሁሌም እንከን ይኖራል፣ ደጋግመህ በሰራኸው ቁጥር ግን እንከኑ እየቀነሰና እየተሻሻለ ይሄዳል። አሁንም ግን ፍፁም አይሆንም። ፍፅምና የለም። ፍፅምና ወይም ፐርፌክሽን የስኬት እንቅፋት ነው። አኪውሬሲ ሌቭል ላይ ለመድረስ ግን ሞክር።

ህይወትህን ተለማመድበት፣ እንደፈለክ ተለማመድ። ልትለማመድ አይደልንዴ ወደዚህ አለም የመጣኸው⁉️ ሲወለድ ማንም አዋቂ ሆኖ አልተወለደም። ደካማ ሆኖ ነው የተወለደው። ነገር ግን የሰው ልጅ ማደግና መበልፀግ የሚችል ክቡር ማንነት ተሰጥቶታል። ሁሉም የመማርና የማወቅ ችሎታ ይዞ ይወለዳል። ስለዚህ እያንዳንዷን ቀን እንደቀላል አትመልከታት። እያንዳንዷን ቀን በከንቱ አታሳልፋት። እድልህን ተጠቀምበት!! በየቀኑ፣ ለማድረግ የምትፈራቸውን ነገር ግን ብታደርጋቸው ህይወትህን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ነገሮችን ለማድረግ ተደፋፈር፣ ሞክር፣ ጀምር፣ ተለማመደው፣ አድርገው!! ይበላሽ፣ አትፈር፣ እንኳን ይሄን የመሰለ የተቀደሰ ሀሳብ ይዘህ ሰው ብዙ አስኮናኝ ነገር ይሰራ የለምንዴ?? ለምን ትሸማቀቃለህ!

Practice makes you perfect. የሚሉት ፈረንጆቹ ወደው አይደለም። አይተውት ነው። ገጥሟቸው ነው። አልፈውበት ነው።
ትምህርትና ልምምድ አንተን ብቁ የማድረግ ኃይል አላቸው። ለእውቀት ቦታ ሰጥተህ ከተማርክና ከተለማመድክ ሰው የሰራውን ሁሉ መስራት ትችላለህ። አብዝተህ የተለማመድከውን ነገር፣ ረጅም ጊዜ ቢወስድብህም ትካነዋለህ። ማስተር ታደርገዋለህ። ትጠበብበታለህ። በፊት በጣም ትቀናባቸው ከነበሩት ሰዎች በላይ አድርገህ ትሰራዋለህ። እና እባክህ ማንኛውንም ነገር ከብዶኛል አትበል። በቶሎ ተስፋ አትቁረጥ፣ ገና መች በደንብ መከርከው? ስታየው አቀበት አይሁንብህ፤ ከልብህ ከፈለከው፣ ሰበብ አታብዛ። ተማረው፣ ተለማመደው፣ ኑርበት፣ እለፍበት፣ ልፋበት_ ይገባዋልና፣ ተለማመደው፣ ከዚያም... ይገባሃል!

ማንኛውም ነገር የልምምድ ውጤት መሆኑን አትዘንጋ። ዛሬ በየብስ፣ በባህርና በህዋ ላይ የሚሄዱ ሰው ሰራሽ ነገሮች ሁሉ ገና በመጀመሪያው ሙከራ የተሰሩ ሳይሆን በብዙ ልምድ የተሰሩ ነገሮች ናቸው። የብዙ ውድቀት ውጤቶች ናቸው።

ስለዚህ ውድቀትን አትፍራው። ወድቆ የተነሳ፣ አገር ያነሳ። ነው የሚባለው ባገራችን። ስኬታማ ለመሆን በዚህ የስተት፣ የልምምድና የሙከራ መንገድ ማለፍ አለብህ!

ተስፋ ቆርጠህና ግራ ተጋብተህ አትቀመጥ ወንድሜ! መሄጃው ጠፍቶብሽ፣ ዙሪያው ጨልሞብሽ አትቀመጭ እህቴ! ተስፋ ሰንቂ፣ አሁንም ጊዜው አልረፈደም መማርና ማዳበር ያለብሽን ክህሎት በቶሎ መማር ጀምሪ! መውጫ መንገዱን ፈልጊ፣ የሚገባውን ዋጋ ከከፈልሽ ታገኝዋለሽ!

በመጨረሻም፣ ህይወታችሁን መቀየር ከፈለጋችሁ የምታገኙትን መልካም ትምህርት ወደ ተግባር ቀይሩት! እጅግ በጣም አስደማሚ ለውጥ ያመጣላችኋል!! የተግባር ልምድ ማዳበሩም ህይወት ቀያሪ ነው።

በሌላ አስተማሪና አነቃቂ ክፍለ ጊዜ እንዲንገናኝ Like ማድረጋችሁን አትርሱ። 👉 https://www.facebook.com/amelekaket የ YouTube ቻነላችንንም ሰብስክራይብ ብታደርጉ በቀጣይ የምንለቀውና እንዴት የህይወት ግብን ማውጣትና ማሳካትም እንደሚቻል በግልፅ የሚያሳየው ቪዲዮ ይደርሳችኋል። እዚህ ጋ (https://www.youtube.com/channel/UC0MJVoHVowEPptclVSvsQ1g?sub_confirmation=1) ባንድ ጠቅታ ብቻ ሰብስክራይብ ማድረግ ትችላላችሁ። እናመሰግናለን። ❤️👍

ትምህርትቱን በቪዲዮ ለመመልከት ይሄን 👉 ሊንክ (https://www.youtube.com/watch?v=UvY0TXDbXtM) ይጫኑ።
ድህረገፃችንን ይጎብኙ። 👉 www.Tmhrt.com

Subscribe Our YouTube Channel 👉https://www.youtube.com/channel/UC0MJVoHVowEPptclVSvsQ1g?sub_confirmation=1👍

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

NL_12_4970 Street
Addis Ababa